የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ዜና መዋዕል 17
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ዜና መዋዕል የመጽሐፉ ይዘት

      • ዳዊት ቤተ መቅደሱን እንደማይሠራ ተነገረው (1-6)

      • ለዳዊት የመንግሥት ቃል ኪዳን ተገባለት (7-15)

      • ዳዊት ያቀረበው የምስጋና ጸሎት (16-27)

1 ዜና መዋዕል 17:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 1:8፤ 1ዜና 29:29
  • +2ሳሙ 7:1-3፤ 1ዜና 15:1፤ 2ዜና 1:4
  • +1ዜና 14:1

1 ዜና መዋዕል 17:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 7:4-7፤ 1ነገ 8:17-19፤ 1ዜና 22:7, 8

1 ዜና መዋዕል 17:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ከአንዱ የድንኳን ስፍራ ወደ ሌላው፣ ከአንዱም የመኖርያ ቦታ ወደ ሌላው” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 40:2፤ ዘኁ 4:24, 25፤ 2ሳሙ 6:17፤ መዝ 78:60

1 ዜና መዋዕል 17:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 16:11, 12፤ 17:15፤ 25:30፤ 2ሳሙ 7:8-11፤ መዝ 78:70, 71

1 ዜና መዋዕል 17:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 18:14፤ 2ሳሙ 8:6
  • +1ሳሙ 25:29፤ 26:10፤ መዝ 89:20, 22
  • +1ሳሙ 18:30

1 ዜና መዋዕል 17:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “አያደክሟቸውም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 2:23

1 ዜና መዋዕል 17:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሥርወ መንግሥት እንደሚያቋቁምልህ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 2:16
  • +መዝ 18:40

1 ዜና መዋዕል 17:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 8:20፤ መዝ 132:11
  • +2ሳሙ 7:12-17፤ 1ነገ 9:5፤ 1ዜና 28:5፤ ኤር 23:5

1 ዜና መዋዕል 17:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 5:5፤ 1ዜና 22:10
  • +መዝ 89:3, 4፤ ኢሳ 9:7፤ ዳን 2:44

1 ዜና መዋዕል 17:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 7:14፤ ሉቃስ 9:35፤ ዕብ 1:5
  • +1ሳሙ 15:24, 28፤ 1ዜና 10:13, 14
  • +ኢሳ 55:3

1 ዜና መዋዕል 17:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዳን 2:44፤ ዮሐ 1:49፤ 2ጴጥ 1:11
  • +መዝ 89:36፤ ኤር 33:20, 21፤ ሉቃስ 1:32, 33፤ ዕብ 1:8፤ ራእይ 3:21

1 ዜና መዋዕል 17:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 7:8, 18-20

1 ዜና መዋዕል 17:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ትልቅ ቦታ እንዳለው ሰው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 22:42፤ ሥራ 13:34፤ ራእይ 22:16

1 ዜና መዋዕል 17:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 139:1

1 ዜና መዋዕል 17:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከፈቃድህ ጋር በሚስማማ ሁኔታ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 7:21-24

1 ዜና መዋዕል 17:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 15:11
  • +ኢሳ 43:10

1 ዜና መዋዕል 17:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 4:7፤ መዝ 147:20
  • +ዘፀ 19:5፤ መዝ 77:15
  • +ዘዳ 7:1፤ ኢያሱ 10:42፤ 21:44
  • +ዘዳ 4:34፤ ነህ 9:10፤ ኢሳ 63:12፤ ሕዝ 20:9

1 ዜና መዋዕል 17:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 12:22
  • +ዘፍ 17:7፤ ዘዳ 7:6, 9

1 ዜና መዋዕል 17:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 7:25-29

1 ዜና መዋዕል 17:24

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የታመነ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 6:33፤ መዝ 72:19፤ ማቴ 6:9፤ ዮሐ 12:28
  • +መዝ 89:35, 36

1 ዜና መዋዕል 17:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሥርወ መንግሥት የማቋቋም።”

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ዜና 17:11ነገ 1:8፤ 1ዜና 29:29
1 ዜና 17:12ሳሙ 7:1-3፤ 1ዜና 15:1፤ 2ዜና 1:4
1 ዜና 17:11ዜና 14:1
1 ዜና 17:42ሳሙ 7:4-7፤ 1ነገ 8:17-19፤ 1ዜና 22:7, 8
1 ዜና 17:5ዘፀ 40:2፤ ዘኁ 4:24, 25፤ 2ሳሙ 6:17፤ መዝ 78:60
1 ዜና 17:71ሳሙ 16:11, 12፤ 17:15፤ 25:30፤ 2ሳሙ 7:8-11፤ መዝ 78:70, 71
1 ዜና 17:81ሳሙ 18:14፤ 2ሳሙ 8:6
1 ዜና 17:81ሳሙ 25:29፤ 26:10፤ መዝ 89:20, 22
1 ዜና 17:81ሳሙ 18:30
1 ዜና 17:9ዘፀ 2:23
1 ዜና 17:10መሳ 2:16
1 ዜና 17:10መዝ 18:40
1 ዜና 17:111ነገ 8:20፤ መዝ 132:11
1 ዜና 17:112ሳሙ 7:12-17፤ 1ነገ 9:5፤ 1ዜና 28:5፤ ኤር 23:5
1 ዜና 17:121ነገ 5:5፤ 1ዜና 22:10
1 ዜና 17:12መዝ 89:3, 4፤ ኢሳ 9:7፤ ዳን 2:44
1 ዜና 17:132ሳሙ 7:14፤ ሉቃስ 9:35፤ ዕብ 1:5
1 ዜና 17:131ሳሙ 15:24, 28፤ 1ዜና 10:13, 14
1 ዜና 17:13ኢሳ 55:3
1 ዜና 17:14ዳን 2:44፤ ዮሐ 1:49፤ 2ጴጥ 1:11
1 ዜና 17:14መዝ 89:36፤ ኤር 33:20, 21፤ ሉቃስ 1:32, 33፤ ዕብ 1:8፤ ራእይ 3:21
1 ዜና 17:162ሳሙ 7:8, 18-20
1 ዜና 17:17ማቴ 22:42፤ ሥራ 13:34፤ ራእይ 22:16
1 ዜና 17:18መዝ 139:1
1 ዜና 17:192ሳሙ 7:21-24
1 ዜና 17:20ዘፀ 15:11
1 ዜና 17:20ኢሳ 43:10
1 ዜና 17:21ዘዳ 4:7፤ መዝ 147:20
1 ዜና 17:21ዘፀ 19:5፤ መዝ 77:15
1 ዜና 17:21ዘዳ 7:1፤ ኢያሱ 10:42፤ 21:44
1 ዜና 17:21ዘዳ 4:34፤ ነህ 9:10፤ ኢሳ 63:12፤ ሕዝ 20:9
1 ዜና 17:221ሳሙ 12:22
1 ዜና 17:22ዘፍ 17:7፤ ዘዳ 7:6, 9
1 ዜና 17:232ሳሙ 7:25-29
1 ዜና 17:242ዜና 6:33፤ መዝ 72:19፤ ማቴ 6:9፤ ዮሐ 12:28
1 ዜና 17:24መዝ 89:35, 36
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ዜና መዋዕል 17:1-27

አንደኛ ዜና መዋዕል

17 ዳዊት በራሱ ቤት* መኖር እንደጀመረ ነቢዩ ናታንን+ “የይሖዋ የቃል ኪዳኑ ታቦት በድንኳን ውስጥ ተቀምጦ+ ሳለ ይኸው እኔ ከአርዘ ሊባኖስ+ በተሠራ ቤት ውስጥ እየኖርኩ ነው” አለው። 2 ናታንም ዳዊትን “እውነተኛው አምላክ ከአንተ ጋር ስለሆነ በልብህ ያለውን ነገር ሁሉ አድርግ” አለው።

3 በዚያው ሌሊት የአምላክ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ናታን መጣ፦ 4 “ሂድና አገልጋዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የምኖርበትን ቤት የምትሠራልኝ አንተ አይደለህም።+ 5 እስራኤልን ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ከአንዱ ድንኳን ወደ ሌላው ድንኳን፣ ከአንዱም የማደሪያ ድንኳን ወደ ሌላው የማደሪያ ድንኳን* እሄድ ነበር እንጂ በቤት ውስጥ አልኖርኩም።+ 6 ከመላው እስራኤል ጋር በተጓዝኩበት ጊዜ ሁሉ ሕዝቤን እረኛ ሆነው እንዲጠብቁ ከሾምኳቸው የእስራኤል ፈራጆች መካከል ‘በአርዘ ሊባኖስ፣ ቤት ያልሠራህልኝ ለምንድን ነው?’ ያልኩት ማን አለ?” ’

7 “አሁንም አገልጋዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ እንድትሆን መንጋ ከምትጠብቅበት ስፍራ ወሰድኩህ።+ 8 እኔም በምትሄድበት ሁሉ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤+ ጠላቶችህንም ሁሉ ከፊትህ አጠፋለሁ፤+ ስምህንም በምድር ላይ እንዳሉ ታላላቅ ሰዎች ስም አደርገዋለሁ።+ 9 ለሕዝቤ ለእስራኤል ቦታ እሰጣቸዋለሁ፤ ተረጋግተው እንዲቀመጡም አደርጋለሁ፤ በዚያም ይኖራሉ፤ ከእንግዲህም የሚረብሻቸው አይኖርም፤ ክፉዎችም እንደቀድሞው ዳግመኛ አይጨቁኗቸውም፤*+ 10 በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሳፍንትን ከሾምኩበት+ ጊዜ አንስቶ ሲያደርጉ እንደነበሩት አያደርጉባቸውም። ጠላቶቻችሁም ሁሉ እንዲገዙላችሁ አደርጋለሁ።+ በተጨማሪም ‘ይሖዋ ቤት እንደሚሠራልህ’* እነግርሃለሁ።

11 “ ‘ “የሕይወት ዘመንህ አብቅቶ ከአባቶችህ ጋር ለመሆን በምትሄድበት ጊዜ ከአንተ በኋላ ዘርህን ይኸውም ከወንዶች ልጆችህ መካከል አንዱን አስነሳለሁ፤+ ንግሥናውንም አጸናለሁ።+ 12 ቤት የሚሠራልኝ እሱ ነው፤+ እኔም ዙፋኑን ለዘላለም አጸናለሁ።+ 13 አባት እሆነዋለሁ፤ እሱም ልጄ ይሆናል።+ ታማኝ ፍቅሬንም ከአንተ በፊት ከነበረው ላይ እንደወሰድኩ+ ከእሱ ላይ አልወስድም።+ 14 በቤቴና በንጉሣዊ ግዛቴ ላይ ለዘላለም ጸንቶ እንዲኖር አደርገዋለሁ፤+ ዙፋኑም ለዘላለም ይዘልቃል።” ’ ”+

15 ናታንም ይህን ቃል ሁሉና ይህን ራእይ በሙሉ ለዳዊት ነገረው።

16 በዚህ ጊዜ ንጉሥ ዳዊት ገብቶ በይሖዋ ፊት ተቀመጠ፤ እንዲህም አለ፦ “ይሖዋ አምላክ ሆይ፣ ኧረ ለመሆኑ እኔ ማን ነኝ? እስከዚህ ድረስ ያደረስከኝስ ቤቴ ምን ስለሆነ ነው?+ 17 አምላክ ሆይ፣ ይህ ሳያንስ ስለ አገልጋይህ ቤት ገና ወደፊት የሚሆነውንም ነገር ተናገርክ፤+ ይሖዋ አምላክ ሆይ፣ ከዚህ በላይ ከፍ ከፍ ሊደረግ እንደሚገባ ሰው* አድርገህ ተመልክተኸኛል። 18 ስለሰጠኸኝ ክብር አገልጋይህ ዳዊት ከዚህ በላይ ምን ሊልህ ይችላል? አንተ አገልጋይህን በሚገባ ታውቀው የለ?+ 19 ይሖዋ ሆይ፣ ለአገልጋይህ ስትል፣ ከልብህ ጋር በሚስማማ ሁኔታ* ታላቅነትህን በመግለጥ እነዚህን ሁሉ ታላላቅ ነገሮች ፈጽመሃል።+ 20 ይሖዋ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ማንም የለም፤+ ከአንተ በቀር አምላክ የለም፤+ በጆሯችን የሰማነው ነገር ሁሉ ይህን ያረጋግጣል። 21 በምድር ላይ እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ ሌላ ብሔር ማን አለ?+ እውነተኛው አምላክ ሄዶ ሕዝቡ አድርጎ ዋጀው።+ ብሔራትን ከግብፅ ከዋጀኸው ሕዝብህ ፊት አባረህ+ ታላላቅና አስፈሪ ነገሮችን በመፈጸም ስምህን አስጠራህ።+ 22 ሕዝብህን እስራኤልን እስከ ወዲያኛው የራስህ ሕዝብ አደረግከው፤+ ይሖዋ ሆይ፣ አንተም አምላኩ ሆንክ።+ 23 አሁንም ይሖዋ ሆይ፣ አገልጋይህንና ቤቱን በተመለከተ የገባኸው ቃል እስከ ወዲያኛው የጸና ይሁን፤ ቃል እንደገባኸውም አድርግ።+ 24 ሰዎች ‘የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ለእስራኤል አምላክ ነው’ እንዲሉ ስምህ የጸና* ይሁን፤ ደግሞም ለዘላለም ከፍ ከፍ ይበል፤+ የአገልጋይህም የዳዊት ቤት በፊትህ የጸና ይሁን።+ 25 አምላኬ ሆይ፣ አንተ ለአገልጋይህ ቤት የመሥራት* ዓላማ እንዳለህ አሳውቀኸዋልና። አገልጋይህ ይህን ጸሎት በልበ ሙሉነት ወደ አንተ የሚያቀርበው በዚህ ምክንያት ነው። 26 አሁንም ይሖዋ ሆይ፣ እውነተኛው አምላክ አንተ ነህ፤ ለአገልጋይህም እነዚህን መልካም ነገሮች ለማድረግ ቃል ገብተህለታል። 27 በመሆኑም የአገልጋይህን ቤት እባክህ ባርክ፤ በፊትህም ለዘላለም የጸና ይሁን፤ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ቀድሞውንም ባርከኸዋልና፤ ለዘላለምም የተባረከ ይሆናል።”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ