አሞጽ
3 “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ ይሖዋ ስለ እናንተ ይኸውም ከግብፅ ምድር ስላወጣሁት ስለ መላው ብሔር የተናገረውን ይህን ቃል ስሙ፦
2 ‘በምድር ላይ ካሉ ብሔራት ሁሉ እኔ የማውቀው እናንተን ብቻ ነው።+
ስለዚህ ለፈጸማችሁት በደል ሁሉ ተጠያቂ አደርጋችኋለሁ።+
3 ሁለት ሰዎች ለመገናኘት ሳይስማሙ* አብረው ይጓዛሉ?
4 አንበሳ አድኖ ሳይዝ በጫካ ውስጥ ያገሳል?
ደቦል አንበሳስ ምንም ነገር ሳይዝ በዋሻው ውስጥ ሆኖ ያጉረመርማል?
5 ወጥመድ ሳይዘጋጅ* ወፍ መሬት ላይ ይጠመዳል?
ወጥመድስ ምንም ነገር ሳይዝ ይፈነጠራል?
6 በከተማ ውስጥ ቀንደ መለከት ቢነፋ ሕዝቡ አይሸበርም?
በከተማው ውስጥ ጥፋት ቢከሰት ይህን ያደረገው ይሖዋ አይደለም?
8 አንበሳ አገሳ!+ የማይፈራ ማን ነው?
ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ተናገረ! ትንቢት የማይናገር ማን ነው?’+
9 ‘በአሽዶድ በሚገኙ የማይደፈሩ ማማዎች
ደግሞም በግብፅ ምድር በሚገኙ የማይደፈሩ ማማዎች ላይ አውጁት።
10 በማይደፈሩ ማማዎቻቸው ውስጥ ዓመፅንና ጥፋትን የሚያከማቹ ሰዎች
ትክክል የሆነውን ነገር ማድረግ አያውቁምና” ይላል ይሖዋ።’
12 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
‘እረኛ ከአንበሳ አፍ ሁለት ቅልጥም ወይም የጆሮ ቁራጭ ነጥቆ እንደሚወስድ ሁሉ
በሰማርያ ባማረ አልጋና ምርጥ በሆነ ድንክ አልጋ* የሚቀመጡ
የእስራኤል ሰዎችም ተነጥቀው ይወሰዳሉ።’+
13 ‘ስሙ፤ የያዕቆብንም ቤት አስጠንቅቁ’* ይላል የሠራዊት አምላክ የሆነው ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
14 ‘እስራኤልን ለፈጸመው የዓመፅ ድርጊት* ሁሉ ተጠያቂ በማደርገው ቀን+
የቤቴልንም መሠዊያዎች ተጠያቂ አደርጋለሁና፤+
የመሠዊያው ቀንዶች ተቆርጠው ወደ ምድር ይወድቃሉ።+
15 የክረምቱን ቤትና የበጋውን ቤት አፈርሳለሁ።’