ሆሴዕ
9 “እስራኤል ሆይ፣ ሐሴት አታድርግ፤+
እንደ ሌሎቹ ሕዝቦች ደስ አይበልህ።
በየእህል አውድማ ላይ ለዝሙት አዳሪ የሚከፈለውን ደሞዝ ወደኸዋል።+
2 ሆኖም የእህል አውድማውና የወይን መጭመቂያው አይመግባቸውም፤
አዲሱም የወይን ጠጅ ይቋረጥባቸዋል።+
እንደ እዝን እንጀራ ናቸው፤
የሚበሉትም ሁሉ ራሳቸውን ያረክሳሉ።
ምግባቸው ለራሳቸው ብቻ* ነውና፤
ወደ ይሖዋ ቤት አይገባም።
5 የምትሰበሰቡበትና* ለይሖዋ በዓል የምታከብሩበት ቀን ሲደርስ
ምን ታደርጉ ይሆን?
6 እነሆ፣ ምድሪቱ በመውደሟ ለመሸሽ ይገደዳሉ።+
ግብፅ ትሰበስባቸዋለች፤+ ሜምፊስ ደግሞ ትቀብራቸዋለች።+
ከብር የተሠሩ ውድ ንብረቶቻቸውን ሳማ ይወርሰዋል፤
በድንኳኖቻቸውም ውስጥ እሾሃማ ቁጥቋጦ ይበቅላል።
የእነሱ ነቢይ ሞኝ፣ በመንፈስ የሚናገረውም ሰው እንደ እብድ ይሆናል፤
ምክንያቱም በደልህ ብዙ ነው፤ በአንተም ላይ የሚደርሰው ጥላቻ በዝቷል።”
አሁን ግን የነቢያቱ+ መንገዶች ሁሉ እንደ ወፍ አዳኝ ወጥመዶች ናቸው፤
በአምላኩ ቤት ጠላትነት አለ።
9 በጊብዓ ዘመን እንደነበረው፣ ጥፋት በሚያስከትሉ ነገሮች ተዘፍቀዋል።+
እሱ በደላቸውን ያስባል፤ በሠሩትም ኃጢአት የተነሳ ይቀጣቸዋል።+
10 “እስራኤልን በምድረ በዳ እንዳለ ወይን ሆኖ አገኘሁት።+
አባቶቻችሁን ለመጀመሪያ ጊዜ ባፈራ የበለስ ዛፍ ላይ እንደ ጎመራ የበለስ ፍሬ ሆነው አየኋቸው።
11 የኤፍሬም ክብር እንደ ወፍ በሮ ይጠፋል፤
መውለድ፣ ማርገዝም ሆነ መፀነስ የለም።+
13 በግጦሽ ስፍራ የተተከለው ኤፍሬም ለእኔ እንደ ጢሮስ ነበር፤+
አሁን ግን ኤፍሬም ልጆቹን ለእርድ አሳልፎ ይሰጣል።”
14 ይሖዋ ሆይ፣ ልትሰጣቸው የሚገባውን ስጣቸው፤
የሚጨነግፍ ማህፀንና የደረቁ* ጡቶች ስጣቸው።
15 “ክፉ ድርጊታቸውን ሁሉ በጊልጋል ፈጸሙ፤+ እኔም በዚያ ጠላኋቸው።
በሠሩት ክፉ ድርጊት የተነሳ ከቤቴ አባርራቸዋለሁ።+
ከእንግዲህ ወዲያ ፍቅሬን እነፍጋቸዋለሁ፤+
አለቆቻቸው ሁሉ እልኸኞች ናቸው።
16 ኤፍሬም ጉዳት ይደርስበታል።+
ሥራቸው ይደርቃል፤ አንዳችም ፍሬ አያፈሩም።
ቢወልዱ እንኳ የሚወዷቸውን ልጆቻቸውን እገድላለሁ።”