መዝሙር 104:27, 28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 በወቅቱ ምግባቸውን እንድትሰጣቸው፣ሁሉም አንተን ይጠባበቃሉ።+ 28 አንተ የምትሰጣቸውን ይሰበስባሉ።+ እጅህን ስትከፍት መልካም ነገሮችን ይጠግባሉ።+ መዝሙር 107:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 እሱ የተጠማውን* አርክቷልና፤የተራበውንም* በመልካም ነገሮች አጥግቧል።+ መዝሙር 132:14, 15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 “ይህች ለዘላለም ማረፊያ ስፍራዬ ነች፤በእሷ እኖራለሁ፤+ ይህ ምኞቴ ነውና። 15 የተትረፈረፈ የምግብ አቅርቦት እንዲኖራት በማድረግ እባርካታለሁ፤ድሆቿን እህል አጠግባለሁ።+
14 “ይህች ለዘላለም ማረፊያ ስፍራዬ ነች፤በእሷ እኖራለሁ፤+ ይህ ምኞቴ ነውና። 15 የተትረፈረፈ የምግብ አቅርቦት እንዲኖራት በማድረግ እባርካታለሁ፤ድሆቿን እህል አጠግባለሁ።+