መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በማሃላት ቅኝት።* ማስኪል።* የዳዊት መዝሙር።
53 ሞኝ* ሰው በልቡ
“ይሖዋ የለም” ይላል።+
የዓመፅ ድርጊታቸው ብልሹና አስጸያፊ ነው፤
መልካም የሚሠራ ማንም የለም።+
3 ሁሉም ወደ ሌላ ዞር ብለዋል፤
ሁሉም ብልሹ ናቸው።
መልካም የሚሠራ ማንም የለም፤
አንድ እንኳ የለም።+
4 ከክፉ አድራጊዎቹ መካከል አንዳቸውም አያስተውሉም?
ምግብ እንደሚበሉ ሕዝቤን ይውጣሉ።
ይሖዋን አይጠሩም።+
ይሖዋ ስላልተቀበላቸው አንተ ታዋርዳቸዋለህ።
6 የእስራኤል መዳን ምነው ከጽዮን በመጣ!+
ይሖዋ የተማረከውን ሕዝቡን በሚመልስበት ጊዜ፣
ያዕቆብ ደስ ይበለው፤ እስራኤል ሐሴት ያድርግ።