የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ሳሙኤል 21
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ሳሙኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • ገባኦናውያን የሳኦልን ቤት ተበቀሉ (1-14)

      • ከፍልስጤማውያን ጋር የተደረጉ ጦርነቶች (15-22)

2 ሳሙኤል 21:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:18, 20
  • +ዘፍ 9:6፤ ዘፀ 20:13፤ ዘኁ 35:30, 33

2 ሳሙኤል 21:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 9:3, 27
  • +ዘፍ 10:15, 16
  • +ኢያሱ 9:15

2 ሳሙኤል 21:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 35:31

2 ሳሙኤል 21:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 21:1

2 ሳሙኤል 21:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እናሰጣለን።” እጃቸውንና እግራቸውን ሰብረው እንደሚያሰጧቸው ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 9:17
  • +1ሳሙ 10:26
  • +ዘኁ 25:4፤ ዘዳ 21:22

2 ሳሙኤል 21:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 18:3፤ 20:42
  • +2ሳሙ 4:4፤ 9:10፤ 19:24

2 ሳሙኤል 21:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ሜሮብ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 3:7
  • +1ሳሙ 18:20፤ 25:44፤ 2ሳሙ 3:14፤ 6:23
  • +1ሳሙ 18:19

2 ሳሙኤል 21:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 35:31፤ ዘዳ 19:21

2 ሳሙኤል 21:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 3:7

2 ሳሙኤል 21:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ባለርስቶች” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 2:5
  • +1ሳሙ 28:4፤ 31:1, 11, 12፤ 2ሳሙ 1:6፤ 1ዜና 10:8

2 ሳሙኤል 21:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በድናቸው የተሰጣውን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 21:9

2 ሳሙኤል 21:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 18:28
  • +1ሳሙ 9:1፤ 10:11
  • +ኢያሱ 7:24-26፤ 2ሳሙ 24:25

2 ሳሙኤል 21:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 5:17, 22

2 ሳሙኤል 21:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወደ 3.42 ኪሎ ግራም ገደማ ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 2:11
  • +1ሳሙ 17:4, 7፤ 1ዜና 11:23

2 ሳሙኤል 21:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 23:18, 19
  • +2ሳሙ 22:19
  • +2ሳሙ 18:3
  • +1ነገ 11:36፤ 15:4፤ 2ነገ 8:19

2 ሳሙኤል 21:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 20:4
  • +1ዜና 11:26, 29፤ 27:1, 11
  • +ዘፍ 14:5

2 ሳሙኤል 21:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 20:5
  • +1ሳሙ 17:4, 7

2 ሳሙኤል 21:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 20:6-8

2 ሳሙኤል 21:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 17:10, 45፤ 2ነገ 19:22
  • +1ሳሙ 16:9፤ 17:13፤ 1ዜና 2:13

2 ሳሙኤል 21:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 60:12

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ሳሙ. 21:1ዘሌ 26:18, 20
2 ሳሙ. 21:1ዘፍ 9:6፤ ዘፀ 20:13፤ ዘኁ 35:30, 33
2 ሳሙ. 21:2ኢያሱ 9:3, 27
2 ሳሙ. 21:2ዘፍ 10:15, 16
2 ሳሙ. 21:2ኢያሱ 9:15
2 ሳሙ. 21:4ዘኁ 35:31
2 ሳሙ. 21:52ሳሙ 21:1
2 ሳሙ. 21:61ሳሙ 9:17
2 ሳሙ. 21:61ሳሙ 10:26
2 ሳሙ. 21:6ዘኁ 25:4፤ ዘዳ 21:22
2 ሳሙ. 21:71ሳሙ 18:3፤ 20:42
2 ሳሙ. 21:72ሳሙ 4:4፤ 9:10፤ 19:24
2 ሳሙ. 21:82ሳሙ 3:7
2 ሳሙ. 21:81ሳሙ 18:20፤ 25:44፤ 2ሳሙ 3:14፤ 6:23
2 ሳሙ. 21:81ሳሙ 18:19
2 ሳሙ. 21:9ዘኁ 35:31፤ ዘዳ 19:21
2 ሳሙ. 21:102ሳሙ 3:7
2 ሳሙ. 21:122ሳሙ 2:5
2 ሳሙ. 21:121ሳሙ 28:4፤ 31:1, 11, 12፤ 2ሳሙ 1:6፤ 1ዜና 10:8
2 ሳሙ. 21:132ሳሙ 21:9
2 ሳሙ. 21:14ኢያሱ 18:28
2 ሳሙ. 21:141ሳሙ 9:1፤ 10:11
2 ሳሙ. 21:14ኢያሱ 7:24-26፤ 2ሳሙ 24:25
2 ሳሙ. 21:152ሳሙ 5:17, 22
2 ሳሙ. 21:16ዘዳ 2:11
2 ሳሙ. 21:161ሳሙ 17:4, 7፤ 1ዜና 11:23
2 ሳሙ. 21:172ሳሙ 23:18, 19
2 ሳሙ. 21:172ሳሙ 22:19
2 ሳሙ. 21:172ሳሙ 18:3
2 ሳሙ. 21:171ነገ 11:36፤ 15:4፤ 2ነገ 8:19
2 ሳሙ. 21:181ዜና 20:4
2 ሳሙ. 21:181ዜና 11:26, 29፤ 27:1, 11
2 ሳሙ. 21:18ዘፍ 14:5
2 ሳሙ. 21:191ዜና 20:5
2 ሳሙ. 21:191ሳሙ 17:4, 7
2 ሳሙ. 21:201ዜና 20:6-8
2 ሳሙ. 21:211ሳሙ 17:10, 45፤ 2ነገ 19:22
2 ሳሙ. 21:211ሳሙ 16:9፤ 17:13፤ 1ዜና 2:13
2 ሳሙ. 21:22መዝ 60:12
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ሳሙኤል 21:1-22

ሁለተኛ ሳሙኤል

21 በዳዊት ዘመን ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ረሃብ ሆነ፤+ ስለዚህ ዳዊት ይሖዋን ምክር ጠየቀ፤ ይሖዋም “ሳኦል ገባኦናውያንን ስለገደለ እሱም ሆነ ቤቱ የደም ዕዳ አለባቸው” አለ።+ 2 በመሆኑም ንጉሡ ገባኦናውያንን+ ጠርቶ አነጋገራቸው። (እርግጥ ገባኦናውያን ከአሞራውያን+ የተረፉ ናቸው እንጂ እስራኤላውያን አልነበሩም፤ እስራኤላውያንም እንደማያጠፏቸው ምለውላቸው ነበር፤+ ይሁንና ሳኦል ለእስራኤልና ለይሁዳ ሕዝብ ባለው ቅንዓት ተነሳስቶ ሊያጠፋቸው ፈልጎ ነበር።) 3 ዳዊትም ገባኦናውያንን “የይሖዋን ርስት እንድትባርኩ ምን ላድርግላችሁ? ማስተሰረይስ የምችለው እንዴት ነው?” አላቸው። 4 ገባኦናውያንም “ከሳኦልና ከእሱ ቤት ጋር በተያያዘ የተፈጠረው ችግር በብርና በወርቅ የሚፈታ አይደለም፤+ ደግሞም በእስራኤል ውስጥ ማንንም ሰው የመግደል መብት የለንም” አሉት። በዚህ ጊዜ ዳዊት “ያላችሁትን ሁሉ አደርግላችኋለሁ” አላቸው። 5 እነሱም ንጉሡን እንዲህ አሉት፦ “ለጥፋት ከዳረገንና በየትኛውም የእስራኤል ግዛት ውስጥ እንዳንኖር እኛን ለመደምሰስ ሴራ ከጠነሰሰብን ሰው+ 6 ወንዶች ልጆች መካከል ሰባቱ ይሰጡን። እኛም በይሖዋ የተመረጠው የሳኦል+ አገር በሆነችው በጊብዓ+ በድናቸውን በይሖዋ ፊት እንሰቅላለን።”*+ ከዚያም ንጉሡ “እሺ፣ እሰጣችኋለሁ” አላቸው።

7 ሆኖም ንጉሡ እሱና የሳኦል ልጅ ዮናታን በይሖዋ ፊት በተማማሉት መሐላ የተነሳ የሳኦል ልጅ ለሆነው ለዮናታን+ ልጅ ለሜፊቦስቴ+ ራራለት። 8 በመሆኑም ንጉሡ የአያ ልጅ ሪጽፋ+ ለሳኦል የወለደችለትን ሁለት ወንዶች ልጆች ማለትም አርሞኒንና ሜፊቦስቴን እንዲሁም የሳኦል ልጅ ሜልኮል*+ የመሆላታዊው የቤርዜሊ ልጅ ለሆነው ለአድሪዔል+ የወለደችለትን አምስት ወንዶች ልጆች ወሰደ። 9 ከዚያም ለገባኦናውያኑ አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነሱም በድናቸውን በተራራው ላይ በይሖዋ ፊት ሰቀሉ።+ ሰባቱም አንድ ላይ ሞቱ፤ የተገደሉትም አዝመራ በሚሰበሰብባቸው የመጀመሪያዎቹ ቀናት ይኸውም የገብስ አዝመራ መሰብሰብ በሚጀምርበት ጊዜ ነበር። 10 ከዚያም የአያ ልጅ ሪጽፋ+ ከመከር ወቅት መጀመሪያ አንስቶ በበድኖቹ ላይ ከሰማይ ዝናብ እስከሚወርድበት ጊዜ ድረስ ማቅ ወስዳ በዓለቱ ላይ አነጠፈች፤ ቀን የሰማይ አሞሮች እንዲያርፉባቸው፣ ሌሊት ደግሞ የዱር አራዊት እንዲጠጓቸው አልፈቀደችም።

11 በኋላም የሳኦል ቁባት የሆነችው የአያ ልጅ ሪጽፋ ያደረገችው ነገር ለዳዊት ተነገረው። 12 ስለዚህ ዳዊት ሄዶ የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን አፅም ከኢያቢስጊልያድ+ መሪዎች* ላይ ወሰደ፤ እነዚህ ሰዎች አፅሙን ፍልስጤማውያን ሳኦልን በጊልቦአ+ በገደሉበት ቀን እሱንና ዮናታንን ከሰቀሉበት ከቤትሻን አደባባይ ሰርቀው ወስደው ነበር። 13 እሱም የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን አፅም ከዚያ አመጣ፤ በተጨማሪም የተገደሉትን* ሰዎች አፅም ሰበሰቡ።+ 14 ከዚያም የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን አፅም በቢንያም ምድር በጸላ+ በሚገኘው በሳኦል አባት በቂስ+ የመቃብር ስፍራ ቀበሩት። ንጉሡ ያዘዘውን ነገር ሁሉ ከፈጸሙም በኋላ አምላክ ስለ ምድሪቱ ያቀረቡትን ልመና ሰማ።+

15 በፍልስጤማውያንና በእስራኤላውያን መካከል እንደገና ጦርነት ተነሳ።+ በመሆኑም ዳዊትና አገልጋዮቹ ወርደው ፍልስጤማውያንን ወጉ፤ በዚህ ጊዜ ዳዊት ዛለ። 16 ከረፋይም+ ዘር የሆነው እንዲሁም 300 ሰቅል*+ የሚመዝን የመዳብ ጦርና አዲስ ሰይፍ የታጠቀው ይሽቢብኖብ ዳዊትን ለመግደል አሰበ። 17 የጽሩያ ልጅ አቢሳም+ ወዲያውኑ ደረሰለት፤+ ፍልስጤማዊውንም መትቶ ገደለው። በዚያን ጊዜ የዳዊት ሰዎች “ከአሁን በኋላ ከእኛ ጋር ወደ ውጊያ መውጣት የለብህም!+ የእስራኤልን መብራት አታጥፋ!”+ በማለት ማሉለት።

18 ከዚህም በኋላ እንደገና ከፍልስጤማውያን ጋር በጎብ ጦርነት ተከፈተ።+ በዚህ ጊዜ ሁሻዊው ሲበካይ+ የረፋይም+ ዘር የሆነውን ሳፍን ገደለው።

19 ዳግመኛም ከፍልስጤማውያን ጋር በጎብ ጦርነት ተቀሰቀሰ፤+ የቤተልሔማዊው የያአሬዖርጊም ልጅ ኤልሃናን የሸማኔ መጠቅለያ የሚመስል ዘንግ ያለው ጦር ይዞ የነበረውን ጌታዊውን ጎልያድን ገደለው።+

20 እንደገናም በጌት ጦርነት ተቀሰቀሰ፤ በዚያም በእጆቹ ላይ ስድስት ስድስት ጣቶች በእግሮቹም ላይ ስድስት ስድስት ጣቶች፣ በድምሩ 24 ጣቶች ያሉት በጣም ግዙፍ የሆነ ሰው ነበር፤ እሱም የረፋይም ዘር ነበር።+ 21 ይህ ሰው እስራኤልን ይገዳደር+ ስለነበር የዳዊት ወንድም የሺምአይ+ ልጅ ዮናታን ገደለው።

22 እነዚህ አራቱ በጌት የሚኖሩ የረፋይም ዘሮች ነበሩ፤ እነሱም በዳዊት እጅና በአገልጋዮቹ እጅ ወደቁ።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ