ኢሳይያስ 11:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 በዚያን ቀን ይሖዋ ዳግመኛ እጁን ዘርግቶ የተረፉትን የሕዝቡን ቀሪዎች ለሁለተኛ ጊዜ ከአሦር፣+ ከግብፅ፣+ ከጳትሮስ፣+ ከኢትዮጵያ፣*+ ከኤላም፣+ ከሰናኦር፣* ከሃማትና ከባሕር ደሴቶች+ መልሶ ይሰበስባል። ኢሳይያስ 35:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ይሖዋ የዋጃቸው ይመለሳሉ፤+ ወደ ጽዮንም በእልልታ ይመጣሉ።+ ፍጻሜ የሌለው ደስታን እንደ አክሊል ይጎናጸፋሉ።+ ደስታንና ሐሴትን ያገኛሉ፤ሐዘንና ሲቃም ከዚያ ይርቃሉ።+ ኤርምያስ 29:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 እኔም እገኝላችኋለሁ’+ ይላል ይሖዋ። ‘በምርኮ የተወሰዱትን ወገኖቻችሁን እሰበስባለሁ፤ እናንተን ከበተንኩባቸው ብሔራትና ቦታዎች ሁሉ እሰበስባችኋለሁ’+ ይላል ይሖዋ። ‘በግዞት እንድትወሰዱ ባደረግኩ ጊዜ ትታችሁት ወደሄዳችሁት ቦታ መልሼ አመጣችኋለሁ።’+ ኤርምያስ 31:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ከሰሜን ምድር መልሼ አመጣቸዋለሁ።+ ከምድር ዳርቻዎች እሰበስባቸዋለሁ።+ በመካከላቸው ዓይነ ስውርና አንካሳ፣+ነፍሰ ጡርና ልትወልድ የተቃረበች ሴት በአንድነት ይገኛሉ። ታላቅ ጉባኤ ሆነው ወደዚህ ይመለሳሉ።+
11 በዚያን ቀን ይሖዋ ዳግመኛ እጁን ዘርግቶ የተረፉትን የሕዝቡን ቀሪዎች ለሁለተኛ ጊዜ ከአሦር፣+ ከግብፅ፣+ ከጳትሮስ፣+ ከኢትዮጵያ፣*+ ከኤላም፣+ ከሰናኦር፣* ከሃማትና ከባሕር ደሴቶች+ መልሶ ይሰበስባል።
10 ይሖዋ የዋጃቸው ይመለሳሉ፤+ ወደ ጽዮንም በእልልታ ይመጣሉ።+ ፍጻሜ የሌለው ደስታን እንደ አክሊል ይጎናጸፋሉ።+ ደስታንና ሐሴትን ያገኛሉ፤ሐዘንና ሲቃም ከዚያ ይርቃሉ።+
14 እኔም እገኝላችኋለሁ’+ ይላል ይሖዋ። ‘በምርኮ የተወሰዱትን ወገኖቻችሁን እሰበስባለሁ፤ እናንተን ከበተንኩባቸው ብሔራትና ቦታዎች ሁሉ እሰበስባችኋለሁ’+ ይላል ይሖዋ። ‘በግዞት እንድትወሰዱ ባደረግኩ ጊዜ ትታችሁት ወደሄዳችሁት ቦታ መልሼ አመጣችኋለሁ።’+
8 ከሰሜን ምድር መልሼ አመጣቸዋለሁ።+ ከምድር ዳርቻዎች እሰበስባቸዋለሁ።+ በመካከላቸው ዓይነ ስውርና አንካሳ፣+ነፍሰ ጡርና ልትወልድ የተቃረበች ሴት በአንድነት ይገኛሉ። ታላቅ ጉባኤ ሆነው ወደዚህ ይመለሳሉ።+