የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ሳሙኤል 15:22
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 22 ከዚያም ሳሙኤል እንዲህ አለ፦ “ይሖዋን ይበልጥ የሚያስደስተው የትኛው ነው? የሚቃጠሉ መባዎችንና መሥዋዕቶችን+ ማቅረብ ወይስ የይሖዋን ቃል መታዘዝ? እነሆ፣ መታዘዝ ከመሥዋዕት፣+ መስማትም ከአውራ በግ ስብ+ ይበልጣል፤

  • ምሳሌ 21:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  3 መሥዋዕት ከማቅረብ ይልቅ

      ትክክልና ፍትሐዊ የሆነ ነገር ማድረግ ይሖዋን ይበልጥ ደስ ያሰኘዋል።+

  • ኢሳይያስ 1:11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 “የመሥዋዕታችሁ ብዛት ለእኔ ምን ይጠቅመኛል?”+ ይላል ይሖዋ።

      “የሚቃጠሉ የአውራ በግ መባዎችና+ የደለቡ እንስሳት ስብ+ በቅቶኛል፤

      በወይፈኖች፣+ በበግ ጠቦቶችና በፍየሎች+ ደም+ ደስ አልሰኝም።

  • ሚክያስ 6:6-8
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  6 በይሖዋ ፊት ምን ይዤ ልቅረብ?

      ከፍ ባለ ስፍራ በሚኖረው አምላክ ፊት ምን ይዤ ልስገድ?

      ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና

      የአንድ ዓመት ጥጃዎች ይዤ ልቅረብ?+

       7 ይሖዋ በሺህ በሚቆጠሩ አውራ በጎች

      ወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋል?+

      ለሠራሁት በደል የበኩር ወንድ ልጄን፣

      ለሠራሁትም* ኃጢአት የሆዴን ፍሬ ላቅርብ?+

       8 ሰው ሆይ፣ መልካም የሆነውን ነግሮሃል።

      ይሖዋ ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው?

      ፍትሕን እንድታደርግ፣*+ ታማኝነትን እንድትወድና*+

      ልክህን አውቀህ+ ከአምላክህ ጋር እንድትሄድ ብቻ ነው!+

  • ማቴዎስ 9:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 እንግዲያው ሄዳችሁ ‘እኔ የምፈልገው ምሕረትን እንጂ መሥዋዕትን አይደለም’+ የሚለውን ቃል ትርጉም አስተውሉ። እኔ የመጣሁት ጻድቃንን ሳይሆን ኃጢአተኞችን ልጠራ ነውና።”

  • ማቴዎስ 12:7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 ይሁንና ‘እኔ የምፈልገው ምሕረትን+ እንጂ መሥዋዕትን+ አይደለም’ የሚለውን ቃል ትርጉም ተረድታችሁ ቢሆን ኖሮ ምንም በደል ባልሠሩት ላይ ባልፈረዳችሁ ነበር።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ