የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ዜና መዋዕል 14
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ዜና መዋዕል የመጽሐፉ ይዘት

      • አቢያህ ሞተ (1)

      • አሳ በይሁዳ ላይ ነገሠ (2-8)

      • አሳ 1,000,000 ኢትዮጵያውያንን ድል አደረገ (9-15)

2 ዜና መዋዕል 14:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 5:9

2 ዜና መዋዕል 14:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 7:5
  • +ዘፀ 23:24
  • +1ነገ 14:22, 23፤ 2ነገ 18:1, 4

2 ዜና መዋዕል 14:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 34:1, 4

2 ዜና መዋዕል 14:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 11:5
  • +2ዜና 15:15፤ ምሳሌ 16:7

2 ዜና መዋዕል 14:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ሁለት ሳንቃዎች ያሏቸው በሮችና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 32:2, 5
  • +መዝ 127:1

2 ዜና መዋዕል 14:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አብዛኛውን ጊዜ ቀስተኞች የሚይዙት ትንሽ ጋሻ።

  • *

    ቃል በቃል “ደጋን የሚረግጡ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 11:1, 12፤ 13:3

2 ዜና መዋዕል 14:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 16:8
  • +ኢያሱ 15:20, 44፤ 2ዜና 11:5, 8

2 ዜና መዋዕል 14:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ተደግፈናልና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 14:10፤ 1ዜና 5:20፤ 2ዜና 32:20
  • +መሳ 7:7፤ 1ሳሙ 14:6
  • +2ዜና 13:12፤ 32:7, 8
  • +1ሳሙ 17:45፤ መዝ 20:5፤ ምሳሌ 18:10
  • +ኢያሱ 7:9፤ መዝ 9:19

2 ዜና መዋዕል 14:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:7

2 ዜና መዋዕል 14:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 20:1

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ዜና 14:12ሳሙ 5:9
2 ዜና 14:3ዘዳ 7:5
2 ዜና 14:3ዘፀ 23:24
2 ዜና 14:31ነገ 14:22, 23፤ 2ነገ 18:1, 4
2 ዜና 14:52ዜና 34:1, 4
2 ዜና 14:62ዜና 11:5
2 ዜና 14:62ዜና 15:15፤ ምሳሌ 16:7
2 ዜና 14:72ዜና 32:2, 5
2 ዜና 14:7መዝ 127:1
2 ዜና 14:82ዜና 11:1, 12፤ 13:3
2 ዜና 14:92ዜና 16:8
2 ዜና 14:9ኢያሱ 15:20, 44፤ 2ዜና 11:5, 8
2 ዜና 14:11ዘፀ 14:10፤ 1ዜና 5:20፤ 2ዜና 32:20
2 ዜና 14:11መሳ 7:7፤ 1ሳሙ 14:6
2 ዜና 14:112ዜና 13:12፤ 32:7, 8
2 ዜና 14:111ሳሙ 17:45፤ መዝ 20:5፤ ምሳሌ 18:10
2 ዜና 14:11ኢያሱ 7:9፤ መዝ 9:19
2 ዜና 14:12ዘዳ 28:7
2 ዜና 14:13ዘፍ 20:1
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ዜና መዋዕል 14:1-15

ሁለተኛ ዜና መዋዕል

14 በመጨረሻም አቢያህ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማም+ ቀበሩት፤ በምትኩም ልጁ አሳ ነገሠ። በእሱም ዘመን ምድሪቱ ለአሥር ዓመት አረፈች።

2 አሳ በአምላኩ በይሖዋ ፊት መልካምና ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ። 3 የባዕድ አማልክቱን መሠዊያዎችና+ ከፍ ያሉትን የማምለኪያ ቦታዎች አስወገደ፤ የማምለኪያ ዓምዶቹንም ሰባበረ፤+ እንዲሁም የማምለኪያ ግንዶቹን* ቆራረጠ።+ 4 በተጨማሪም የይሁዳ ሰዎች የአባቶቻቸውን አምላክ ይሖዋን እንዲፈልጉ እንዲሁም ሕጉንና ትእዛዙን እንዲያከብሩ አዘዘ። 5 ከይሁዳም ከተሞች ሁሉ ከፍ ያሉትን የማምለኪያ ቦታዎችና የዕጣን ማጨሻዎቹን አስወገደ፤+ መንግሥቱም በእሱ አገዛዝ ሥር ሰላም አገኘ። 6 ምድሪቱ እረፍት አግኝታ ስለነበር በይሁዳ የተመሸጉ ከተሞችን ገነባ፤+ ይሖዋ እረፍት ሰጥቶት ስለነበር በእነዚያ ዓመታት በእሱ ላይ ጦርነት የከፈተ አልነበረም።+ 7 የይሁዳንም ሰዎች እንዲህ አላቸው፦ “እነዚህን ከተሞች እንገንባ፤ በዙሪያቸውም ቅጥርና ማማዎች+ እንዲሁም በሮችና* መቀርቀሪያዎች እንሥራ። አምላካችንን ይሖዋን ስለፈለግነው ምድሪቱ አሁንም በእጃችን ናት። እኛ ፈልገነዋል፤ እሱም በዙሪያችን ካሉት ጠላቶቻችን ሁሉ እረፍት ሰጥቶናል።” በመሆኑም የግንባታ ሥራቸው ስኬታማ ሆነ።+

8 አሳ ትልቅ ጋሻና ጦር የታጠቁ 300,000 የይሁዳ ሰዎችን ያቀፈ ሠራዊት ነበረው። ከቢንያምም ነገድ ትንሽ ጋሻ* የሚያነግቡና ደጋን የሚይዙ* 280,000 ኃያላን ተዋጊዎች ነበሩ።+

9 ከጊዜ በኋላ ኢትዮጵያዊው ዛራ 1,000,000 ሰዎችንና 300 ሠረገሎችን ያቀፈ ሠራዊት አስከትሎ ዘመተባቸው።+ ማሬሻህ+ በደረሰ ጊዜ 10 አሳ ሊገጥመው ወጣ፤ በማሬሻህ በሚገኘው በጸፋታ ሸለቆም ለውጊያ ተሰለፉ። 11 በዚህ ጊዜ አሳ ወደ አምላኩ ወደ ይሖዋ እንዲህ ሲል ጮኸ፦+ “ይሖዋ ሆይ፣ የምትረዳው ሕዝብ ብዛት ያለውም ይሁን ደካማ ለአንተ የሚያመጣው ለውጥ የለም።+ ይሖዋ አምላካችን ሆይ፣ እርዳን፤ በአንተ ታምነናልና፤*+ በስምህ ይህን ታላቅ ሠራዊት ለመግጠም ወጥተናል።+ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ አምላካችን ነህ። ሟች የሆነ ሰው በአንተ ላይ አይበርታ።”+

12 በመሆኑም ይሖዋ ኢትዮጵያውያንን በአሳና በይሁዳ ፊት ድል አደረጋቸው፤ ኢትዮጵያውያኑም ሸሹ።+ 13 አሳና ከእሱ ጋር ያለው ሕዝብም እስከ ጌራራ+ ድረስ አሳደዷቸው፤ ኢትዮጵያውያኑም ፈጽመው እስኪጠፉ ድረስ ተመተው ወደቁ፤ በይሖዋና በሠራዊቱ ተደምስሰው ነበርና። በኋላም የይሁዳ ሰዎች እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰዱ። 14 በተጨማሪም ይሖዋ በከተሞቹ ላይ ታላቅ ፍርሃት ለቆባቸው ስለነበር በጌራራ ዙሪያ ያሉትን ከተሞች ሁሉ መቱ፤ እነሱም በከተሞቹ ውስጥ ብዙ የሚበዘበዝ ነገር ስለነበር ከተሞቹን ሁሉ በዘበዙ። 15 በተጨማሪም የእረኞችን ድንኳኖች በመምታት እጅግ ብዙ በጎችንና ግመሎችን ማረኩ፤ ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ