-
መዝሙር 122:በመዝሙሩ አናት ላይ የሚገኘው መግለጫ-9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር። የዳዊት መዝሙር።
122 “ወደ ይሖዋ ቤት እንሂድ”
ባሉኝ ጊዜ እጅግ ደስ አለኝ።+
2 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ አሁን በበሮችሽ ገብተን
ከውስጥ ቆመናል።+
3 ኢየሩሳሌም አንድ ወጥ ሆና
እንደተገነባች ከተማ ናት።+
6 ለኢየሩሳሌም ሰላም ጸልዩ።+
አንቺ ከተማ ሆይ፣ አንቺን የሚወዱ ከስጋት ነፃ ይሆናሉ።
7 በመከላከያ ግንቦችሽ* ውስጥ ሰላም ለዘለቄታው ይኑር፤
በማይደፈሩ ማማዎችሽ ውስጥ የተረጋጋ ሁኔታ ይስፈን።
8 እንግዲህ ለወንድሞቼና ለወዳጆቼ ስል
“በውስጥሽ ሰላም ይስፈን” እላለሁ።
9 ለአምላካችን ለይሖዋ ቤት ስል+
ለአንቺ መልካም ነገር እሻለሁ።
-