ዘፀአት 23:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 “የሐሰት ወሬ አትንዛ።*+ ተንኮል የሚሸርብ ምሥክር በመሆን ከክፉ ሰው ጋር አትተባበር።+ ዘፀአት 23:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 “ከሐሰት ክስ* ራቅ፤ እኔ ክፉውን ሰው ጻድቅ እንደሆነ አድርጌ ስለማልቆጥር*+ ንጹሑንና ጻድቁን ሰው አትግደል። ዘሌዋውያን 19:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 “‘አትስረቁ፤+ አታታሉ፤+ አንዳችሁ በሌላው ላይ ሐቀኝነት የጎደለው ድርጊት አትፈጽሙ።