የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መኃልየ መኃልይ 1
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

መኃልየ መኃልይ የመጽሐፉ ይዘት

    • ሱላማዊቷ ልጃገረድ በንጉሥ ሰለሞን ሰፈር (1:1–3:5)

        • ከመዝሙሮች ሁሉ የሚበልጥ መዝሙር (1)

        • ልጃገረዷ (2-7)

        • የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች (8)

        • ንጉሡ (9-11)

          • “የወርቅ ጌጦች እንሠራልሻለን” (11)

        • ልጃገረዷ (12-14)

          • “ውዴ ለእኔ ጥሩ መዓዛ እንዳለው በከረጢት ያለ ከርቤ ነው” (13)

        • እረኛው (15)

          • ‘ፍቅሬ ሆይ፣ አንቺ ውብ ነሽ’

        • ልጃገረዷ (16, 17)

          • ‘ውዴ ሆይ፣ አንተ ውብ ነህ’ (16)

መኃልየ መኃልይ 1:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    መኃልየ መኃልይ የሚለው የመጽሐፉ ስም “ከመዝሙሮች ሁሉ የሚበልጥ መዝሙር” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 4:29, 32

መኃልየ መኃልይ 1:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 4:10

መኃልየ መኃልይ 1:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 27:9፤ መክ 9:8፤ መኃ 5:5
  • +መክ 7:1

መኃልየ መኃልይ 1:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እየሳብክ ውሰደኝ።”

  • *

    ወይም “ከወይን ጠጅ ይልቅ ስለ ፍቅር መግለጫዎችህ እናውራ።”

  • *

    ቆነጃጅቱን ያመለክታል።

መኃልየ መኃልይ 1:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 120:5፤ ሕዝ 27:21
  • +ዘፀ 36:14

መኃልየ መኃልይ 1:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሴ እጅግ የምትወድህ።”

  • *

    ወይም “በሐዘን መሸፈኛ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 6:3

መኃልየ መኃልይ 1:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ባዝራዬ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 10:28፤ 2ዜና 1:16, 17፤ መኃ 6:4

መኃልየ መኃልይ 1:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “በሹሩባዎች መካከል ሲታዩ ያምራሉ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

መኃልየ መኃልይ 1:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ክብ የወርቅ ጌጦች።”

መኃልየ መኃልይ 1:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የናርዶሴ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 4:13, 14

መኃልየ መኃልይ 1:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 30:23, 25፤ አስ 2:12፤ መዝ 45:8፤ መኃ 4:6፤ 5:13

መኃልየ መኃልይ 1:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 15:20, 62፤ 1ሳሙ 23:29፤ 2ዜና 20:2
  • +መኃ 4:13

መኃልየ መኃልይ 1:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 4:1፤ 5:2

መኃልየ መኃልይ 1:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አንተ መልከ መልካም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 5:10

መኃልየ መኃልይ 1:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የታላቁ ቤታችን።”

ተዛማጅ ሐሳብ

መኃ. 1:11ነገ 4:29, 32
መኃ. 1:2መኃ 4:10
መኃ. 1:3ምሳሌ 27:9፤ መክ 9:8፤ መኃ 5:5
መኃ. 1:3መክ 7:1
መኃ. 1:5መዝ 120:5፤ ሕዝ 27:21
መኃ. 1:5ዘፀ 36:14
መኃ. 1:7መኃ 6:3
መኃ. 1:91ነገ 10:28፤ 2ዜና 1:16, 17፤ መኃ 6:4
መኃ. 1:12መኃ 4:13, 14
መኃ. 1:13ዘፀ 30:23, 25፤ አስ 2:12፤ መዝ 45:8፤ መኃ 4:6፤ 5:13
መኃ. 1:14ኢያሱ 15:20, 62፤ 1ሳሙ 23:29፤ 2ዜና 20:2
መኃ. 1:14መኃ 4:13
መኃ. 1:15መኃ 4:1፤ 5:2
መኃ. 1:16መኃ 5:10
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
መኃልየ መኃልይ 1:1-17

መኃልየ መኃልይ

1 ከመዝሙሮች ሁሉ የሚበልጠው የሰለሞን+ መዝሙር፦*

 2 “በከንፈሩ መሳም ይሳመኝ፤

የፍቅር መግለጫዎችህ ከወይን ጠጅ ይልቅ ደስ ያሰኛሉና።+

 3 የዘይትህ መዓዛ ደስ ይላል።+

ስምህ ጥሩ መዓዛ እንዳለው የሚፈስ ዘይት ነው።+

ቆነጃጅት የሚወዱህ ለዚህ ነው።

 4 ይዘኸኝ ሂድ፤* አብረን እንሩጥ።

ንጉሡ ወደ እልፍኞቹ አስገብቶኛል!

በአንተ ደስ ይበለን፤ ሐሴትም እናድርግ።

ከወይን ጠጅ ይልቅ የፍቅር መግለጫዎችህን እናወድስ።*

አንተን መውደዳቸው* ተገቢ ነው።

 5 የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ እኔ ጥቁር ብሆንም ውብ ነኝ፤

እንደ ቄዳር+ ድንኳኖች፣ እንደ ሰለሞን ድንኳኖችም+ ነኝ።

 6 ጥቁር ስለሆንኩ ትኩር ብላችሁ አትዩኝ፤

ፀሐይ ፊቴን አክስሎታልና።

ወንድሞቼ በጣም ተቆጡኝ፤

የወይን እርሻዎች ጠባቂ አደረጉኝ፤

የገዛ ራሴን የወይን እርሻ ግን መጠበቅ አልቻልኩም።

 7 “እጅግ የምወድህ* ፍቅረኛዬ፣

መንጋህን የት እንደምታሰማራ፣+

እኩለ ቀንም ላይ የት እንደምታሳርፍ ንገረኝ።

በጓደኞችህ መንጎች መካከል

በመሸፈኛ* ፊቷን ተሸፋፍና እንደምትቅበዘበዝ ሴት ለምን ልሁን?”

 8 “አንቺ ከሴቶች ሁሉ እጅግ የተዋብሽ ሆይ፣ የማታውቂ ከሆነ

የመንጋውን ዱካ ተከትለሽ ሂጂ፤

የፍየል ግልገሎችሽንም በእረኞቹ ድንኳኖች አጠገብ አሰማሪ።”

 9 “ፍቅሬ ሆይ፣ የፈርዖንን ሠረገሎች በሚጎትቱ ፈረሶች መካከል እንዳለች ባዝራ* ውብ ነሽ።+

10 ጉንጮችሽ በማስዋቢያ ተውበዋል፤*

አንገትሽም በጨሌ ሐብል አጊጧል።

11 በብር ፈርጥ የተንቆጠቆጡ

የወርቅ ጌጦች* እንሠራልሻለን።”

12 “ንጉሡ ክብ ጠረጴዛው ጋ ተቀምጦ ሳለ

የሽቶዬ*+ መዓዛ አካባቢውን አወደው።

13 ውዴ ለእኔ ጥሩ መዓዛ እንዳለው በከረጢት ያለ ከርቤ+ ነው፤

በጡቶቼ መካከል ያድራል።

14 ውዴ በኤንገዲ+ የወይን እርሻዎች መካከል

እጅብ ብሎ እንደበቀለ የሂና ተክል+ ነው።”

15 “ፍቅሬ ሆይ፣ እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ።

እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ። ዓይኖችሽ እንደ ርግብ+ ዓይኖች ናቸው።”

16 “ውዴ ሆይ፣ እነሆ፣ አንተ ውብ* ነህ፤ ደግሞም ደስ ትላለህ።+

አልጋችን በለምለም ቅጠል መካከል ነው።

17 የቤታችን* ተሸካሚዎች አርዘ ሊባኖሶች፣

ጣሪያችንም የጥድ ዛፎች ናቸው።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ