የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘካርያስ 7
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘካርያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ይሖዋ ልባዊ ያልሆነን ጾም ያወግዛል (1-14)

        • “ትጾሙ የነበረው በእርግጥ ለእኔ ነበር?” (5)

        • ‘አንዳችሁ ለሌላው ፍትሕ፣ ታማኝ ፍቅርና ምሕረት አሳዩ’ (9)

ዘካርያስ 7:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ15ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕዝራ 6:14፤ ዘካ 1:1

ዘካርያስ 7:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መቅደስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 25:8-10፤ ኤር 52:12-14

ዘካርያስ 7:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 25:11፤ ዘካ 1:12
  • +ኤር 41:1, 2

ዘካርያስ 7:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 36:15

ዘካርያስ 7:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 21:3፤ ኤር 21:12
  • +ምሳሌ 16:6፤ ሆሴዕ 10:12፤ ሚክ 6:8

ዘካርያስ 7:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ወላጅ አልባ የሆነውን ልጅ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 22:22፤ ዘዳ 24:17፤ ኢሳ 1:17
  • +ዘፀ 23:9፤ ሚል 3:5
  • +ምሳሌ 22:22
  • +ዘካ 8:17

ዘካርያስ 7:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 33:10፤ ኤር 6:10
  • +ነህ 9:29
  • +2ነገ 17:13, 14፤ ኢሳ 6:10፤ ኤር 25:7

ዘካርያስ 7:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “እንደ ጠንካራ ድንጋይ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

  • *

    ወይም “መመሪያና፤ ትምህርትና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 3:7
  • +ነህ 9:30፤ ሥራ 7:51
  • +2ዜና 36:15, 16፤ ኤር 21:5

ዘካርያስ 7:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 50:2
  • +ኢሳ 1:15፤ ሰቆ 3:44

ዘካርያስ 7:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:64፤ ኤር 5:15
  • +ዘሌ 26:22, 33፤ 2ዜና 36:20, 21

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘካ. 7:1ዕዝራ 6:14፤ ዘካ 1:1
ዘካ. 7:32ነገ 25:8-10፤ ኤር 52:12-14
ዘካ. 7:5ኤር 25:11፤ ዘካ 1:12
ዘካ. 7:5ኤር 41:1, 2
ዘካ. 7:72ዜና 36:15
ዘካ. 7:9ምሳሌ 21:3፤ ኤር 21:12
ዘካ. 7:9ምሳሌ 16:6፤ ሆሴዕ 10:12፤ ሚክ 6:8
ዘካ. 7:10ዘፀ 22:22፤ ዘዳ 24:17፤ ኢሳ 1:17
ዘካ. 7:10ዘፀ 23:9፤ ሚል 3:5
ዘካ. 7:10ምሳሌ 22:22
ዘካ. 7:10ዘካ 8:17
ዘካ. 7:112ዜና 33:10፤ ኤር 6:10
ዘካ. 7:11ነህ 9:29
ዘካ. 7:112ነገ 17:13, 14፤ ኢሳ 6:10፤ ኤር 25:7
ዘካ. 7:12ሕዝ 3:7
ዘካ. 7:12ነህ 9:30፤ ሥራ 7:51
ዘካ. 7:122ዜና 36:15, 16፤ ኤር 21:5
ዘካ. 7:13ኢሳ 50:2
ዘካ. 7:13ኢሳ 1:15፤ ሰቆ 3:44
ዘካ. 7:14ዘዳ 28:64፤ ኤር 5:15
ዘካ. 7:14ዘሌ 26:22, 33፤ 2ዜና 36:20, 21
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘካርያስ 7:1-14

ዘካርያስ

7 ንጉሥ ዳርዮስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣ ኪስሌው* በተባለው በዘጠነኛው ወር፣ ከወሩም በአራተኛው ቀን የይሖዋ ቃል ወደ ዘካርያስ መጣ።+ 2 የቤቴል ሰዎች ይሖዋ ሞገስ እንዲያሳያቸው ለመለመን ሳሬጸርንና ረጌምሜሌክን ከሰዎቹ ጋር ላኩ፤  3 እነሱም የሠራዊት ጌታን የይሖዋን ቤት* ካህናትና ነቢያቱን “ለብዙ ዓመታት እንዳደረግኩት በአምስተኛው ወር ማልቀስና+ መጾም ይኖርብኛል?” ብለው ጠየቁ።

4 የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ዳግመኛ ወደ እኔ መጣ፦ 5 “ለምድሪቱ ነዋሪዎች ሁሉና ለካህናቱ እንዲህ በላቸው፦ ‘ለ70 ዓመታት+ በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር ስትጾሙና ዋይ ዋይ ስትሉ፣+ ትጾሙ የነበረው በእርግጥ ለእኔ ነበር? 6 ትበሉና ትጠጡ በነበረበት ጊዜስ ትበሉና ትጠጡ የነበረው ለራሳችሁ አልነበረም? 7 ኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ያሉት ከተሞቿ በሰዎች ተሞልተውና ሰላም ሰፍኖባቸው በነበረበት ጊዜ እንዲሁም ሰዎች በኔጌብና በሸፌላ ይኖሩ በነበረበት ወቅት ይሖዋ በቀድሞዎቹ ነቢያት አማካኝነት ያወጀውን ቃል መታዘዝ አልነበረባችሁም?’”+

8 የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ዳግመኛ ወደ ዘካርያስ መጣ፦ 9 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በእውነተኛ ፍትሕ ላይ ተመሥርታችሁ ፍረዱ፤+ አንዳችሁ ለሌላው ታማኝ ፍቅርና+ ምሕረት አሳዩ። 10 መበለቲቱንም ሆነ አባት የሌለውን ልጅ፣*+ ከባዕድ አገር የመጣውን ሰውም+ ሆነ ድሃውን አታታሉ፤+ ደግሞም አንዳችሁ በሌላው ላይ ክፉ ለማድረግ በልባችሁ አታሲሩ።’+ 11 እነሱ ግን ለመስማት ፈቃደኛ አልሆኑም፤+ በግትርነትም ጀርባቸውን ሰጡ፤+ ላለመስማትም ሲሉ ጆሯቸውን ደፈኑ።+ 12 ልባቸውን እንደ አልማዝ* አጠነከሩ፤+ እንዲሁም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በመንፈሱ አማካኝነት፣ በቀድሞዎቹ ነቢያት በኩል የላከውን ሕግና* ቃል አልታዘዙም።+ ከዚህም የተነሳ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እጅግ ተቆጣ።”+

13 “‘እኔ ስጠራቸው እንዳልሰሙኝ ሁሉ+ እነሱ ሲጣሩም አልሰማቸውም’+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። 14 ‘ደግሞም ወደማያውቋቸው ብሔራት ሁሉ በአውሎ ነፋስ በተንኳቸው፤+ ምድሪቱም ትተዋት ከሄዱ በኋላ ባድማ ሆነች፤ በእሷ የሚያልፍ ወይም ወደ እሷ የሚመለስ ማንም የለም፤+ የተወደደችውን ምድር አስፈሪ ቦታ አድርገዋታልና።’”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ