የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዳንኤል 10
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዳንኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • ከአምላክ የተላከ መልእክተኛ ወደ ዳንኤል መጣ (1-21)

        • ሚካኤል መልአኩን ረዳው (13)

ዳንኤል 10:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕዝራ 1:1, 2፤ ኢሳ 45:1፤ ዳን 1:21፤ 6:28
  • +ዳን 1:7፤ 4:8

ዳንኤል 10:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዳን 9:3

ዳንኤል 10:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በሂዲኬል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 2:14

ዳንኤል 10:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ራእይ 19:14

ዳንኤል 10:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 1:16
  • +ሕዝ 1:5, 7

ዳንኤል 10:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 6:17፤ ሥራ 9:7

ዳንኤል 10:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዳን 7:28፤ 8:27

ዳንኤል 10:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዳን 8:18

ዳንኤል 10:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 1:9፤ ራእይ 1:17

ዳንኤል 10:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ትልቅ ግምት የሚሰጥህ፤ እጅግ የተከበርክ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዳን 9:23፤ 10:19

ዳንኤል 10:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ራእይ 1:17
  • +ዳን 9:23

ዳንኤል 10:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የመጀመሪያውን ደረጃ ከያዙት አለቆች።”

  • *

    “እንደ አምላክ ያለ ማን ነው?” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤፌ 6:12
  • +ዳን 10:21፤ 12:1፤ ይሁዳ 9፤ ራእይ 12:7, 8

ዳንኤል 10:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዳን 8:17, 26፤ 12:4
  • +ዳን 2:28

ዳንኤል 10:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 6:7፤ ኤር 1:9
  • +ዳን 10:8

ዳንኤል 10:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 6:22
  • +ኢሳ 6:5

ዳንኤል 10:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዳን 10:10

ዳንኤል 10:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ትልቅ ግምት የሚሰጥህ፤ እጅግ የተከበርክ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዳን 9:22, 23፤ 10:11
  • +ራእይ 1:17
  • +መሳ 6:23

ዳንኤል 10:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዳን 10:13

ዳንኤል 10:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዳን 12:1
  • +ዳን 10:13፤ ይሁዳ 9፤ ራእይ 12:7, 8

ተዛማጅ ሐሳብ

ዳን. 10:1ዕዝራ 1:1, 2፤ ኢሳ 45:1፤ ዳን 1:21፤ 6:28
ዳን. 10:1ዳን 1:7፤ 4:8
ዳን. 10:2ዳን 9:3
ዳን. 10:4ዘፍ 2:14
ዳን. 10:5ራእይ 19:14
ዳን. 10:6ሕዝ 1:16
ዳን. 10:6ሕዝ 1:5, 7
ዳን. 10:72ነገ 6:17፤ ሥራ 9:7
ዳን. 10:8ዳን 7:28፤ 8:27
ዳን. 10:9ዳን 8:18
ዳን. 10:10ኤር 1:9፤ ራእይ 1:17
ዳን. 10:11ዳን 9:23፤ 10:19
ዳን. 10:12ራእይ 1:17
ዳን. 10:12ዳን 9:23
ዳን. 10:13ኤፌ 6:12
ዳን. 10:13ዳን 10:21፤ 12:1፤ ይሁዳ 9፤ ራእይ 12:7, 8
ዳን. 10:14ዳን 8:17, 26፤ 12:4
ዳን. 10:14ዳን 2:28
ዳን. 10:16ኢሳ 6:7፤ ኤር 1:9
ዳን. 10:16ዳን 10:8
ዳን. 10:17መሳ 6:22
ዳን. 10:17ኢሳ 6:5
ዳን. 10:18ዳን 10:10
ዳን. 10:19ዳን 9:22, 23፤ 10:11
ዳን. 10:19ራእይ 1:17
ዳን. 10:19መሳ 6:23
ዳን. 10:20ዳን 10:13
ዳን. 10:21ዳን 12:1
ዳን. 10:21ዳን 10:13፤ ይሁዳ 9፤ ራእይ 12:7, 8
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዳንኤል 10:1-21

ዳንኤል

10 የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ+ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት ብልጣሶር ተብሎ የተጠራው ዳንኤል+ አንድ ራእይ ተሰጠው፤ ይህም መልእክት እውነት ነው፤ መልእክቱም ስለ አንድ ታላቅ ውጊያ ይገልጻል። እሱም መልእክቱን ተረድቶት ነበር፤ ያየውንም ነገር ማስተዋል ችሎ ነበር።

2 በዚያን ጊዜ እኔ ዳንኤል ሦስት ሳምንት ሙሉ በሐዘን ላይ ነበርኩ።+ 3 ሦስቱ ሳምንታት እስኪያበቁ ድረስ ምርጥ ምግብ አልበላሁም፤ ሥጋም ሆነ የወይን ጠጅ አልቀመስኩም እንዲሁም ሰውነቴን ቅባት አልተቀባሁም። 4 በመጀመሪያው ወር በ24ኛው ቀን በታላቁ ወንዝ ይኸውም በጤግሮስ*+ ዳርቻ ሳለሁ፣ 5 ቀና ብዬ ስመለከት በፍታ የለበሰና+ ወገቡ ላይ በዑፋዝ ወርቅ የተሠራ ቀበቶ የታጠቀ አንድ ሰው አየሁ። 6 ሰውነቱ እንደ ክርስቲሎቤ፣+ ፊቱ እንደ መብረቅ፣ ዓይኖቹ እንደሚንቦገቦግ ችቦ፣ ክንዶቹና እግሮቹ እንደሚያብረቀርቅ መዳብ፣+ ድምፁም እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበር። 7 ራእዩን ያየሁት እኔ ዳንኤል ብቻ ነበርኩ፤ ከእኔ ጋር የነበሩት ሰዎች ግን ራእዩን አላዩም።+ ነገር ግን እጅግ ስለተሸበሩ ሸሽተው ተደበቁ።

8 እኔም ብቻዬን ቀረሁ፤ ይህን ታላቅ ራእይ በተመለከትኩ ጊዜም በውስጤ ምንም ኃይል አልቀረም፤ ግርማ ሞገስ የተላበሰው ቁመናዬ ተለወጠ፤ ኃይሌም በሙሉ ተሟጠጠ።+  9 ከዚያም ሲናገር ድምፁን ሰማሁ፤ ሆኖም ሲናገር እየሰማሁት ሳለ በግንባሬ መሬት ላይ ተደፍቼ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰደኝ።+ 10 በዚህ ጊዜ አንድ እጅ ዳሰሰኝ፤+ ከቀሰቀሰኝ በኋላ በእጄና በጉልበቴ ተደግፌ እንድነሳ አደረገኝ። 11 ከዚያም እንዲህ አለኝ፦

“እጅግ የተወደድክ*+ ዳንኤል ሆይ፣ የምነግርህን ቃል አስተውል። በነበርክበት ቦታ ላይ ቁም፤ ወደ አንተ ተልኬ መጥቼአለሁና።”

ይህን ሲለኝ እየተንቀጠቀጥኩ ቆምኩ።

12 ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “ዳንኤል ሆይ፣ አትፍራ።+ እነዚህን ነገሮች ለመረዳት ልባዊ ጥረት ማድረግና በአምላክህ ፊት ራስህን ዝቅ ማድረግ ከጀመርክበት ቀን አንስቶ ቃልህ ተሰምቷል፤ እኔም የመጣሁት ከቃልህ የተነሳ ነው።+ 13 ሆኖም የፋርስ ንጉሣዊ ግዛት አለቃ+ ለ21 ቀናት ተቋቋመኝ። በኋላ ግን ከዋነኞቹ አለቆች* አንዱ የሆነው ሚካኤል*+ ሊረዳኝ መጣ፤ እኔም በዚያን ጊዜ ከፋርስ ነገሥታት ጋር በዚያ ቆየሁ። 14 ራእዩ ከብዙ ዘመን በኋላ የሚፈጸም ስለሆነ+ በዘመኑ መጨረሻ በሕዝብህ ላይ የሚደርሰውን ነገር አስረዳህ ዘንድ መጥቻለሁ።”+

15 ይህን ቃል በነገረኝ ጊዜ ወደ መሬት አቀረቀርኩ፤ መናገርም ተሳነኝ። 16 በዚህ ጊዜ የሰው ልጅ የሚመስል ከንፈሮቼን ዳሰሰ፤+ እኔም አፌን ከፍቼ በፊቴ ቆሞ የነበረውን እንዲህ አልኩት፦ “ጌታዬ ሆይ፣ ከራእዩ የተነሳ እየተንቀጠቀጥኩ ነው፤ ኃይሌም ተሟጥጧል።+ 17 ስለዚህ የጌታዬ አገልጋይ ከጌታዬ ጋር እንዴት መነጋገር ይችላል?+ አሁን ምንም ኃይል የለኝምና፤ በውስጤም የቀረ እስትንፋስ የለም።”+

18 ሰው የሚመስለው እንደገና ዳሰሰኝ፤ አበረታኝም።+ 19 ከዚያም “አንተ እጅግ የተወደድክ* ሰው+ ሆይ፣ አትፍራ።+ ሰላም ለአንተ ይሁን።+ በርታ፣ አይዞህ በርታ” አለኝ። እንዲህ ባለኝ ጊዜ ተበረታትቼ “ጌታዬ ሆይ፣ ብርታት ሰጥተኸኛልና ተናገር” አልኩት።

20 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “ወደ አንተ የመጣሁት ለምን እንደሆነ ታውቃለህ? አሁን ከፋርስ አለቃ ጋር ለመዋጋት ተመልሼ እሄዳለሁ።+ እኔ ስሄድ የግሪክ አለቃ ይመጣል። 21 ሆኖም በእውነት መጽሐፍ ላይ የሠፈሩትን ነገሮች እነግርሃለሁ። ከእነዚህ ነገሮች ጋር በተያያዘ የሕዝብህ አለቃ+ ከሆነው ከሚካኤል+ በስተቀር በእጅጉ ሊረዳኝ የሚችል የለም።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ