የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሕዝቅኤል 8
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሕዝቅኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • ሕዝቅኤል በራእይ ወደ ኢየሩሳሌም ተወሰደ (1-4)

      • በቤተ መቅደሱ ውስጥ አስጸያፊ ነገሮች ታዩ (5-18)

        • ሴቶች ለታሙዝ አለቀሱ (14)

        • ወንዶች ፀሐይን አመለኩ (16)

ሕዝቅኤል 8:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የሚያብረቀርቅ የወርቅና የብር ቅይጥ።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዳን 7:9
  • +ሕዝ 1:4, 27

ሕዝቅኤል 8:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ምስል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 32:16
  • +ኤር 20:2፤ ሕዝ 9:2

ሕዝቅኤል 8:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 40:34፤ ሕዝ 1:27, 28

ሕዝቅኤል 8:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ምስል።”

ሕዝቅኤል 8:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 26:4, 6
  • +2ዜና 36:14

ሕዝቅኤል 8:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል “ፋንድያ” ከሚለው ቃል ጋር ዝምድና ሊኖረው የሚችል ሲሆን ንቀትን ለማመልከት ተሠርቶበታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 11:10
  • +ዘፀ 20:4, 5

ሕዝቅኤል 8:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 22:3, 4፤ 25:22፤ ኤር 26:24
  • +ሕዝ 16:17, 18

ሕዝቅኤል 8:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የተቀረጹ ምስሎቻቸው በሚገኙባቸው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 29:15፤ ሕዝ 9:9

ሕዝቅኤል 8:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 36:14

ሕዝቅኤል 8:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 4:9
  • +ዘዳ 4:19፤ 2ነገ 17:16፤ ኤር 8:1, 2

ሕዝቅኤል 8:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ለጣዖት አምልኮ ይጠቀሙበት የነበረ ቅርንጫፍ እንደሆነ ይታመናል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 21:16፤ ኤር 19:4፤ ሕዝ 9:9

ሕዝቅኤል 8:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 5:11፤ 7:9
  • +ኢሳ 1:15፤ ሚክ 3:4

ተዛማጅ ሐሳብ

ሕዝ. 8:2ዳን 7:9
ሕዝ. 8:2ሕዝ 1:4, 27
ሕዝ. 8:3ዘዳ 32:16
ሕዝ. 8:3ኤር 20:2፤ ሕዝ 9:2
ሕዝ. 8:4ዘፀ 40:34፤ ሕዝ 1:27, 28
ሕዝ. 8:6ኤር 26:4, 6
ሕዝ. 8:62ዜና 36:14
ሕዝ. 8:10ዘሌ 11:10
ሕዝ. 8:10ዘፀ 20:4, 5
ሕዝ. 8:112ነገ 22:3, 4፤ 25:22፤ ኤር 26:24
ሕዝ. 8:11ሕዝ 16:17, 18
ሕዝ. 8:12ኢሳ 29:15፤ ሕዝ 9:9
ሕዝ. 8:152ዜና 36:14
ሕዝ. 8:162ዜና 4:9
ሕዝ. 8:16ዘዳ 4:19፤ 2ነገ 17:16፤ ኤር 8:1, 2
ሕዝ. 8:172ነገ 21:16፤ ኤር 19:4፤ ሕዝ 9:9
ሕዝ. 8:18ሕዝ 5:11፤ 7:9
ሕዝ. 8:18ኢሳ 1:15፤ ሚክ 3:4
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ሕዝቅኤል 8:1-18

ሕዝቅኤል

8 በስድስተኛውም ዓመት፣ በስድስተኛው ወር፣ ከወሩም በአምስተኛው ቀን በቤቴ ተቀምጬ ሳለሁ፣ የይሁዳም ሽማግሌዎች በፊቴ ተቀምጠው ሳሉ በዚያ የሉዓላዊው ጌታ የይሖዋ እጅ ያዘኝ። 2 እነሆም እሳት የሚመስል ነገር ተመለከትኩ፤ ወገቡ ከሚመስለው ነገር በታች እሳት ነበር፤+ ደግሞም ከወገቡ በላይ መልኩ እንደሚያብረቀርቅ ብረት* ደማቅ ነበር።+ 3 ከዚያም እጅ የሚመስል ነገር ዘርግቶ የራስ ፀጉሬን ያዘ፤ መንፈስም በምድርና በሰማይ መካከል ይዞ ወሰደኝ፤ አምላክ በገለጠልኝ ራእዮች አማካኝነት ወደ ኢየሩሳሌም ይኸውም ቅናት የሚቀሰቅሰው የቅናት ጣዖት ምልክት* ወደቆመበት+ በሰሜን ትይዩ ወደሚገኘው ወደ ውስጠኛው ግቢ በር+ አመጣኝ። 4 እነሆም፣ በሸለቋማው ሜዳ አይቼው የነበረውን የሚመስል የእስራኤል አምላክ ክብር በዚያ ነበር።+

5 ከዚያም “የሰው ልጅ ሆይ፣ እባክህ ዓይንህን አንስተህ ወደ ሰሜን ተመልከት” አለኝ። ስለዚህ ወደ ሰሜን ተመለከትኩ፤ በዚያም ከመሠዊያው በር በስተ ሰሜን በኩል መግቢያው ላይ ይህ የቅናት ምልክት* ነበር። 6 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ የእስራኤል ቤት ሰዎች በዚህ ቦታ የሚሠሯቸውን ከመቅደሴ እንድርቅ የሚያደርጉ ነገሮች+ ይኸውም የሚፈጽሟቸውን አስከፊና አስጸያፊ ነገሮች ትመለከታለህ?+ ይበልጥ አስከፊ የሆኑ አስጸያፊ ነገሮችን ገና ታያለህ።”

7 ከዚያም ወደ ቅጥር ግቢው መግቢያ አመጣኝ፤ እኔም ስመለከት በግድግዳው ላይ አንድ ቀዳዳ አየሁ። 8 እሱም “የሰው ልጅ ሆይ፣ እስቲ ግድግዳውን ንደለው” አለኝ። እኔም ግድግዳውን ነደልኩት፤ አንድ መግቢያም ተመለከትኩ። 9 እሱም “ወደ ውስጥ ግባና በዚህ ቦታ የሚሠሯቸውን ክፉና አስጸያፊ ነገሮች ተመልከት” አለኝ። 10 እኔም ገብቼ አየሁ፤ መሬት ለመሬት የሚሳቡ ፍጥረታትንና የሚያስጠሉ አራዊትን+ ሁሉ እንዲሁም አስጸያፊ የሆኑ የእስራኤል ቤት ጣዖቶችን* ሁሉ ምስል+ ተመለከትኩ፤ ምስላቸውም በግድግዳው ዙሪያ ተቀርጾ ነበር። 11 ደግሞም 70 የሚሆኑ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች በምስሎቹ ፊት ቆመው ነበር፤ የሳፋን+ ልጅ ያአዛንያህ በመካከላቸው ቆሞ ነበር። እያንዳንዳቸውም በእጃቸው ጥና የያዙ ሲሆን መልካም መዓዛ ያለው የዕጣን ጭስም እየተትጎለጎለ ይወጣ ነበር።+ 12 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች እያንዳንዳቸው ጣዖቶቻቸው ባሉባቸው* እልፍኞች ውስጥ በጨለማ ምን እንደሚያደርጉ ታያለህ? እነሱ ‘ይሖዋ አያየንም። ይሖዋ ምድሪቱን ትቷታል’ ይላሉና።”+

13 ደግሞም “እነሱ የሚሠሯቸውን ይበልጥ አስከፊ የሆኑ አስጸያፊ ነገሮች ታያለህ” አለኝ። 14 በመሆኑም በሰሜን በኩል ወዳለው ወደ ይሖዋ ቤት በር መግቢያ አመጣኝ፤ በዚያም ሴቶች ተቀምጠው ታሙዝ ለተባለው አምላክ ሲያለቅሱ አየሁ።

15 እሱም በመቀጠል “የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህን ታያለህ? ከእነዚህ የባሰ አስከፊ የሆኑ አስጸያፊ ነገሮች ታያለህ” አለኝ።+ 16 በመሆኑም ወደ ይሖዋ ቤት ውስጠኛው ግቢ+ አመጣኝ። በዚያም በይሖዋ ቤተ መቅደስ መግቢያ ላይ በበረንዳውና በመሠዊያው መካከል 25 ያህል ወንዶች ነበሩ፤ እነሱም ጀርባቸውን ለይሖዋ ቤተ መቅደስ ሰጥተው ፊታቸውን ወደ ምሥራቅ አዙረው ነበር፤ ደግሞም በምሥራቅ አቅጣጫ ለፀሐይ ይሰግዱ ነበር።+

17 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህን ታያለህ? የይሁዳ ቤት እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች መፈጸማቸው፣ ምድሪቱን በዓመፅ መሙላታቸውና+ እኔን ማስቆጣታቸው ቀላል ነገር ነው? እነሆ፣ ቅርንጫፉን* ወደ አፍንጫዬ አቅርበዋል። 18 በመሆኑም በቁጣ እርምጃ እወስዳለሁ። ዓይኔ አያዝንም፤ ደግሞም አልራራም።+ በታላቅ ድምፅ ወደ ጆሮዬ ቢጮኹም አልሰማቸውም።”+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ