የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢያሱ 16:10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 ሆኖም በጌዜር+ ይኖሩ የነበሩትን ከነአናውያን አላባረሯቸውም፤ ከነአናውያንም እስከ ዛሬ ድረስ በኤፍሬም መካከል ይኖራሉ፤+ የግዳጅ ሥራ የመሥራት ግዴታም ተጥሎባቸዋል።+

  • 1 ነገሥት 9:20-22
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 20 ከእስራኤላውያን ወገን ያልሆኑትን+ ከአሞራውያን፣ ከሂታውያን፣ ከፈሪዛውያን፣ ከሂዋውያንና ከኢያቡሳውያን+ የተረፉትን ሕዝቦች በሙሉ 21 ይኸውም እስራኤላውያን ፈጽመው ሊያጠፏቸው ያልቻሏቸውን በምድሪቱ ላይ የቀሩትን ዘሮቻቸውን ሰለሞን እንደ ባሪያ ሆነው የግዳጅ ሥራ እንዲሠሩ መልምሏቸው ነበር፤ እስከ ዛሬም ድረስ ይሠራሉ።+ 22 ሆኖም ሰለሞን ከእስራኤላውያን መካከል አንዳቸውንም ባሪያ አላደረገም፤+ ምክንያቱም እነሱ ተዋጊዎቹ፣ አገልጋዮቹ፣ መኳንንቱ፣ የጦር መኮንኖቹ እንዲሁም የሠረገለኞቹና የፈረሰኞቹ አለቆች ነበሩ።

  • 2 ዜና መዋዕል 2:2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 2 ሰለሞን 70,000 ተራ የጉልበት ሠራተኞችና* በተራሮቹ ላይ ድንጋይ የሚጠርቡ 80,000 ሰዎች መረጠ፤+ በእነሱም ላይ 3,600 ሰዎችን የበላይ ተመልካቾች አድርጎ ሾመ።+

  • 2 ዜና መዋዕል 2:17, 18
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 17 በዚህ ጊዜ ሰለሞን አባቱ ዳዊት ካደረገው ቆጠራ+ በኋላ በእስራኤል ምድር የሚኖሩትን የባዕድ አገር ወንዶች ሁሉ ቆጠረ፤+ ቁጥራቸውም 153,600 ሆነ። 18 ከእነሱም መካከል 70,000ዎቹን ተራ የጉልበት ሠራተኞች፣* 80,000ዎቹን በተራሮቹ ላይ ድንጋይ ጠራቢዎች፣+ 3,600ዎቹን ደግሞ ሰዎቹን የሚያሠሩ የበላይ ተመልካቾች አድርጎ ሾማቸው።+

  • 2 ዜና መዋዕል 8:7-9
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 ከእስራኤል ወገን ያልሆኑትን+ ከሂታውያን፣ ከአሞራውያን፣ ከፈሪዛውያን፣ ከሂዋውያንና ከኢያቡሳውያን+ የተረፉትን ሕዝቦች በሙሉ፣ 8 ይኸውም እስራኤላውያን ፈጽመው ያላጠፏቸውን+ በምድሪቱ ላይ የቀሩትን ዘሮቻቸውን ሰለሞን የግዳጅ ሥራ እንዲሠሩ መለመላቸው፤+ እስከ ዛሬም ድረስ ይሠራሉ። 9 ሆኖም ሰለሞን ለሚያከናውነው ሥራ ከእስራኤላውያን መካከል አንዳቸውንም ባሪያ አላደረገም፤+ ምክንያቱም እነሱ ተዋጊዎቹ፣ የጦር መኮንኖቹ፣ የሠረገለኞቹና የፈረሰኞቹ አለቆች ነበሩ።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ