-
ዘፀአት 20:11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 ምክንያቱም ይሖዋ ሰማያትን፣ ምድርን፣ ባሕርንና በውስጣቸው ያሉትን ነገሮች ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ ሠርቶ ካጠናቀቀ በኋላ በሰባተኛው ቀን ማረፍ ጀምሯል።+ ይሖዋ የሰንበትን ቀን የባረከውና የቀደሰው ለዚህ ነው።
-
-
ነህምያ 9:6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 “አንተ ብቻ ይሖዋ ነህ፤+ አንተ ሰማያትን፣ አዎ ሰማየ ሰማያትንና ሠራዊታቸውን ሁሉ፣ ምድርንና በላይዋ ያሉትን ሁሉ፣ ባሕርንና በውስጡ ያሉትን ሁሉ ሠርተሃል። ሁሉንም ሕያው አድርገህ ታኖራቸዋለህ፤ የሰማይ ሠራዊትም ለአንተ ይሰግዳል።
-