ኢሳይያስ
50 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“እናታችሁን በሰደድኳት ጊዜ የፍቺ የምሥክር ወረቀት+ ሰጥቻታለሁ?
እናንተንስ የሸጥኳችሁ ለየትኛው አበዳሪዬ ነው?
2 ታዲያ በመጣሁ ጊዜ እዚህ ማንም ያልነበረው ለምንድን ነው?
በተጣራሁስ ጊዜ የሚመልስ ሰው የጠፋው ለምንድን ነው?+
እጄ አጭር ሆና እናንተን መዋጀት ተስኗታል?
ወይስ እናንተን ለመታደግ የሚያስችል ኃይል የለኝም?+
ዓሣዎቻቸው ውኃ ባለማግኘታቸው ይበሰብሳሉ፤
በውኃ ጥምም ይሞታሉ።
3 ሰማያትን ጨለማ አለብሳለሁ፤+
ማቅንም መሸፈኛቸው አደርጋለሁ።”
በየማለዳው ያነቃኛል፤
እንደ ተማሪ አዳምጥ ዘንድ ጆሮዬን ያነቃል።+
5 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ጆሮዬን ከፍቷል፤
እኔም ዓመፀኛ አልነበርኩም።+
ጀርባዬን አልሰጠሁም።+
6 ለሚገርፉኝ ጀርባዬን፣
ጢም ለሚነጩም ጉንጮቼን ሰጠሁ።
ፊቴን፣ ከሚያዋርዱ ነገሮችና ከትፋት አልሰወርኩም።+
7 ሆኖም ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ይረዳኛል።+
ስለዚህ አልዋረድም።
ከዚህም የተነሳ ፊቴን እንደ ባልጩት አደረግኩ፤+
ለኀፍረት እንደማልዳረግም አውቃለሁ።
8 ጻድቅ መሆኔን የሚመሠክርልኝ ቀርቧል።
በአንድነት እንቁም።*
ከእኔ ጋር ሙግት ያለው ማን ነው?
እስቲ ወደ እኔ ይቅረብ።
9 እነሆ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ይረዳኛል።
ታዲያ ጥፋተኛ ነህ ሊለኝ የሚችል ማን ነው?
እነሆ፣ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ።
ብል ይበላቸዋል።
10 ከመካከላችሁ ይሖዋን የሚፈራ፣
የአገልጋዩንም ድምፅ የሚሰማ ማን ነው?+
ብርሃን በሌለበት በድቅድቅ ጨለማ የሄደ ማን ነው?
በይሖዋ ስም ይታመን፤ በአምላኩም ይደገፍ።*
11 “እነሆ፣ እናንተ እሳት የምታያይዙ፣
የእሳት ፍንጣሪ የምታበሩ ሁሉ፣
በእሳታችሁ ብርሃን፣
ባያያዛችሁትም እሳት ብልጭታዎች መካከል ሂዱ።
ከእጄ የምትቀበሉት ይህ ነው፦
በከባድ ሥቃይ ትጋደማላችሁ።