-
ኢሳይያስ 44:16, 17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
16 ግማሹን በእሳት ያነደዋል፤
በዚያም ላይ የሚበላውን ሥጋ ይጠብሳል፤ በልቶም ይጠግባል።
እሳቱንም እየሞቀ
“እሰይ! እሳቱን እያየሁ ሞቅኩ” ይላል።
17 የቀረውን ግን ምስል ይቀርጽበታል፤ አምላክ አድርጎም ይሠራዋል።
በፊቱም ተደፍቶ ይሰግድለታል።
“አንተ አምላኬ ነህና አድነኝ” ብሎ
ወደ እሱ ይጸልያል።+
-
-
ዳንኤል 3:5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 የቀንደ መለከት፣ የእምቢልታ፣ የተለያዩ ባለ አውታር መሣሪያዎች፣ የባለ ሦስት ማዕዘን በገና፣ የባለ ከረጢት ዋሽንትና የሌሎቹን የሙዚቃ መሣሪያዎች ሁሉ ድምፅ ስትሰሙ በግንባራችሁ ተደፍታችሁ ንጉሥ ናቡከደነጾር ላቆመው የወርቅ ምስል ስገዱ።
-