የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ዜና መዋዕል 7
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ዜና መዋዕል የመጽሐፉ ይዘት

      • ቤተ መቅደሱ በይሖዋ ክብር ተሞላ (1-3)

      • የምረቃው ሥርዓት (4-10)

      • ይሖዋ ለሰለሞን ተገለጠለት (11-22)

2 ዜና መዋዕል 7:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 8:54
  • +ዘሌ 9:24፤ 1ዜና 21:26
  • +ዘፀ 40:34, 35

2 ዜና መዋዕል 7:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 8:11

2 ዜና መዋዕል 7:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 8:62, 63

2 ዜና መዋዕል 7:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕዝራ 6:16

2 ዜና መዋዕል 7:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ሌዋውያኑን የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 25:7፤ 2ዜና 5:11, 12
  • +2ዜና 5:13

2 ዜና መዋዕል 7:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 1:3
  • +2ዜና 4:1
  • +ዘሌ 2:1
  • +ዘሌ 4:8-10፤ 1ነገ 8:64-66

2 ዜና መዋዕል 7:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከሃማት መግቢያ።”

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

  • *

    የዳስ በዓልን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 34:2, 5, 8
  • +ዘሌ 23:34፤ ዘዳ 16:13

2 ዜና መዋዕል 7:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከበዓሉ በኋላ ያለው ቀን ወይም 15ኛው ቀን።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 23:36

2 ዜና መዋዕል 7:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 6:41
  • +ዘዳ 16:15

2 ዜና መዋዕል 7:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መክ 2:4
  • +1ነገ 9:1-3

2 ዜና መዋዕል 7:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 1:7
  • +ዘዳ 12:5, 6፤ መዝ 78:68

2 ዜና መዋዕል 7:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 43:10
  • +ዘሌ 26:41፤ 2ዜና 33:12, 13
  • +ኢሳ 55:7
  • +2ዜና 6:39

2 ዜና መዋዕል 7:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 6:40

2 ዜና መዋዕል 7:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 12:21
  • +2ዜና 6:20

2 ዜና መዋዕል 7:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 9:4, 5

2 ዜና መዋዕል 7:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 2:4
  • +መዝ 89:28, 29
  • +2ሳሙ 7:12, 13

2 ዜና መዋዕል 7:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:5፤ 1ነገ 9:6-9

2 ዜና መዋዕል 7:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “መተረቻና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 4:25, 26፤ 2ነገ 17:20
  • +ዘዳ 28:37፤ ኤር 24:9

2 ዜና መዋዕል 7:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 29:8፤ ዳን 9:12
  • +ዘዳ 29:24, 25፤ 2ነገ 25:8, 9፤ ኤር 22:8, 9

2 ዜና መዋዕል 7:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 12:51
  • +2ዜና 15:2
  • +ኢሳ 2:8፤ ኤር 2:11
  • +2ዜና 36:17

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ዜና 7:11ነገ 8:54
2 ዜና 7:1ዘሌ 9:24፤ 1ዜና 21:26
2 ዜና 7:1ዘፀ 40:34, 35
2 ዜና 7:21ነገ 8:11
2 ዜና 7:41ነገ 8:62, 63
2 ዜና 7:5ዕዝራ 6:16
2 ዜና 7:61ዜና 25:7፤ 2ዜና 5:11, 12
2 ዜና 7:62ዜና 5:13
2 ዜና 7:7ዘሌ 1:3
2 ዜና 7:72ዜና 4:1
2 ዜና 7:7ዘሌ 2:1
2 ዜና 7:7ዘሌ 4:8-10፤ 1ነገ 8:64-66
2 ዜና 7:8ዘኁ 34:2, 5, 8
2 ዜና 7:8ዘሌ 23:34፤ ዘዳ 16:13
2 ዜና 7:9ዘሌ 23:36
2 ዜና 7:102ዜና 6:41
2 ዜና 7:10ዘዳ 16:15
2 ዜና 7:11መክ 2:4
2 ዜና 7:111ነገ 9:1-3
2 ዜና 7:122ዜና 1:7
2 ዜና 7:12ዘዳ 12:5, 6፤ መዝ 78:68
2 ዜና 7:14ኢሳ 43:10
2 ዜና 7:14ዘሌ 26:41፤ 2ዜና 33:12, 13
2 ዜና 7:14ኢሳ 55:7
2 ዜና 7:142ዜና 6:39
2 ዜና 7:152ዜና 6:40
2 ዜና 7:16ዘዳ 12:21
2 ዜና 7:162ዜና 6:20
2 ዜና 7:171ነገ 9:4, 5
2 ዜና 7:181ነገ 2:4
2 ዜና 7:18መዝ 89:28, 29
2 ዜና 7:182ሳሙ 7:12, 13
2 ዜና 7:19ዘፀ 20:5፤ 1ነገ 9:6-9
2 ዜና 7:20ዘዳ 4:25, 26፤ 2ነገ 17:20
2 ዜና 7:20ዘዳ 28:37፤ ኤር 24:9
2 ዜና 7:212ዜና 29:8፤ ዳን 9:12
2 ዜና 7:21ዘዳ 29:24, 25፤ 2ነገ 25:8, 9፤ ኤር 22:8, 9
2 ዜና 7:22ዘፀ 12:51
2 ዜና 7:222ዜና 15:2
2 ዜና 7:22ኢሳ 2:8፤ ኤር 2:11
2 ዜና 7:222ዜና 36:17
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ዜና መዋዕል 7:1-22

ሁለተኛ ዜና መዋዕል

7 ሰለሞንም ጸሎቱን እንደጨረሰ+ እሳት ከሰማያት ወርዶ+ የሚቃጠለውን መባና መሥዋዕቶቹን በላ፤ የይሖዋም ክብር ቤቱን ሞላው።+ 2 የይሖዋ ክብር የይሖዋን ቤት ሞልቶት ስለነበር ካህናቱ ወደ ይሖዋ ቤት መግባት አልቻሉም።+ 3 የእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ እሳቱ ሲወርድና የይሖዋ ክብር ከቤቱ በላይ ሲሆን ይመለከቱ ነበር፤ ወደ መሬት አጎንብሰው ድንጋይ በተነጠፈበት ወለል ላይ በግንባራቸው ተደፍተው ሰገዱ፤ ደግሞም “እሱ ጥሩ ነውና፤ ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል” እያሉ ይሖዋን አመሰገኑ።

4 ከዚያም ንጉሡና ሕዝቡ ሁሉ በይሖዋ ፊት መሥዋዕት አቀረቡ።+ 5 ንጉሥ ሰለሞን 22,000 ከብቶችና 120,000 በጎች መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ። በዚህ መንገድ ንጉሡና ሕዝቡ ሁሉ የእውነተኛውን አምላክ ቤት መረቁ።+ 6 ካህናቱም ሆኑ የይሖዋን መዝሙር ለማጀብ የሚያገለግሉ የሙዚቃ መሣሪያዎችን የያዙት ሌዋውያን እንዲያገለግሉ በተመደቡበት ስፍራ ቆመው ነበር።+ (ንጉሥ ዳዊት እነዚህን መሣሪያዎች የሠራው ከእነሱ ጋር* ሆኖ ውዳሴ በሚያቀርብበት ጊዜ “ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና” በማለት ይሖዋን ለማመስገን ነው።) ካህናቱ በእነሱ ትይዩ ሆነው መለከቶቹን በኃይል ይነፉ ነበር፤+ በዚህ ጊዜ እስራኤላውያን ሁሉ በዚያ ቆመው ነበር።

7 ከዚያም ሰለሞን በይሖዋ ቤት ፊት የሚገኘውን የግቢውን መሃል ቀደሰው፤ ምክንያቱም ሰለሞን የሚቃጠለውን መባና+ የኅብረት መሥዋዕቱን ስብ በዚያ ማቅረብ ነበረበት፤ ይህም የሆነው ሰለሞን የሠራው የመዳብ መሠዊያ+ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፣ የእህሉን መባና+ ስቡን+ መያዝ ስላልቻለ ነው። 8 በዚያን ጊዜ ሰለሞን ከመላው እስራኤል ጋር ይኸውም ከሌቦሃማት* አንስቶ እስከ ግብፅ ደረቅ ወንዝ* ድረስ+ ካለው ምድር ከመጣው ታላቅ ጉባኤ ጋር በመሆን ለሰባት ቀን በዓሉን* አከበረ።+ 9 ይሁንና የመሠዊያውን የምረቃ ሥነ ሥርዓት ለሰባት ቀን ስላከናወኑና በዓሉን ለሰባት ቀን ስላከበሩ በስምንተኛው ቀን* የተቀደሰ ጉባኤ አደረጉ።+ 10 ከዚያም በሰባተኛው ወር፣ በ23ኛው ቀን ሕዝቡን ወደየቤታቸው አሰናበተ፤ እነሱም ይሖዋ ለዳዊት፣ ለሰለሞንና ለሕዝቡ ለእስራኤል ባሳየው ጥሩነት እየተደሰቱና+ ከልባቸው እየፈነደቁ ሄዱ።+

11 ሰለሞንም የይሖዋን ቤትና የንጉሡን ቤት*+ ሠርቶ ጨረሰ፤ ከይሖዋ ቤትና ከራሱ ቤት ጋር በተያያዘ በልቡ ያሰበውን ሁሉ በተሳካ ሁኔታ አከናወነ።+ 12 ከዚያም ይሖዋ በሌሊት ለሰለሞን ተገልጦለት+ እንዲህ አለው፦ “ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ ይህን ቦታ መሥዋዕት የሚቀርብበት ቤት እንዲሆን ለራሴ መርጬዋለሁ።+ 13 ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማያትን ብዘጋ፣ ምድሪቱን እንዲበሉ አንበጦችን ብልክ፣ በሕዝቤ መካከል ቸነፈር ብሰድ፣ 14 በስሜ የተጠሩትም ሕዝቤ+ ራሳቸውን ዝቅ ቢያደርጉ፣+ ቢጸልዩ፣ ፊቴን ቢሹና ከክፉ መንገዳቸው ቢመለሱ፣+ ከሰማያት ሆኜ እሰማለሁ፤ ኃጢአታቸውን ይቅር እላለሁ፤ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ።+ 15 በዚህም ስፍራ ለሚቀርበው ጸሎት ዓይኖቼ ይገለጣሉ፤ ጆሮዎቼም ይከፈታሉ።+ 16 አሁንም ስሜ ለዘለቄታው በዚያ እንዲጠራ ይህን ቤት መርጬዋለሁ፤+ ደግሞም ቀድሼዋለሁ፤ ዓይኔም ሆነ ልቤ ሁልጊዜ በዚያ ይሆናል።+

17 “አንተም አባትህ ዳዊት እንዳደረገው ያዘዝኩህን ሁሉ በመፈጸም በፊቴ ብትሄድ እንዲሁም ሥርዓቶቼንና ድንጋጌዎቼን ብትጠብቅ፣+ 18 ለአባትህ ለዳዊት ‘ከዘር ሐረግህ በእስራኤል ላይ ገዢ የሚሆን አይታጣም’+ በማለት በገባሁለት ቃል ኪዳን መሠረት+ የንግሥና ዙፋንህን አጸናለሁ።+ 19 ሆኖም ጀርባችሁን ብትሰጡ፣ በፊታችሁ ያስቀመጥኳቸውን ደንቦቼንና ትእዛዛቴን ብትተዉ፣ ሄዳችሁም ሌሎች አማልክትን ብታገለግሉና ለእነሱ ብትሰግዱ፣+ 20 እስራኤልን ከሰጠሁት ምድሬ ላይ እነቅለዋለሁ፤+ ለስሜ የቀደስኩትንም ይህን ቤት ከፊቴ አስወግደዋለሁ፤ በሕዝቦች ሁሉ ዘንድ መቀለጃና* መሳለቂያ አደርገዋለሁ።+ 21 ይህም ቤት የፍርስራሽ ክምር ይሆናል። በዚያም የሚያልፉ ሰዎች ሁሉ በመገረም ትኩር ብለው እየተመለከቱ+ ‘ይሖዋ በዚህች ምድርና በዚህ ቤት ላይ እንዲህ ያለ ነገር ያደረገው ለምንድን ነው?’ በማለት ይጠይቃሉ።+ 22 ከዚያም እንዲህ ይላሉ፦ ‘ይህ የደረሰባቸው ከግብፅ ምድር ያወጣቸውን+ የአባቶቻቸውን አምላክ ይሖዋን ትተው+ ሌሎች አማልክትን ስለተከተሉና ለእነሱ ስለሰገዱ እንዲሁም እነሱን ስላገለገሉ ነው።+ ይህን ሁሉ መከራ ያመጣባቸው ለዚህ ነው።’”+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ