ሩት 2:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ላደረግሽው ሁሉ ይሖዋ ብድራትሽን ይመልስልሽ፤+ በክንፎቹ ሥር ለመጠለል+ ብለሽ ወደ እሱ የመጣሽበት የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሙሉ ዋጋሽን* ይክፈልሽ።” መዝሙር 17:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 እንደ ዓይንህ ብሌን ጠብቀኝ፤+በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ።+ መዝሙር 91:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 በላባዎቹ ይከልልሃል፤*በክንፎቹም ሥር መጠጊያ ታገኛለህ።+ ታማኝነቱ+ ትልቅ ጋሻና+ መከላከያ ቅጥር* ይሆንልሃል።