ኢሳይያስ
56 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
2 ይህን የሚያደርግ ሰው፣
ደግሞም ይህን አጥብቆ የሚይዝ፣
ሰንበትን የሚጠብቅና የማያረክስ፣+
እንዲሁም ከማንኛውም ዓይነት ክፋት እጁን የሚመልስ የሰው ልጅ ደስተኛ ነው።
3 ከይሖዋ ጋር የሚቆራኝ የባዕድ አገር ሰው+
‘ይሖዋ ከሕዝቡ እንደሚለየኝ ጥርጥር የለውም’ አይበል።
ጃንደረባም ‘እነሆ፣ እኔ ደረቅ ዛፍ ነኝ’ አይበል።”
4 ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “ሰንበቶቼን ለሚጠብቁ፣ ደስ የሚያሰኘኝን ነገር ለሚመርጡና ቃል ኪዳኔን አጥብቀው ለሚይዙ ጃንደረቦች፣
5 በቤቴና በቅጥሮቼ ውስጥ
ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች የሚሻል ነገር፣
ይኸውም የመታሰቢያ ሐውልትና ስም እሰጣቸዋለሁ።
ለዘላለም የማይጠፋ ስም እሰጣቸዋለሁ።
6 እሱን ለማገልገል፣ የይሖዋን ስም ለመውደድና
የእሱ አገልጋዮች ለመሆን
ከይሖዋ ጋር የሚቆራኙትን የባዕድ አገር ሰዎች፣+
ሰንበትን የሚጠብቁትንና የማያረክሱትን፣
ቃል ኪዳኔንም አጥብቀው የሚይዙትን ሁሉ፣
7 ቅዱስ ወደሆነው ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፤+
በጸሎት ቤቴም ውስጥ እጅግ እንዲደሰቱ አደርጋቸዋለሁ።
የሚያቀርቧቸውም ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና መሥዋዕቶች በመሠዊያዬ ላይ ተቀባይነት ያገኛሉ።
ቤቴም ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ተብሎ ይጠራልና።”+
8 የተበተኑትን የእስራኤል ሰዎች የሚሰበስበው ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ+ እንዲህ ይላል፦
“አስቀድሞ ከተሰበሰቡት በተጨማሪ ሌሎችን ወደ እሱ እሰበስባለሁ።”+
9 እናንተ በሜዳ ያላችሁ አራዊት ሁሉ፣
እናንተ በጫካ የምትኖሩ አራዊት ሁሉ፣ ኑና ብሉ።+
10 ጠባቂዎቹ ዕውሮች ናቸው፤+ አንዳቸውም አላስተዋሉም።+
ሁሉም መናገር የማይችሉ ውሾች ናቸው፤ መጮኽ አይችሉም።+
ተጋድመው ያለከልካሉ፤ እንቅልፍም ይወዳሉ።
11 በቀላሉ የማይጠግቡ* ውሾች ናቸው፤
ጠገብኩ ማለትን አያውቁም።
ማስተዋል የሌላቸው እረኞች ናቸው።+
ሁሉም በገዛ ራሳቸው መንገድ ሄደዋል፤
እያንዳንዳቸው አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ይሻሉ፤ እንዲህም ይላሉ፦
12 “ኑ! የወይን ጠጅ ላምጣና
እስኪወጣልን ድረስ እንጠጣ።+
ነገም እንደ ዛሬ ይሆናል፤ እንዲያውም በጣም የተሻለ ይሆናል።”