ኢሳይያስ
3 ይሖዋን በመፍራትም ደስ ይሰኛል።+
ዓይኑ እንዳየ አይፈርድም
ወይም ጆሮው በሰማው ነገር ላይ ብቻ ተመሥርቶ አይወቅስም።+
4 ለችግረኞች በትክክል* ይፈርዳል፤
በምድር ላሉ የዋሆች ጥቅም ሲል ሌሎችን ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ይወቅሳል።
5 ጽድቅ የወገቡ መታጠቂያ፣
ታማኝነትም የጎኑ መታጠቂያ ይሆናል።+
6 ተኩላ ከበግ ጠቦት ጋር የሚቀመጥበት ጊዜ ይኖራል፤+
ነብርም ከፍየል ግልገል ጋር ይተኛል፤
ጥጃ፣ አንበሳና* የሰባ ከብት አብረው ይሆናሉ፤*+
ትንሽ ልጅም ይመራቸዋል።
7 ላምና ድብ አብረው ይበላሉ፤
ልጆቻቸውም አብረው ይተኛሉ።
አንበሳ እንደ በሬ ገለባ ይበላል።+
8 ጡት የሚጠባ ሕፃንም በእባብ* ጉድጓድ ላይ ይጫወታል፤
ጡት የጣለውም ሕፃን እጁን በመርዘኛ እባብ ጎሬ ላይ ያደርጋል።
10 በዚያን ቀን የእሴይ ሥር+ ለሕዝቦች ምልክት* ሆኖ ይቆማል።+
11 በዚያን ቀን ይሖዋ ዳግመኛ እጁን ዘርግቶ የተረፉትን የሕዝቡን ቀሪዎች ለሁለተኛ ጊዜ ከአሦር፣+ ከግብፅ፣+ ከጳትሮስ፣+ ከኢትዮጵያ፣*+ ከኤላም፣+ ከሰናኦር፣* ከሃማትና ከባሕር ደሴቶች+ መልሶ ይሰበስባል። 12 ለብሔራት ምልክት* ያቆማል፤ በየቦታው የተሰራጩትን እስራኤላውያንም መልሶ ያመጣቸዋል፤+ እንዲሁም የተበታተኑትን የይሁዳ ሰዎች ከአራቱም የምድር ማዕዘኖች ይሰበስባል።+
13 የኤፍሬም ቅናት ይወገዳል፤+
ይሁዳንም የሚጠሉ ይጠፋሉ።
ኤፍሬም በይሁዳ አይቀናም፤
ይሁዳም ኤፍሬምን አይጠላውም።+
14 በምዕራብ በኩል በፍልስጤም ተረተር* ላይ በድንገት ይወርዳሉ፤
ግንባር ፈጥረው በምሥራቅ የሚኖሩ ሕዝቦችን ይዘርፋሉ።