መዝሙር 27:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 ይሖዋ ብርሃኔና+ አዳኜ ነው። ማንን እፈራለሁ?+ ይሖዋ የሕይወቴ ተገን ነው።+ ማን ያሸብረኛል? መዝሙር 62:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 በእርግጥም እሱ ዓለቴና አዳኜ እንዲሁም አስተማማኝ መጠጊያዬ ነው፤+ከልክ በላይ አልናወጥም።+ ኢሳይያስ 12:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 እነሆ፣ አምላክ አዳኜ ነው!+ በእሱ እታመናለሁ፤ ምንም የሚያስፈራኝ ነገር የለም፤+ያህ* ይሖዋ ብርታቴና ኃይሌ ነው፤ለእኔም አዳኝ ሆኖልኛል።”+