13 ከሕዝቦች መካከል አወጣቸዋለሁ፤ ከየአገሩም እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ ምድራቸውም አመጣቸዋለሁ፤ በእስራኤል ተራሮች፣ በየጅረቱ ዳርና በምድሪቱ ላይ በሚገኙት መኖሪያ ስፍራዎች ሁሉ አሰማራቸዋለሁ።+ 14 ጥሩ በሆነ መስክ ላይ አሰማራቸዋለሁ፤ ከፍ ያሉት የእስራኤል ተራሮችም የግጦሽ መሬት ይሆኗቸዋል።+ በዚያም ጥሩ በሆነ የግጦሽ መሬት ላይ ያርፋሉ፤+ በእስራኤልም ተራሮች ላይ በለመለመ መስክ ይሰማራሉ።”