ዘኁልቁ 21:8, 9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የመርዛማ* እባብ ምስል ሠርተህ እንጨት ላይ ስቀለው። ማንኛውም ሰው በሚነደፍበት ጊዜ በሕይወት እንዲኖር ምስሉን ማየት አለበት።” 9 ሙሴም ወዲያው የመዳብ እባብ+ ሠርቶ እንጨት ላይ ሰቀለው፤+ አንድ ሰው እባብ ሲነድፈው ከመዳብ ወደተሠራው እባብ ከተመለከተ ይድን ነበር።+ ዳንኤል 7:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 “በሌሊት የተገለጡልኝን ራእዮች ማየቴን ቀጠልኩ፤ እነሆ የሰው ልጅ+ የሚመስል ከሰማያት ደመና ጋር መጣ፤ ከዘመናት በፊት ወደነበረውም+ እንዲገባ ተፈቀደለት፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት። ማቴዎስ 26:64 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 64 ኢየሱስም “አንተው ራስህ ተናገርከው። ነገር ግን እላችኋለሁ፦ ከዚህ በኋላ የሰው ልጅ+ በኃያሉ ቀኝ ተቀምጦ+ በሰማይ ደመና ሲመጣ ታያላችሁ”+ አለው። ዮሐንስ 3:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ሙሴ በምድረ በዳ እባቡን እንደሰቀለ፣+ የሰው ልጅም እንዲሁ ሊሰቀል ይገባዋል፤+ ዮሐንስ 12:32, 33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 እኔ ግን ከምድር ወደ ላይ ከፍ ከተደረግኩ+ ሁሉንም ዓይነት ሰዎች ወደ ራሴ እስባለሁ።” 33 ይህን የተናገረው በቅርብ ጊዜ ውስጥ ምን ዓይነት አሟሟት እንደሚሞት ለማመልከት ነው።+ ገላትያ 3:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ክርስቶስ በእኛ ፋንታ የተረገመ ሆኖ እኛን ከሕጉ እርግማን ነፃ በማውጣት+ ዋጅቶናል፤+ ምክንያቱም “በእንጨት ላይ የተሰቀለ ሰው ሁሉ የተረገመ ነው” ተብሎ ተጽፏል።+
8 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የመርዛማ* እባብ ምስል ሠርተህ እንጨት ላይ ስቀለው። ማንኛውም ሰው በሚነደፍበት ጊዜ በሕይወት እንዲኖር ምስሉን ማየት አለበት።” 9 ሙሴም ወዲያው የመዳብ እባብ+ ሠርቶ እንጨት ላይ ሰቀለው፤+ አንድ ሰው እባብ ሲነድፈው ከመዳብ ወደተሠራው እባብ ከተመለከተ ይድን ነበር።+
13 “በሌሊት የተገለጡልኝን ራእዮች ማየቴን ቀጠልኩ፤ እነሆ የሰው ልጅ+ የሚመስል ከሰማያት ደመና ጋር መጣ፤ ከዘመናት በፊት ወደነበረውም+ እንዲገባ ተፈቀደለት፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት።
32 እኔ ግን ከምድር ወደ ላይ ከፍ ከተደረግኩ+ ሁሉንም ዓይነት ሰዎች ወደ ራሴ እስባለሁ።” 33 ይህን የተናገረው በቅርብ ጊዜ ውስጥ ምን ዓይነት አሟሟት እንደሚሞት ለማመልከት ነው።+
13 ክርስቶስ በእኛ ፋንታ የተረገመ ሆኖ እኛን ከሕጉ እርግማን ነፃ በማውጣት+ ዋጅቶናል፤+ ምክንያቱም “በእንጨት ላይ የተሰቀለ ሰው ሁሉ የተረገመ ነው” ተብሎ ተጽፏል።+