-
ዘፀአት 23:5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 የሚጠላህ ሰው አህያ ጭነቱ ከብዶት ወድቆ ብታይ ዝም ብለህ አትለፈው። ከዚህ ይልቅ ጭነቱን ከእንስሳው ላይ ለማውረድ እርዳው።+
-
-
2 ነገሥት 6:21, 22አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
21 የእስራኤል ንጉሥ ባያቸው ጊዜ ኤልሳዕን “አባቴ ሆይ፣ ልግደላቸው? ልፍጃቸው?” አለው። 22 እሱ ግን እንዲህ አለው፦ “አትግደላቸው። ለመሆኑ በሰይፍህ ወይም በቀስትህ ማርከህ የወሰድካቸውን ሰዎች ትገድላለህ? በል አሁን እንዲበሉና እንዲጠጡ ምግብና ውኃ ስጣቸው፤+ ከዚያም ወደ ጌታቸው ይመለሱ።”
-