የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ዜና መዋዕል 13
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ዜና መዋዕል የመጽሐፉ ይዘት

      • አቢያህ በይሁዳ ላይ ነገሠ (1-22)

        • አቢያህ ኢዮርብዓምን ድል አደረገ (3-20)

2 ዜና መዋዕል 13:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 15:1, 2

2 ዜና መዋዕል 13:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    1ነገ 15:2 እና 2ዜና 11:20-22 ላይ ማአካ ተብላም ተጠርታለች።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 11:20, 21
  • +ኢያሱ 18:28፤ 1ሳሙ 10:26
  • +1ነገ 15:6

2 ዜና መዋዕል 13:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የተመረጡ።”

  • *

    ቃል በቃል “የተመረጡ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 11:1

2 ዜና መዋዕል 13:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ዘላቂና የማይለወጥ ቃል ኪዳንን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 7:12, 13፤ 1ዜና 17:11, 14፤ ሉቃስ 1:32
  • +መዝ 89:28, 29
  • +ዘፍ 49:10፤ 2ሳሙ 7:8፤ መዝ 78:70, 71

2 ዜና መዋዕል 13:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 10:2
  • +1ነገ 11:26, 27፤ 12:20

2 ዜና መዋዕል 13:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 12:26, 28፤ 2ዜና 11:15

2 ዜና መዋዕል 13:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 11:14
  • +1ነገ 12:31, 33፤ 13:33

2 ዜና መዋዕል 13:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 11:16

2 ዜና መዋዕል 13:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ገጸ ኅብስቱን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 29:39
  • +ዘፀ 30:1
  • +ዘፀ 25:30
  • +ዘፀ 25:31
  • +ዘፀ 27:20

2 ዜና መዋዕል 13:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 10:9

2 ዜና መዋዕል 13:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 14:11፤ 18:31

2 ዜና መዋዕል 13:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የተመረጡ ተዋጊዎች።”

2 ዜና መዋዕል 13:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በመደገፋቸው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 18:1, 5፤ 1ዜና 5:20፤ 2ዜና 16:8፤ መዝ 22:5፤ 37:5፤ ናሆም 1:7

2 ዜና መዋዕል 13:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በዙሪያዋ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 12:28, 29
  • +ዮሐ 11:54

2 ዜና መዋዕል 13:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 25:38፤ 1ነገ 14:20፤ ሥራ 12:21-23

2 ዜና መዋዕል 13:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 17:17

2 ዜና መዋዕል 13:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ዘገባ፤ ሐተታ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 9:29፤ 12:15

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ዜና 13:11ነገ 15:1, 2
2 ዜና 13:22ዜና 11:20, 21
2 ዜና 13:2ኢያሱ 18:28፤ 1ሳሙ 10:26
2 ዜና 13:21ነገ 15:6
2 ዜና 13:32ዜና 11:1
2 ዜና 13:52ሳሙ 7:12, 13፤ 1ዜና 17:11, 14፤ ሉቃስ 1:32
2 ዜና 13:5መዝ 89:28, 29
2 ዜና 13:5ዘፍ 49:10፤ 2ሳሙ 7:8፤ መዝ 78:70, 71
2 ዜና 13:62ዜና 10:2
2 ዜና 13:61ነገ 11:26, 27፤ 12:20
2 ዜና 13:81ነገ 12:26, 28፤ 2ዜና 11:15
2 ዜና 13:92ዜና 11:14
2 ዜና 13:91ነገ 12:31, 33፤ 13:33
2 ዜና 13:102ዜና 11:16
2 ዜና 13:11ዘፀ 29:39
2 ዜና 13:11ዘፀ 30:1
2 ዜና 13:11ዘፀ 25:30
2 ዜና 13:11ዘፀ 25:31
2 ዜና 13:11ዘፀ 27:20
2 ዜና 13:12ዘኁ 10:9
2 ዜና 13:142ዜና 14:11፤ 18:31
2 ዜና 13:182ነገ 18:1, 5፤ 1ዜና 5:20፤ 2ዜና 16:8፤ መዝ 22:5፤ 37:5፤ ናሆም 1:7
2 ዜና 13:191ነገ 12:28, 29
2 ዜና 13:19ዮሐ 11:54
2 ዜና 13:201ሳሙ 25:38፤ 1ነገ 14:20፤ ሥራ 12:21-23
2 ዜና 13:21ዘዳ 17:17
2 ዜና 13:222ዜና 9:29፤ 12:15
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ዜና መዋዕል 13:1-22

ሁለተኛ ዜና መዋዕል

13 ንጉሥ ኢዮርብዓም በነገሠ በ18ኛው ዓመት አቢያህ በይሁዳ ላይ ነገሠ።+ 2 እሱም በኢየሩሳሌም ለሦስት ዓመት ገዛ። የእናቱ ስም ሚካያህ*+ ነበር፤ እሷም የጊብዓዊው+ የዑሪኤል ልጅ ነበረች። በአቢያህና በኢዮርብዓም መካከልም ጦርነት ነበር።+

3 በመሆኑም አቢያህ 400,000 የሠለጠኑ* ኃያላን ተዋጊዎችን ያቀፈ ሠራዊት ይዞ ዘመተ።+ ኢዮርብዓምም 800,000 የሠለጠኑ* ኃያላን ተዋጊዎችን አስከትሎ እሱን ለመግጠም ተሰለፈ። 4 አቢያህ በኤፍሬም ተራራማ ክልል በሚገኘው በጸማራይም ተራራ ላይ ቆሞ እንዲህ አለ፦ “ኢዮርብዓምና እስራኤላውያን ሁሉ፣ ስሙኝ። 5 የእስራኤል አምላክ ይሖዋ፣ ዳዊትና ልጆቹ+ በእስራኤል ላይ ለዘላለም እንዲነግሡ በጨው ቃል ኪዳን*+ መንግሥት እንደሰጣቸው አታውቁም?+ 6 የዳዊት ልጅ የሰለሞን አገልጋይ የነበረው የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም+ ግን ተነስቶ በጌታው ላይ ዓመፀ።+ 7 ሥራ ፈት የሆኑ የማይረቡ ሰዎችም ወደ እሱ ተሰበሰቡ። የሰለሞን ልጅ ሮብዓም ለጋ ወጣት በነበረበትና ልቡ በቀላሉ ይሸበር በነበረበት ጊዜም በእሱ ላይ በረቱበት፤ ሊቋቋማቸውም አልቻለም።

8 “አሁንም እናንተ እጅግ ብዙ ስለሆናችሁና ኢዮርብዓም አማልክት አድርጎ የሠራላችሁን የወርቅ ጥጃዎች+ ስለያዛችሁ በዳዊት ልጆች እጅ ያለውን የይሖዋን መንግሥት መቋቋም እንደምትችሉ ተሰምቷችኋል። 9 የአሮን ዘሮች የሆኑትን የይሖዋን ካህናትና ሌዋውያንን አላባረራችሁም?+ ደግሞስ እንደ ሌሎቹ አገሮች ሕዝቦች የራሳችሁን ካህናት አልሾማችሁም?+ አንድ ወይፈንና ሰባት አውራ በጎች ይዞ የሚመጣ ማንኛውም ሰው አማልክት ላልሆኑት ጣዖቶች ካህን መሆን ይችላል። 10 እኛ ግን አምላካችን ይሖዋ ነው፤+ እሱንም አልተውነውም፤ የአሮን ዘሮች የሆኑት ካህናት ይሖዋን እያገለገሉ ሲሆን ሌዋውያንም በሥራው ይረዷቸዋል። 11 በየጠዋቱና በየማታው+ ለይሖዋ የሚቃጠል መባ እንዲሁም ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን+ ያቀርባሉ፤ የሚነባበረውም ዳቦ*+ ከንጹሕ ወርቅ በተሠራው ጠረጴዛ ላይ ይቀመጣል፤ የወርቁን መቅረዝና+ መብራቶቹን በየማታው ያበራሉ፤+ ምክንያቱም እኛ በአምላካችን በይሖዋ ፊት ያለብንን ኃላፊነት እየተወጣን ነው፤ እናንተ ግን እሱን ትታችሁታል። 12 እነሆ፣ እውነተኛው አምላክ ከእኛ ጋር ነው፤ እሱም በእናንተ ላይ ጦርነት መታወጁን የሚያመለክት ድምፅ ለማሰማት መለከት ከያዙ ካህናቱ ጋር ሆኖ እየመራን ነው። የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ ስለማይሳካላችሁ ከአባቶቻችሁ አምላክ ከይሖዋ ጋር አትዋጉ።”+

13 ኢዮርብዓም ግን ከበስተ ጀርባቸው አድፍጠው ጥቃት የሚሰነዝሩ ተዋጊዎችን ላከ፤ ዋናው ሠራዊት ከፊት፣ ያደፈጡትም ተዋጊዎች ከበስተ ጀርባ ይሁዳን እንዲገጥሙ አደረገ። 14 የይሁዳ ሰዎች ዙሪያቸውን ሲመለከቱ ከፊትና ከኋላ መከበባቸውን አዩ። በዚህ ጊዜ ወደ ይሖዋ ጮኹ፤+ ካህናቱም መለከቶቹን በኃይል ነፉ። 15 የይሁዳ ሰዎች ቀረርቶ አሰሙ፤ የይሁዳ ሰዎች ቀረርቶ ባሰሙ ጊዜም እውነተኛው አምላክ ኢዮርብዓምንና እስራኤላውያንን ሁሉ በአቢያህና በይሁዳ ፊት ድል አደረጋቸው። 16 እስራኤላውያን ከይሁዳ ፊት ሸሹ፤ አምላክም በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው። 17 አቢያህና ሕዝቡም ፈጇቸው፤ ከእስራኤላውያንም መካከል 500,000 የሠለጠኑ ተዋጊዎች* ተገደሉ። 18 በዚህ ጊዜ የእስራኤል ሰዎች ተዋረዱ፤ የይሁዳ ሰዎች ግን በአባቶቻቸው አምላክ በይሖዋ በመታመናቸው* ድል ነሱ።+ 19 አቢያህ ኢዮርብዓምን አሳደደው፤ ከተሞቹን ይኸውም ቤቴልንና+ በሥሯ* ያሉትን ከተሞች፣ የሻናንና በሥሯ ያሉትን ከተሞች እንዲሁም ኤፍራይንንና+ በሥሯ ያሉትን ከተሞች ወሰደበት። 20 ኢዮርብዓምም በአቢያህ ዘመን እንደገና ሊያንሰራራ አልቻለም፤ ከዚያም ይሖዋ ስለቀሰፈው ሞተ።+

21 አቢያህ ግን እየበረታ ሄደ። ከጊዜ በኋላም 14 ሚስቶችን+ አግብቶ 22 ወንዶች ልጆችና 16 ሴቶች ልጆች ወለደ። 22 የቀረው የአቢያህ ታሪክ፣ የሠራውና የተናገረው ነገር ሁሉ በነቢዩ ኢዶ ጽሑፎች* ላይ ሰፍሯል።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ