ኢሳይያስ
ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፣
ለተማረኩት ነፃነትን እንዳውጅ
እንዲሁም ‘የእስረኞች ዓይን ይከፈታል’ ብዬ እንድናገር ልኮኛል፤+
2 ይሖዋ በጎ ፈቃድ* የሚያሳይበትን ዓመት፣
አምላካችን የሚበቀልበትንም ቀን እንዳውጅ፣+
የሚያለቅሱትንም ሁሉ እንዳጽናና ልኮኛል፤+
3 በጽዮን የተነሳ ላዘኑት
በአመድ ፋንታ የራስ መሸፈኛ፣
በሐዘን ፋንታ የደስታ ዘይት፣
በተደቆሰም መንፈስ ፋንታ የውዳሴ ልብስ እንድሰጥ ልኮኛል።
4 የጥንቶቹን ፍርስራሾች መልሰው ይገነባሉ፤
በቀድሞዎቹ ጊዜያት ባድማ የሆኑትን ቦታዎች ይሠራሉ፤+
የወደሙትን ከተሞች፣
ከትውልድ እስከ ትውልድም ፈራርሰው የቆዩትን ቦታዎች መልሰው ይገነባሉ።+
6 እናንተም የይሖዋ ካህናት ተብላችሁ ትጠራላችሁ፤+
የአምላካችን አገልጋዮች ብለው ይጠሯችኋል።
7 በኀፍረት ፋንታ እጥፍ ድርሻ ይኖራችኋል፤
በውርደትም ፋንታ በሚያገኙት ድርሻ በደስታ እልል ይላሉ።
አዎ፣ በምድራቸው እጥፍ ድርሻ ይወርሳሉ።+
የዘላለም ሐሴት የእነሱ ይሆናል።+
ደሞዛቸውን በታማኝነት እሰጣቸዋለሁ፤
ከእነሱም ጋር ዘላለማዊ ቃል ኪዳን አደርጋለሁ።+
9 ዘሮቻቸው በብሔራት፣
ልጆቻቸውም በሕዝቦች መካከል የታወቁ ይሆናሉ።+
የሚያዩአቸው ሁሉ
ይሖዋ የባረካቸው ዘሮች እንደሆኑ ይገነዘባሉ።”+
10 እኔ በይሖዋ እጅግ ደስ ይለኛል።