አሞጽ
8 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ይህን አሳየኝ፦ እነሆ፣ የበጋ ፍሬ* የያዘ ቅርጫት ነበር። 2 ከዚያም “አሞጽ፣ ምን ይታይሃል?” አለኝ። እኔም “የበጋ ፍሬ የያዘ ቅርጫት” ብዬ መለስኩ። ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “የሕዝቤ የእስራኤል ፍጻሜ ደርሷል። ከእንግዲህ ወዲህ ይቅር አልላቸውም።+ 3 ‘በዚያን ቀን የቤተ መቅደሱ መዝሙሮች ወደ ዋይታ ይቀየራሉ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘በየቦታው የተጣሉ ብዙ አስከሬኖች ይኖራሉ፤+ ዝምታ ይስፈን!’
4 እናንተ ድሆችን የምትረጋግጡ፣
በምድሪቱ ላይ ያሉትንም የዋሆች የምታጠፉ ይህን ስሙ፤+
5 እንዲህም ትላላችሁ፦ ‘እህላችንን መሸጥ እንድንችል የወር መባቻው የሚያልፈው መቼ ነው?+
አዝመራችንንስ መሸጥ እንድንችል ሰንበት+ የሚያልፈው መቼ ነው?
ያን ጊዜ በሐሰተኛ ሚዛን ለማጭበርበር
የኢፍ* መስፈሪያውን ማሳነስ፣
6 ደግሞም ችግረኛውን በብር፣
ድሃውንም በጥንድ ጫማ ዋጋ እንገዛለን፤+
መናኛውንም እህል መሸጥ እንችላለን።’
ምድሪቱ በሙሉ እንደ አባይ ወደ ላይ አትነሳም?
በግብፅ እንዳለውም የአባይ ወንዝ ወደ ላይ ከወጣች በኋላ ተመልሳ ወደ ታች አትወርድም?’+
ወገብን ሁሉ ማቅ አስታጥቃለሁ፤ ራስንም ሁሉ እመልጣለሁ፤
ለአንድያ ልጅ እንደሚለቀስ ያለቅሳሉ፤
ፍጻሜውም እንደ መራራ ቀን ይሆናል።’
11 ‘እነሆ፣ በምድሪቱ ላይ ረሃብ የምሰድበት ጊዜ ይመጣል’
ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፤
‘ረሃቡ የይሖዋን ቃል የመስማት ረሃብ እንጂ
ምግብን የመራብ ወይም ውኃን የመጠማት አይደለም።+
12 እነሱ ከባሕር ወደ ባሕር፣
ከሰሜንም ወደ ምሥራቅ* ይባዝናሉ።
የይሖዋን ቃል ፍለጋ በየቦታው ይንከራተታሉ፤ ሆኖም አያገኙትም።
13 በዚያ ቀን፣ ውብ የሆኑት ደናግልና
ወጣት ወንዶች ከውኃ ጥም የተነሳ ራሳቸውን ይስታሉ፤
14 በሰማርያ በደል+ የሚምሉ
ደግሞም “ዳን ሆይ፣ ሕያው በሆነው በአምላክህ እምላለሁ!”+
እንዲሁም “ሕያው በሆነው በቤርሳቤህ መንገድ+ እምላለሁ!” የሚሉ ሰዎች፣
ይወድቃሉ፤ ዳግመኛም አይነሱም።’”+