7 ብዙ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን+ ወደሚያጠምቅበት ቦታ ሲመጡ ባየ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የእፉኝት ልጆች፣+ ከሚመጣው ቁጣ+ እንድትሸሹ ያስጠነቀቃችሁ ማን ነው? 8 እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አፍሩ። 9 ‘እኛ እኮ አባታችን አብርሃም ነው’ ብላችሁ አታስቡ።+ አምላክ ለአብርሃም ከእነዚህ ድንጋዮች ልጆች ሊያስነሳለት እንደሚችል ልነግራችሁ እወዳለሁ። 10 መጥረቢያው ዛፎቹ ሥር ተቀምጧል። ስለዚህ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ተቆርጦ እሳት ውስጥ ይጣላል።+