27 እንዲህ ያለውን ነገር ይኸውም በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የይሖዋን ቤት የማስዋቡን ሐሳብ በንጉሡ ልብ ውስጥ ያኖረው የአባቶቻችን አምላክ ይሖዋ ይወደስ!+ 28 በንጉሡና+ በአማካሪዎቹ+ እንዲሁም ኃያላን በሆኑት የንጉሡ መኳንንት ሁሉ ፊት ታማኝ ፍቅር አሳይቶኛል። በመሆኑም የአምላኬ የይሖዋ እጅ በላዬ ስለነበር ድፍረት አገኘሁ፤ ከእኔም ጋር አብረው እንዲሄዱ ከእስራኤል መካከል መሪ የሆኑትን ሰበሰብኩ።