ኢሳይያስ
47 አንቺ ድንግል የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ፣+
ወርደሽ አፈር ላይ ተቀመጪ።
2 ወፍጮ ወስደሽ እህል ፍጪ።
መሸፋፈኛሽን አንሺ።
ቀሚስሽን አውልቂ፤ ባትሽን ግለጪ።
ወንዞቹን ተሻገሪ።
3 እርቃንሽ ይገለጣል።
ኀፍረትሽም ይታያል።
እኔ የበቀል እርምጃ እወስዳለሁ፤+ ማንም ሰው ሊያግደኝ አይችልም።*
6 ሕዝቤን ተቆጣሁ።+
አንቺ ግን ምሕረት አላሳየሻቸውም።+
በሽማግሌው ላይ እንኳ ሳይቀር ከባድ ቀንበር ጫንሽ።+
7 አንቺም “ሁልጊዜ ብሎም ለዘላለም እመቤት* እሆናለሁ” አልሽ።+
እነዚህን ነገሮች ልብ አላልሽም፤
ነገሩ ምን ፍጻሜ እንደሚኖረው አላሰብሽም።
8 በመሆኑም አንቺ ለሥጋዊ ደስታ ያደርሽ፣+
ተማምነሽ የተቀመጥሽና
በልብሽ “እኔ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።+
መበለት አልሆንም።
በምንም ዓይነት የወላድ መሃን አልሆንም” የምትዪ ሴት ሆይ፣+ ይህን ስሚ።
9 ሆኖም እነዚህ ሁለት ነገሮች ይኸውም
የወላድ መሃንነትና መበለትነት በአንድ ቀን በድንገት ይደርሱብሻል።+
10 አንቺ በክፋትሽ ታምነሻል።
“ማንም አያየኝም” ብለሻል።
ያሳቱሽ ጥበብሽና እውቀትሽ ናቸው፤
በልብሽም “እኔ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም” ትያለሽ።
11 ሆኖም ጥፋት ይመጣብሻል፤
ደግሞም ከዚህ ሊያስጥልሽ የሚችል ድግምት የለሽም።*
መከራ ይደርስብሻል፤ ልታስወግጂውም አትችዪም።
አይተሽው የማታውቂው ጥፋት በድንገት ይደርስብሻል።+
12 እንግዲያው ከልጅነትሽ ጀምሮ ስትደክሚበት የነበረውን
ድግምት ሁሉና ብዛት ያለው የጥንቆላ ድርጊት+ መፈጸምሽን ቀጥዪ።
ምናልባት ይጠቅምሽ ይሆናል፤
ሰዎችን ለማሸበር ይረዳሽ ይሆናል።
13 በመካሪዎችሽ ብዛት እጅግ ተዳክመሻል።
በሰማያት ያሉ ነገሮችን የሚያመልኩ፣* ከዋክብትን በትኩረት የሚመለከቱ፣+
አዲስ ጨረቃም ስትወጣ
በአንቺ ላይ ስለሚመጣው ነገር የሚተነብዩ ሰዎች፣
እስቲ አሁን ተነስተው ያድኑሽ።
14 እነሆ፣ እነሱ እንደ ገለባ ናቸው።
እሳት ያቃጥላቸዋል።
ራሳቸውን* ከነበልባሉ ኃይል ማዳን አይችሉም።
ይህ ሰዎች የሚሞቁት ፍምም ሆነ
በፊቱ ተቀምጠው የሚሞቁት እሳት አይደለም።
15 ከልጅነትሽ ጀምሮ አብረሻቸው ስትደክሚ የነበሩት
ድግምተኞች እንዲሁ ይሆኑብሻል።
እያንዳንዳቸው የመረጡትን አቅጣጫ ተከትለው ይባዝናሉ።*
አንቺን የሚያድን አይኖርም።+