የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፀአት 37
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘፀአት የመጽሐፉ ይዘት

      • የታቦቱ አሠራር (1-9)

      • ጠረጴዛው (10-16)

      • መቅረዙ (17-24)

      • የዕጣን መሠዊያው (25-29)

ዘፀአት 37:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አንድ ክንድ 44.5 ሴንቲ ሜትር ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 31:2-5፤ 38:22
  • +ዘፀ 40:3፤ ዘኁ 10:33
  • +ዘፀ 25:10-15

ዘፀአት 37:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕብ 9:4

ዘፀአት 37:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 5:9

ዘፀአት 37:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 3:8

ዘፀአት 37:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 16:2, 14፤ 1ዜና 28:11
  • +ዘፀ 25:17-20

ዘፀአት 37:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 40:20
  • +ዘፍ 3:24

ዘፀአት 37:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕብ 9:5
  • +1ሳሙ 4:4፤ መዝ 80:1

ዘፀአት 37:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 40:4
  • +ዘፀ 25:23-28

ዘፀአት 37:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አንድ ጋት 7.4 ሴንቲ ሜትር ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

ዘፀአት 37:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 25:29

ዘፀአት 37:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 40:24፤ ዘሌ 24:4፤ 2ዜና 13:11
  • +ዘፀ 25:31-39

ዘፀአት 37:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 8:2

ዘፀአት 37:24

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አንድ ታላንት 34.2 ኪሎ ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

ዘፀአት 37:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 30:7፤ 40:5፤ መዝ 141:2፤ ራእይ 8:3
  • +ዘፀ 30:1-5

ዘፀአት 37:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 30:25, 33፤ 40:9
  • +ዘፀ 30:34, 35፤ መዝ 141:2

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘፀ. 37:1ዘፀ 31:2-5፤ 38:22
ዘፀ. 37:1ዘፀ 40:3፤ ዘኁ 10:33
ዘፀ. 37:1ዘፀ 25:10-15
ዘፀ. 37:2ዕብ 9:4
ዘፀ. 37:42ዜና 5:9
ዘፀ. 37:5ኢያሱ 3:8
ዘፀ. 37:6ዘሌ 16:2, 14፤ 1ዜና 28:11
ዘፀ. 37:6ዘፀ 25:17-20
ዘፀ. 37:7ዘፀ 40:20
ዘፀ. 37:7ዘፍ 3:24
ዘፀ. 37:9ዕብ 9:5
ዘፀ. 37:91ሳሙ 4:4፤ መዝ 80:1
ዘፀ. 37:10ዘፀ 40:4
ዘፀ. 37:10ዘፀ 25:23-28
ዘፀ. 37:16ዘፀ 25:29
ዘፀ. 37:17ዘፀ 40:24፤ ዘሌ 24:4፤ 2ዜና 13:11
ዘፀ. 37:17ዘፀ 25:31-39
ዘፀ. 37:23ዘኁ 8:2
ዘፀ. 37:25ዘፀ 30:7፤ 40:5፤ መዝ 141:2፤ ራእይ 8:3
ዘፀ. 37:25ዘፀ 30:1-5
ዘፀ. 37:29ዘፀ 30:25, 33፤ 40:9
ዘፀ. 37:29ዘፀ 30:34, 35፤ መዝ 141:2
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘፀአት 37:1-29

ዘፀአት

37 ከዚያም ባስልኤል+ ከግራር እንጨት ታቦቱን+ ሠራ። ርዝመቱ ሁለት ክንድ* ተኩል፣ ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል፣ ከፍታው ደግሞ አንድ ክንድ ተኩል ነበር።+ 2 ውስጡንና ውጭውንም በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ ሠራለት።+ 3 ከአራቱ እግሮቹ በላይ የሚሆኑ አራት የወርቅ ቀለበቶችን ሠራለት፤ ሁለቱን ቀለበቶች በአንድ ጎኑ፣ ሁለቱን ቀለበቶች ደግሞ በሌላኛው ጎኑ በኩል አደረጋቸው። 4 ከዚያም ከግራር እንጨት መሎጊያዎችን ሠራ፤ በወርቅም ለበጣቸው።+ 5 ታቦቱንም ለመሸከም እንዲያገለግሉ መሎጊያዎቹን በታቦቱ ጎንና ጎን ባሉት ቀለበቶች ውስጥ አስገባቸው።+

6 እሱም ከንጹሕ ወርቅ መክደኛውን ሠራ።+ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል ወርዱ ደግሞ አንድ ክንድ ተኩል ነበር።+ 7 በተጨማሪም በመክደኛው+ ጫፍና ጫፍ ላይ ከተጠፈጠፈ ወርቅ ሁለት ኪሩቦችን+ ሠራ። 8 አንዱ ኪሩብ በአንዱ ጫፍ ሌላኛው ኪሩብ ደግሞ በሌላኛው ጫፍ ላይ ነበር። ኪሩቦቹን በሁለቱም የመክደኛው ጫፎች ላይ ሠራቸው። 9 ሁለቱ ኪሩቦችም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ በመዘርጋት መክደኛውን በክንፎቻቸው ከልለውት ነበር።+ እርስ በርስ ትይዩ ነበሩ፤ ፊታቸውንም ወደ መክደኛው አጎንብሰው ነበር።+

10 ከዚያም ከግራር እንጨት ጠረጴዛውን ሠራ።+ ርዝመቱ ሁለት ክንድ፣ ወርዱ አንድ ክንድ ከፍታው ደግሞ አንድ ክንድ ተኩል ነበር።+ 11 በንጹሕ ወርቅም ለበጠው፤ ዙሪያውንም የወርቅ ክፈፍ ሠራለት። 12 ከዚያም በዙሪያው አንድ ጋት* ስፋት ያለው ጠርዝ ሠራለት፤ ለጠርዙም ዙሪያውን የወርቅ ክፈፍ ሠራለት። 13 በተጨማሪም አራት የወርቅ ቀለበቶች ሠራለት፤ ቀለበቶቹንም አራቱ እግሮቹ በሚገኙባቸው አራት ማዕዘኖች ላይ አደረጋቸው። 14 ጠረጴዛውን ለመሸከም የሚያገለግሉትን መሎጊያዎች የሚይዙት ቀለበቶች በጠርዙ አጠገብ ነበሩ። 15 ከዚያም ጠረጴዛውን ለመሸከም የሚያገለግሉትን መሎጊያዎች ከግራር እንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው። 16 በኋላም በጠረጴዛው ላይ የሚሆኑትን ዕቃዎች ይኸውም ሳህኖቹንና ጽዋዎቹን እንዲሁም ለመጠጥ መባ ማፍሰሻ የሚያገለግሉትን ጎድጓዳ ሳህኖቹንና ማንቆርቆሪያዎቹን ከንጹሕ ወርቅ ሠራ።+

17 ከዚያም መቅረዙን ከንጹሕ ወርቅ ሠራ።+ መቅረዙን ጠፍጥፎ ሠራው። የመቅረዙ መቆሚያ፣ ግንዱ፣ አበባ አቃፊዎቹ፣ እንቡጦቹና የፈኩት አበቦች ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ።+ 18 መቅረዙ ከግንዱ ላይ የወጡ ስድስት ቅርንጫፎች ነበሩት፤ ሦስቱ ቅርንጫፎቹ ከአንዱ ጎን ሦስቱ ቅርንጫፎቹ ደግሞ ከሌላው ጎን የወጡ ነበሩ። 19 በአንዱ በኩል ባሉት ቅርንጫፎች በእያንዳንዳቸው ላይ የአልሞንድ አበባ የሚመስሉ ሦስት የአበባ አቃፊዎች ከእንቡጦችና ከፈኩ አበቦች ጋር በማፈራረቅ ተሠርተው ነበር፤ በሌላኛው በኩል ባሉት ቅርንጫፎችም በእያንዳንዳቸው ላይ የአልሞንድ አበባ የሚመስሉ ሦስት የአበባ አቃፊዎች ከእንቡጦችና ከፈኩ አበቦች ጋር በማፈራረቅ ተሠርተው ነበር። ከመቅረዙ ግንድ በሚወጡት ስድስት ቅርንጫፎች ላይ የተደረገው ይህ ነበር። 20 በመቅረዙም ግንድ ላይ የአልሞንድ አበባ የሚመስሉ አራት የአበባ አቃፊዎች ከእንቡጦችና ከፈኩ አበቦች ጋር በማፈራረቅ ተሠርተው ነበር። 21 ከግንዱ በሚወጡት በመጀመሪያዎቹ ጥንድ ቅርንጫፎች ሥር አንድ እንቡጥ፣ ቀጥሎ ባሉት ጥንድ ቅርንጫፎች ሥር አንድ እንቡጥ እንዲሁም ቀጥሎ ባሉት ጥንድ ቅርንጫፎች ሥር አንድ እንቡጥ ነበር፤ ከመቅረዙ ግንድ ለሚወጡት ስድስት ቅርንጫፎች እንዲሁ ተደርጎላቸው ነበር። 22 እንቡጦቹም ሆኑ ቅርንጫፎቹ፣ መላው መቅረዙ ከንጹሕ ወርቅ ተጠፍጥፎ ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበር። 23 ከዚያም ሰባቱን መብራቶች+ እንዲሁም መቆንጠጫዎቹንና መኮስተሪያዎቹን ከንጹሕ ወርቅ ሠራ። 24 መቅረዙን ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋር የሠራው ከአንድ ታላንት* ንጹሕ ወርቅ ነበር።

25 ከዚያም ከግራር እንጨት የዕጣን መሠዊያውን+ ሠራ። ርዝመቱ አንድ ክንድ፣ ወርዱ አንድ ክንድ ሆኖ አራቱም ጎኖቹ እኩል ሲሆኑ ከፍታው ደግሞ ሁለት ክንድ ነበር። ቀንዶቹ ከዚያው ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ።+ 26 እሱም ላዩን፣ ሁሉንም ጎኖቹን እንዲሁም ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ ሠራለት። 27 መሠዊያውን ለመሸከም የሚያገለግሉትን መሎጊያዎች እንዲይዙም በሁለቱ ተቃራኒ ጎኖቹ ላይ ከክፈፉ በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠራለት። 28 ከዚያ በኋላ መሎጊያዎቹን ከግራር እንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው። 29 በተጨማሪም ቅዱሱን የቅብዓት ዘይትና+ በብልሃት የተቀመመውን ጥሩ መዓዛ ያለውን ንጹሕ ዕጣን+ አዘጋጀ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ