ማቴዎስ 26:57 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 57 ኢየሱስን ያሰሩት ሰዎች ጸሐፍትና ሽማግሌዎች ወደተሰበሰቡበት+ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ+ ወሰዱት። ዮሐንስ 18:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 በመጀመሪያም ወደ ሐና ወሰዱት፤ ምክንያቱም ሐና በዚያ ዓመት ሊቀ ካህናት+ የነበረው የቀያፋ+ አማት ነበር። ዮሐንስ 18:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ከዚያም ሐና ኢየሱስን እንደታሰረ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ላከው።+ የሐዋርያት ሥራ 4:5, 6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 በማግስቱም የሕዝቡ ገዢዎች፣ ሽማግሌዎችና ጸሐፍት በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ፤ 6 የካህናት አለቃው ሐና፣+ ቀያፋ፣+ ዮሐንስ፣ እስክንድርና የካህናት አለቃው ዘመዶችም ሁሉ ከእነሱ ጋር ነበሩ።
5 በማግስቱም የሕዝቡ ገዢዎች፣ ሽማግሌዎችና ጸሐፍት በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ፤ 6 የካህናት አለቃው ሐና፣+ ቀያፋ፣+ ዮሐንስ፣ እስክንድርና የካህናት አለቃው ዘመዶችም ሁሉ ከእነሱ ጋር ነበሩ።