የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፀአት 4:21
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 21 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደ ግብፅ ከተመለስክ በኋላ፣ በሰጠሁህ ኃይል የምታከናውናቸውን ተአምራት ሁሉ በፈርዖን ፊት መፈጸም እንዳለብህ አትዘንጋ።+ እኔ ግን ልቡ እንዲደነድን እፈቅዳለሁ፤+ እሱም ሕዝቡን አይለቅም።+

  • ዘፀአት 7:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ያም ሆኖ የፈርዖን ልብ ደነደነ፤+ ልክ ይሖዋ እንዳለውም ያሉትን ነገር አልሰማቸውም።

  • ዘፀአት 7:22
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 22 ይሁንና አስማት የሚሠሩ የግብፅ ካህናትም በሚስጥራዊ ጥበባቸው ተመሳሳይ ነገር አደረጉ፤+ በመሆኑም የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ ልክ ይሖዋ እንዳለውም እነሱን ለመስማት እንቢተኛ ሆነ።+

  • ዘፀአት 8:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 ፈርዖንም ችግሩ ጋብ ማለቱን ባየ ጊዜ ልቡን አደነደነ፤ ልክ ይሖዋ እንደተናገረውም እነሱን ለመስማት ፈቃደኛ አልሆነም።+

  • ዘፀአት 8:19
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 19 በመሆኑም አስማተኞቹ ካህናት ፈርዖንን “ይህ የአምላክ ጣት ነው!”+ አሉት። የፈርዖን ልብ ግን ደነደነ፤ ልክ ይሖዋ እንዳለውም እነሱን አልሰማቸውም።

  • ዘፀአት 9:12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 ሆኖም ይሖዋ የፈርዖን ልብ እንዲደነድን ፈቀደ፤ ፈርዖንም ልክ ይሖዋ ለሙሴ እንደነገረው እነሱን አልሰማቸውም።+

  • ዘፀአት 9:35
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 35 የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ ልክ ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት እንደተናገረውም እስራኤላውያንን አለቀቀም።+

  • ዘፀአት 10:20
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 20 ሆኖም ይሖዋ የፈርዖን ልብ እንዲደነድን ፈቀደ፤+ እሱም እስራኤላውያንን አለቀቀም።

  • ዘፀአት 10:27
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 27 ይሖዋም የፈርዖን ልብ እንዲደነድን ፈቀደ፤ እሱም ሊለቃቸው ፈቃደኛ አልሆነም።+

  • ዘፀአት 11:10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 ሙሴና አሮንም እነዚህን ሁሉ ተአምራት በፈርዖን ፊት ፈጸሙ፤+ ሆኖም ይሖዋ የፈርዖን ልብ እንዲደነድን ስለፈቀደ ፈርዖን እስራኤላውያን ከምድሩ እንዲሄዱ ለመልቀቅ ፈቃደኛ አልሆነም።+

  • ዘፀአት 14:8
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 8 በዚህ መንገድ ይሖዋ የግብፁ ንጉሥ የፈርዖን ልብ እንዲደነድን ፈቀደ፤ እስራኤላውያን ወጥተው በልበ ሙሉነት* እየሄዱ ሳሉ ፈርዖን እነሱን ማሳደዱን ተያያዘው።+

  • ሮም 9:17, 18
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 17 ቅዱስ መጽሐፉ ስለ ፈርዖን ሲናገር “በሕይወት ያቆየሁህ ኃይሌን በአንተ ለማሳየትና ስሜ በመላው ምድር እንዲታወጅ ለማድረግ ነው” ይላል።+ 18 ስለዚህ አምላክ የፈለገውን ይምራል፤ የፈለገውን ደግሞ ግትር እንዲሆን ይፈቅዳል።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ