የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ቆሮንቶስ 3
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ቆሮንቶስ የመጽሐፉ ይዘት

      • የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ገና ሥጋውያን ናቸው (1-4)

      • ‘የሚያሳድገው አምላክ ነው’ (5-9)

        • “ከአምላክ ጋር አብረን የምንሠራ ነን” (9)

      • እሳትን መቋቋም በሚችሉ ነገሮች መገንባት (10-15)

      • ‘የአምላክ ቤተ መቅደስ ናችሁ’ (16, 17)

      • የዓለም ጥበብ በአምላክ ዘንድ ሞኝነት ነው (18-23)

1 ቆሮንቶስ 3:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 14:20
  • +1ቆሮ 2:15፤ ቆላ 1:9

1 ቆሮንቶስ 3:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕብ 5:12-14

1 ቆሮንቶስ 3:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 8:7, 8
  • +ገላ 5:19, 20

1 ቆሮንቶስ 3:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 18:24, 25

1 ቆሮንቶስ 3:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 3:5, 6፤ ቆላ 1:23፤ 1ጢሞ 1:12

1 ቆሮንቶስ 3:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 18:4
  • +ሥራ 18:26-28፤ 19:1

1 ቆሮንቶስ 3:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 9:16

1 ቆሮንቶስ 3:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “አንድ ናቸው።” ወይም “አንድ ዓላማ አላቸው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 2:6፤ 1ቆሮ 4:5፤ ራእይ 22:12

1 ቆሮንቶስ 3:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤፌ 2:22፤ 1ጴጥ 2:5

1 ቆሮንቶስ 3:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በሙያው እንደተካነ መሐንዲስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 15:20፤ ዕብ 6:1

1 ቆሮንቶስ 3:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 118:22፤ ኢሳ 28:16፤ ማቴ 21:42፤ ኤፌ 2:20፤ 1ጴጥ 2:6

1 ቆሮንቶስ 3:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ጴጥ 4:12

1 ቆሮንቶስ 3:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 6:16፤ ኤፌ 2:21፤ 1ጴጥ 2:5
  • +1ቆሮ 6:19

1 ቆሮንቶስ 3:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ጴጥ 2:5

1 ቆሮንቶስ 3:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በዚህ ዘመን።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

1 ቆሮንቶስ 3:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዮብ 5:13

1 ቆሮንቶስ 3:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 94:11

1 ቆሮንቶስ 3:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ጴጥሮስ ተብሎም ይጠራል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 1:12

1 ቆሮንቶስ 3:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 17:9፤ 2ቆሮ 10:7

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ቆሮ. 3:11ቆሮ 14:20
1 ቆሮ. 3:11ቆሮ 2:15፤ ቆላ 1:9
1 ቆሮ. 3:2ዕብ 5:12-14
1 ቆሮ. 3:3ሮም 8:7, 8
1 ቆሮ. 3:3ገላ 5:19, 20
1 ቆሮ. 3:4ሥራ 18:24, 25
1 ቆሮ. 3:52ቆሮ 3:5, 6፤ ቆላ 1:23፤ 1ጢሞ 1:12
1 ቆሮ. 3:6ሥራ 18:4
1 ቆሮ. 3:6ሥራ 18:26-28፤ 19:1
1 ቆሮ. 3:7ሮም 9:16
1 ቆሮ. 3:8ሮም 2:6፤ 1ቆሮ 4:5፤ ራእይ 22:12
1 ቆሮ. 3:9ኤፌ 2:22፤ 1ጴጥ 2:5
1 ቆሮ. 3:10ሮም 15:20፤ ዕብ 6:1
1 ቆሮ. 3:11መዝ 118:22፤ ኢሳ 28:16፤ ማቴ 21:42፤ ኤፌ 2:20፤ 1ጴጥ 2:6
1 ቆሮ. 3:131ጴጥ 4:12
1 ቆሮ. 3:162ቆሮ 6:16፤ ኤፌ 2:21፤ 1ጴጥ 2:5
1 ቆሮ. 3:161ቆሮ 6:19
1 ቆሮ. 3:171ጴጥ 2:5
1 ቆሮ. 3:19ኢዮብ 5:13
1 ቆሮ. 3:20መዝ 94:11
1 ቆሮ. 3:221ቆሮ 1:12
1 ቆሮ. 3:23ዮሐ 17:9፤ 2ቆሮ 10:7
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ቆሮንቶስ 3:1-23

ለቆሮንቶስ ሰዎች የተጻፈ የመጀመሪያው ደብዳቤ

3 በመሆኑም ወንድሞች፣ ከክርስቶስ ጋር በተያያዘ ገና ሕፃናት+ እንደሆኑ እንደ ሥጋውያን ሰዎች እንጂ እንደ መንፈሳውያን ሰዎች+ ላነጋግራችሁ አልቻልኩም። 2 ጠንካራ ስላልነበራችሁ ወተት እንጂ ጠንካራ ምግብ አልመገብኳችሁም። አሁንም ቢሆን ገና አልጠነከራችሁም፤+ 3 ደግሞም ገና ሥጋውያን ናችሁ።+ ቅናትና ጠብ በመካከላችሁ ስላለ ሥጋውያን መሆናችሁ፣+ ደግሞም በዓለም እንዳሉ ሰዎች መመላለሳችሁ አይደለም? 4 አንዱ “እኔ የጳውሎስ ነኝ፣” ሌላው ደግሞ “እኔ የአጵሎስ+ ነኝ” ሲል እንደ ማንኛውም ሰው መሆናችሁ አይደለም?

5 ለመሆኑ አጵሎስ ምንድን ነው? ጳውሎስስ ምንድን ነው? ጌታ የሰጣቸውን ሥራ የሚያከናውኑ አገልጋዮች+ ናቸው፤ እናንተም አማኞች የሆናችሁት በእነሱ አማካኝነት ነው። 6 እኔ ተከልኩ፤+ አጵሎስ አጠጣ፤+ ያሳደገው ግን አምላክ ነው፤ 7 ስለዚህ ምስጋና የሚገባው የሚያሳድገው አምላክ እንጂ የሚተክለውም ሆነ የሚያጠጣው አይደለም።+ 8 የሚተክለውም ሆነ የሚያጠጣው በኅብረት የሚሠሩ ናቸው፤* ሆኖም እያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው መጠን የራሱን ወሮታ ይቀበላል።+ 9 እኛ ከአምላክ ጋር አብረን የምንሠራ ነንና። እናንተ በመልማት ላይ ያለ የአምላክ እርሻ ናችሁ፤ የአምላክ ሕንፃ ናችሁ።+

10 በተሰጠኝ የአምላክ ጸጋ መሠረት በሙያው እንደተካነ ግንበኛ* እኔ መሠረት ጣልኩ፤+ ሌላው ደግሞ በዚያ ላይ ይገነባል። ሆኖም እያንዳንዱ በዚያ ላይ እንዴት እንደሚገነባ በጥንቃቄ ሊያስብ ይገባል። 11 ማንም ሰው ከተጣለው መሠረት ሌላ አዲስ መሠረት መጣል አይችልምና፤ ይህም መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።+ 12 ማንም በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ፣ በብር፣ በከበሩ ድንጋዮች፣ በእንጨት፣ በሣር ወይም በአገዳ ቢገነባ 13 የፈተናው ቀን ሲመጣ የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤ እሳቱ+ ሁሉንም ነገር ይገልጣልና፤ እንዲሁም እያንዳንዱ ሰው ምን ዓይነት ግንባታ እንዳከናወነ እሳቱ ራሱ ፈትኖ ያሳያል። 14 ማንም በመሠረቱ ላይ የገነባው ነገር ቢጸናለት ወሮታ ያገኛል፤ 15 ይሁንና ማንም ሰው የሠራው ሥራ ቢቃጠል ኪሳራ ይደርስበታል፤ እሱ ግን ይተርፋል፤ ሆኖም በእሳት ውስጥ አልፎ የመትረፍ ያህል ይሆናል።

16 እናንተ ራሳችሁ የአምላክ ቤተ መቅደስ+ እንደሆናችሁና የአምላክ መንፈስ በእናንተ ውስጥ እንደሚያድር አታውቁም?+ 17 ማንም የአምላክን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ አምላክ ያፈርሰዋል፤ የአምላክ ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፤ ቤተ መቅደሱም እናንተ ናችሁ።+

18 ማንም ራሱን አያታል፤ ከእናንተ መካከል ማንም በዚህ ሥርዓት* ጥበበኛ እንደሆነ ቢያስብ፣ ጥበበኛ መሆን ይችል ዘንድ ሞኝ ይሁን። 19 ምክንያቱም የዚህ ዓለም ጥበብ በአምላክ ፊት ሞኝነት ነው፤ “ጥበበኞችን በራሳቸው ተንኮል ይይዛቸዋል” ተብሎ ተጽፏልና።+ 20 ደግሞም “ይሖዋ* የጥበበኞች ሐሳብ ከንቱ እንደሆነ ያውቃል” ተብሏል።+ 21 በመሆኑም ማንም በሰዎች አይኩራራ፤ ሁሉም ነገር የእናንተ ነውና፤ 22 ጳውሎስም ቢሆን አጵሎስም ቢሆን ኬፋም*+ ቢሆን ዓለምም ቢሆን ሕይወትም ቢሆን ሞትም ቢሆን አሁን ያሉት ነገሮችም ቢሆኑ የሚመጡትም ነገሮች ቢሆኑ ሁሉም ነገር የእናንተ ነው፤ 23 እናንተም የክርስቶስ ናችሁ፤+ ክርስቶስ ደግሞ የአምላክ ነው።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ