የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 58
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኢሳይያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • እውነተኛ ጾምና የይስሙላ ጾም (1-12)

      • ሰንበትን በማክበር መደሰት (13, 14)

ኢሳይያስ 58:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 1:2፤ 31:6፤ 59:13

ኢሳይያስ 58:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 29:13፤ ሕዝ 33:32
  • +ኢሳ 1:14, 15

ኢሳይያስ 58:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሳችንን።”

  • *

    ወይም “ደስታ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሚል 3:14
  • +ዘሌ 16:29
  • +ኤር 34:15, 16፤ ሚክ 3:2-4

ኢሳይያስ 58:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሱን።”

ኢሳይያስ 58:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 34:8, 9
  • +ምሳሌ 28:27

ኢሳይያስ 58:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 41:1፤ 112:9፤ ምሳሌ 19:17፤ 22:9
  • +ሕዝ 18:7, 8፤ ያዕ 2:15, 16፤ 1ዮሐ 3:17

ኢሳይያስ 58:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 4:18
  • +ዘፀ 14:19፤ ኢሳ 52:12

ኢሳይያስ 58:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 32:6፤ 59:3

ኢሳይያስ 58:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የገዛ ነፍስህ።”

  • *

    ወይም “የተጎሳቆሉትንም ነፍሳት ብታረካ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 15:7, 8
  • +መዝ 37:5, 6

ኢሳይያስ 58:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስህን ያረካል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 49:10
  • +ኢሳ 61:11፤ ኤር 31:12

ኢሳይያስ 58:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ክፍተት ያላቸውን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ነህ 2:5፤ ኤር 31:38
  • +ኢሳ 61:4
  • +ነህ 6:1፤ አሞጽ 9:11, 14

ኢሳይያስ 58:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ደስ የሚያሰኝህን።”

  • *

    ቃል በቃል “እግርህን ብትመልስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ነህ 13:15፤ ኢሳ 56:2፤ ኤር 17:21
  • +ዘዳ 5:12-14

ኢሳይያስ 58:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በአባትህ በያዕቆብ ርስት እንድትደሰት አደርጋለሁ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 32:13
  • +መዝ 105:10, 11፤ ኤር 3:18

ተዛማጅ ሐሳብ

ኢሳ. 58:1ኢሳ 1:2፤ 31:6፤ 59:13
ኢሳ. 58:2ኢሳ 29:13፤ ሕዝ 33:32
ኢሳ. 58:2ኢሳ 1:14, 15
ኢሳ. 58:3ሚል 3:14
ኢሳ. 58:3ዘሌ 16:29
ኢሳ. 58:3ኤር 34:15, 16፤ ሚክ 3:2-4
ኢሳ. 58:6ኤር 34:8, 9
ኢሳ. 58:6ምሳሌ 28:27
ኢሳ. 58:7መዝ 41:1፤ 112:9፤ ምሳሌ 19:17፤ 22:9
ኢሳ. 58:7ሕዝ 18:7, 8፤ ያዕ 2:15, 16፤ 1ዮሐ 3:17
ኢሳ. 58:8ምሳሌ 4:18
ኢሳ. 58:8ዘፀ 14:19፤ ኢሳ 52:12
ኢሳ. 58:9ኢሳ 32:6፤ 59:3
ኢሳ. 58:10ዘዳ 15:7, 8
ኢሳ. 58:10መዝ 37:5, 6
ኢሳ. 58:11ኢሳ 49:10
ኢሳ. 58:11ኢሳ 61:11፤ ኤር 31:12
ኢሳ. 58:12ነህ 2:5፤ ኤር 31:38
ኢሳ. 58:12ኢሳ 61:4
ኢሳ. 58:12ነህ 6:1፤ አሞጽ 9:11, 14
ኢሳ. 58:13ነህ 13:15፤ ኢሳ 56:2፤ ኤር 17:21
ኢሳ. 58:13ዘዳ 5:12-14
ኢሳ. 58:14ዘዳ 32:13
ኢሳ. 58:14መዝ 105:10, 11፤ ኤር 3:18
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኢሳይያስ 58:1-14

ኢሳይያስ

58 “ጉሮሮህ እስኪሰነጠቅ ጩኽ፤ ምንም አትቆጥብ!

ድምፅህን እንደ ቀንደ መለከት አሰማ።

ለሕዝቤ ዓመፃቸውን፣

ለያዕቆብ ቤት ኃጢአታቸውን አውጅ።+

 2 እነሱ በየዕለቱ እኔን ይፈልጉኛል፤

ጽድቅ ይሠራ የነበረ፣

የአምላኩንም ፍትሕ ያልተወ ብሔር የሆኑ ይመስል+

መንገዶቼን ማወቅ ደስ እንደሚያሰኛቸው ይገልጻሉ።

በጽድቅ እንድፈርድላቸው ይጠይቃሉ፤

ወደ አምላክ መቅረብ ደስ ያሰኛቸዋል፦+

 3 ‘ስንጾም የማታየው ለምንድን ነው?+

ራሳችንን* ስናጎሳቁል የማታስተውለውስ ለምንድን ነው?’+

በምትጾሙበት ቀን የራሳችሁን ጥቅም* ስለምታሳድዱና

ሠራተኞቻችሁን ስለምትጨቁኑ ነው።+

 4 ጾማችሁ በጭቅጭቅና በጥል ያበቃል፤

እንዲሁም ያለርኅራኄ በቡጢ ትማታላችሁ።

ዛሬ እንደምትጾሙት እየጾማችሁ ድምፃችሁ በሰማይ ሊሰማ አይችልም።

 5 እኔ የመረጥኩት ጾም እንዲህ ሊሆን ይገባል?

ሰው ራሱን* የሚያጎሳቁልበት፣

እንደ እንግጫ ራሱን የሚደፋበት፣

መኝታውን በማቅና በአመድ ላይ የሚያነጥፍበት ቀን መሆን አለበት?

እናንተ ጾም የምትሉት፣ ይሖዋንም ደስ የሚያሰኝ ቀን ብላችሁ የምትጠሩት ይህን ነው?

 6 አይደለም፤ እኔ የመረጥኩት ጾም ይህ ነው፦

የክፋትን የእግር ብረት እንድታስወግዱ፣

የቀንበርን ማሰሪያ እንድትፈቱ፣+

የተጨቆኑትን በነፃ እንድትለቁ፣+

ቀንበርንም ሁሉ እንድትሰብሩ ነው፤

 7 ምግብህን ለተራበው እንድታካፍል፣+

ድሆችንና ቤት የሌላቸውን ወደ ቤትህ እንድታስገባ፣

የተራቆተ ሰው ስታይ እንድታለብስ፣+

ለሥጋ ዘመድህም ጀርባህን እንዳትሰጥ ነው።

 8 በዚህ ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ጮራ ይፈነጥቃል፤+

ፈውስህም ፈጥኖ ይመጣል።

ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፤

የይሖዋም ክብር ደጀን ይሆንልሃል።+

 9 የዚያን ጊዜ ትጣራለህ፤ ይሖዋም ይመልስልሃል፤

እርዳታ ለማግኘት ትጮኻለህ፤ እሱም ‘አለሁልህ!’ ይልሃል።

ከመካከልህ ቀንበሩን ብታስወግድ

እንዲሁም ጣትህን መቀሰርና ተንኮል ያዘለ ንግግር መናገር ብትተው፣+

10 ለተራበው ሰው አንተ ራስህ* የምትፈልገውን ነገር ብታደርግለት፣+

የተጎሳቆሉትንም ብታረካ፣*

ያን ጊዜ ብርሃንህ በጨለማ እንኳ ቦግ ብሎ ይበራል፤

ጨለማህም እንደ ቀትር ብርሃን ይሆናል።+

11 ይሖዋ ምንጊዜም ይመራሃል፤

ደረቅ በሆነ ምድርም እንኳ ፍላጎትህን ያረካል፤*+

አጥንቶችህን ያበረታል፤

አንተም ውኃ እንደሚጠግብ የአትክልት ቦታና

ውኃው እንደማይቋረጥ ምንጭ ትሆናለህ።+

12 ከአንተም የተነሳ የጥንቶቹን ፍርስራሾች መልሰው ይገነባሉ፤+

ያለፉትን ትውልዶች መሠረቶች ታድሳለህ።+

አንተም የፈረሱትን* ግንቦች የሚያድስ፣

በመኖሪያ ቦታዎች አካባቢ የሚገኙ ጎዳናዎችን የሚጠግን ተብለህ ትጠራለህ።+

13 ሰንበትን በማክበር በተቀደሰው ቀኔ የራስህን ጥቅም* ከማሳደድ ብትቆጠብ፣*+

ሰንበትንም ሐሴት፣ የተቀደሰ የይሖዋ ቀንና ሊከበር የሚገባው ቀን ብለህ ብትጠራው+

እንዲሁም የራስህን ጥቅም ከማሳደድና ከንቱ ቃል ከመናገር ይልቅ ብታከብረው፣

14 ያን ጊዜ በይሖዋ ሐሴት ታደርጋለህ፤

ደግሞም በምድር ከፍ ያሉ ቦታዎች ላይ እንድትጋልብ አደርግሃለሁ።+

ከአባትህ ከያዕቆብ ርስት አበላሃለሁ፤*+

የይሖዋ አፍ ተናግሯልና።”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ