የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሕዝቅኤል 14
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሕዝቅኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • ጣዖት አምላኪዎች ተወገዙ (1-11)

      • በኢየሩሳሌም ላይ ከሚወሰደው የፍርድ እርምጃ ማምለጥ አይቻልም (12-23)

        • ጻድቅ የሆኑት ኖኅ፣ ዳንኤልና ኢዮብ (14, 20)

ሕዝቅኤል 14:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 33:30, 31

ሕዝቅኤል 14:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል “ፋንድያ” ከሚለው ቃል ጋር ዝምድና ሊኖረው የሚችል ሲሆን ንቀትን ለማመልከት ተሠርቶበታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 3:13፤ ኢሳ 1:15፤ ኤር 11:11

ሕዝቅኤል 14:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የእስራኤልን ቤት በልባቸው እይዛለሁና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 2:5

ሕዝቅኤል 14:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 55:7

ሕዝቅኤል 14:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 21:1, 2፤ ሕዝ 33:31

ሕዝቅኤል 14:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 20:2, 3

ሕዝቅኤል 14:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 22:21, 22፤ ኤር 4:10፤ 2ተሰ 2:10, 11

ሕዝቅኤል 14:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 24:7፤ ሕዝ 11:19, 20

ሕዝቅኤል 14:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የዳቦ በትሮቹንም እሰብራለሁ።” ዳቦ ለማስቀመጥ የሚያገለግሉ በትሮችን የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:26
  • +ኢሳ 3:1፤ ኤር 15:2
  • +ኤር 7:20

ሕዝቅኤል 14:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሳቸውን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 6:8, 9፤ ዕብ 11:7
  • +ዳን 10:11
  • +ኢዮብ 1:8፤ 42:8
  • +ምሳሌ 11:4፤ ኤር 15:1፤ 2ጴጥ 2:9

ሕዝቅኤል 14:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ልጆች ቢጨርሱና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:22፤ ኤር 15:3

ሕዝቅኤል 14:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:25፤ ኤር 25:9፤ ሕዝ 21:3
  • +ሶፎ 1:3

ሕዝቅኤል 14:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:21, 22

ሕዝቅኤል 14:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሳቸውን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 7:1
  • +ዳን 10:11
  • +ኢዮብ 1:8፤ 42:8
  • +ሕዝ 18:20፤ ሶፎ 2:3

ሕዝቅኤል 14:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አደገኛ የሆኑትን አራት የፍርድ እርምጃዎቼን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 32:43
  • +ኤር 15:2
  • +ሕዝ 5:17፤ 33:27

ሕዝቅኤል 14:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 4:31፤ 2ዜና 36:20፤ ሕዝ 6:8፤ ሚክ 5:7

ሕዝቅኤል 14:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ነህ 9:33፤ ኤር 22:8, 9፤ ሕዝ 9:9፤ ዳን 9:7

ተዛማጅ ሐሳብ

ሕዝ. 14:1ሕዝ 33:30, 31
ሕዝ. 14:32ነገ 3:13፤ ኢሳ 1:15፤ ኤር 11:11
ሕዝ. 14:5ኤር 2:5
ሕዝ. 14:6ኢሳ 55:7
ሕዝ. 14:7ኤር 21:1, 2፤ ሕዝ 33:31
ሕዝ. 14:8ዘሌ 20:2, 3
ሕዝ. 14:91ነገ 22:21, 22፤ ኤር 4:10፤ 2ተሰ 2:10, 11
ሕዝ. 14:11ኤር 24:7፤ ሕዝ 11:19, 20
ሕዝ. 14:13ዘሌ 26:26
ሕዝ. 14:13ኢሳ 3:1፤ ኤር 15:2
ሕዝ. 14:13ኤር 7:20
ሕዝ. 14:14ዘፍ 6:8, 9፤ ዕብ 11:7
ሕዝ. 14:14ዳን 10:11
ሕዝ. 14:14ኢዮብ 1:8፤ 42:8
ሕዝ. 14:14ምሳሌ 11:4፤ ኤር 15:1፤ 2ጴጥ 2:9
ሕዝ. 14:15ዘሌ 26:22፤ ኤር 15:3
ሕዝ. 14:17ዘሌ 26:25፤ ኤር 25:9፤ ሕዝ 21:3
ሕዝ. 14:17ሶፎ 1:3
ሕዝ. 14:19ዘዳ 28:21, 22
ሕዝ. 14:20ዘፍ 7:1
ሕዝ. 14:20ዳን 10:11
ሕዝ. 14:20ኢዮብ 1:8፤ 42:8
ሕዝ. 14:20ሕዝ 18:20፤ ሶፎ 2:3
ሕዝ. 14:21ኤር 32:43
ሕዝ. 14:21ኤር 15:2
ሕዝ. 14:21ሕዝ 5:17፤ 33:27
ሕዝ. 14:22ዘዳ 4:31፤ 2ዜና 36:20፤ ሕዝ 6:8፤ ሚክ 5:7
ሕዝ. 14:23ነህ 9:33፤ ኤር 22:8, 9፤ ሕዝ 9:9፤ ዳን 9:7
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ሕዝቅኤል 14:1-23

ሕዝቅኤል

14 ከእስራኤል ሽማግሌዎች መካከል አንዳንዶቹ ወደ እኔ መጥተው በፊቴ ተቀመጡ።+ 2 ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 3 “የሰው ልጅ ሆይ፣ እነዚህ ሰዎች አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቻቸውን* ለመከተል ቆርጠው ተነስተዋል፤ ሰዎች ኃጢአት እንዲሠሩ የሚያደርግ የማሰናከያ ድንጋይ አስቀምጠዋል። ታዲያ እኔን እንዲጠይቁኝ ልፈቅድላቸው ይገባል?+ 4 እንግዲህ ንገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አንድ እስራኤላዊ አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቹን ለመከተል ቆርጦ ተነስቶና ሰዎች ኃጢአት እንዲሠሩ የሚያደርግ የማሰናከያ ድንጋይ አስቀምጦ አንድን ነቢይ ለመጠየቅ ቢመጣ እኔ ይሖዋ፣ እንደ አስጸያፊ ጣዖቶቹ ብዛት በተገቢው መንገድ እመልስለታለሁ። 5 የእስራኤልን ቤት ሰዎች ልብ አሸብራለሁና፤* ምክንያቱም ሁሉም ከእኔ ርቀዋል፤ እንዲሁም አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቻቸውን ተከትለዋል።”’+

6 “ስለሆነም የእስራኤልን ቤት ሰዎች እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ተመለሱ፤ አስጸያፊ ከሆኑት ጣዖቶቻችሁ ራቁ፤ ቀፋፊ ከሆኑት ልማዶቻችሁ ሁሉ ፊታችሁን መልሱ።+ 7 ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በእስራኤል የሚኖር የባዕድ አገር ሰው ከእኔ በመለየት አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቹን ለመከተል ቆርጦ ተነስቶና ሰዎች ኃጢአት እንዲሠሩ የሚያደርግ የማሰናከያ ድንጋይ አስቀምጦ የእኔን ነቢይ ለመጠየቅ ቢመጣ+ እኔ ይሖዋ፣ አዎ እኔ ራሴ እመልስለታለሁ። 8 ፊቴን ወደዚህ ሰው አዞራለሁ፤ መቀጣጫና መተረቻ አደርገዋለሁ፤ ከሕዝቤም መካከል አስወግደዋለሁ፤+ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።”’

9 “‘ይሁንና ነቢዩ ቢሞኝና ምላሽ ቢሰጥ፣ ያንን ነቢይ ያሞኘሁት እኔ ይሖዋ ነኝ።+ ከዚያም እጄን በእሱ ላይ ዘርግቼ ከሕዝቤ ከእስራኤል መካከል አጠፋዋለሁ። 10 የፈጸሙት በደል የሚያስከትልባቸውን መዘዝ ይሸከማሉ፤ ነቢዩን ሊጠይቅ የመጣው ሰው በደል ነቢዩ ከፈጸመው በደል ጋር አንድ ዓይነት ይሆናል፤ 11 ይህም የሚሆነው የእስራኤል ቤት ሰዎች ከእኔ ርቀው እንዳይባዝኑና በሚፈጽሙት በደል ሁሉ ራሳቸውን ከማርከስ እንዲቆጠቡ ነው። እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”

12 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 13 “የሰው ልጅ ሆይ፣ አንድ አገር ታማኝ ሳይሆን ቀርቶ በእኔ ላይ ኃጢአት ቢፈጽም እጄን በእሱ ላይ እዘረጋለሁ፤ የምግብ አቅርቦቱም እንዲቋረጥ አደርጋለሁ፤*+ ረሃብም እሰድበታለሁ+ እንዲሁም ሰውንም ሆነ እንስሳን ከዚያ አጠፋለሁ።”+ 14 “‘እነዚህ ሦስት ሰዎች ይኸውም ኖኅ፣+ ዳንኤልና+ ኢዮብ+ በዚያ ቢኖሩ እንኳ በጽድቃቸው የሚያድኑት ራሳቸውን* ብቻ ነው’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”

15 “‘ወይም አደገኛ የዱር አራዊትን ወደዚያ አገር ብሰድ፣ በአገሩ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ቢፈጁና* አገሩ በዱር አራዊቱ የተነሳ ማንም ሰው የማያልፍበት ወና እንዲሆን ቢያደርጉ፣+ 16 በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘እነዚህ ሦስት ሰዎች በዚያ ቢኖሩ እንኳ ወንዶችንም ሆነ ሴቶች ልጆቻቸውን ማዳን አይችሉም፤ የሚያድኑት ራሳቸውን ብቻ ነው፤ አገሩም ባድማ ይሆናል።’”

17 “‘ወይም ደግሞ በአገሩ ላይ ሰይፍ ባመጣና+ “በአገሩ መካከል ሰይፍ ይለፍ” ብል፣ በአገሩም ላይ ያለውን ሰውም ሆነ እንስሳ ባጠፋ፣+ 18 እነዚህ ሦስት ሰዎች በዚያ ቢኖሩ እንኳ፣ በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ወንዶችንም ሆነ ሴቶች ልጆቻቸውን ማዳን አይችሉም፤ የሚያድኑት ራሳቸውን ብቻ ነው።’”

19 “‘ወይም በአገሩ ላይ ቸነፈር ብሰድና+ ሰውንም ሆነ እንስሳን ለማጥፋት ደም በማፍሰስ በአገሩ ላይ ቁጣዬን ባወርድ፣ 20 ኖኅ፣+ ዳንኤልና+ ኢዮብ+ በዚያ ቢኖሩ እንኳ፣ በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ወንዶችንም ሆነ ሴቶች ልጆቻቸውን ማዳን አይችሉም፤ በጽድቃቸው የሚያድኑት ራሳቸውን* ብቻ ነው።’”+

21 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሰውንም ሆነ እንስሳን ለማጥፋት+ በኢየሩሳሌም ላይ አራት ቅጣቶቼን*+ ይኸውም ሰይፍን፣ ረሃብን፣ አደገኛ የዱር አራዊትንና ቸነፈርን በምሰድበት ጊዜ+ ምንኛ የከፋ ይሆን! 22 ሆኖም በዚያ የሚቀሩ አንዳንድ ወንዶችና ሴቶች ልጆች በሕይወት ይተርፋሉ፤ ደግሞም ከዚያ ይወሰዳሉ።+ ወደ እናንተ ይመጣሉ፤ መንገዳቸውንና ሥራቸውንም በምታዩበት ጊዜ በኢየሩሳሌም ላይ ካመጣሁት ጥፋት፣ በእሷም ላይ ካደረስኩት ነገር ሁሉ በእርግጥ ትጽናናላችሁ።’”

23 “‘መንገዳቸውንና ሥራቸውን ስታዩ ያጽናኗችኋል፤ በእሷም ላይ ላደርገው የሚገባኝን ነገር ያደረግኩት ያለምክንያት አለመሆኑን ትገነዘባላችሁ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ