ሆሴዕ
8 “ቀንደ መለከት ንፋ!+
2 ‘አምላካችን ሆይ፣ እኛ የእስራኤል ሰዎች እናውቅሃለን!’ እያሉ ወደ እኔ ይጮኻሉ።+
3 እስራኤል መልካም የሆነውን ነገር ገሸሽ አድርጓል።+
ጠላት ያሳደው።
4 እኔ ሳልላቸው ነገሥታትን አነገሡ።
መኳንንትን ሾሙ፤ እኔ ግን እውቅና አልሰጠኋቸውም።
5 ሰማርያ ሆይ፣ የጥጃ ጣዖትሽ ተጥሏል።+
ቁጣዬ በእነሱ ላይ ይነዳል።+
ንጹሕ መሆን* የሚሳናቸው እስከ መቼ ነው?
6 ይህ ከእስራኤል ነውና።
የእጅ ጥበብ ባለሙያ የሠራው ይህ ጥጃ አምላክ አይደለም፤
የሰማርያ ጥጃ ተሰባብሮ እንዳልነበረ ይሆናል።
7 ነፋስን ይዘራሉ፤
አውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ።+
8 የእስራኤል ሰዎች ይዋጣሉ።+
በብሔራት መካከል
ማንም እንደማይፈልገው ዕቃ ይሆናሉ።+
9 ተገልሎ እንደሚኖር የዱር አህያ ወደ አሦር ሄደዋልና።+
ኤፍሬም በገንዘብ ፍቅረኞች አፍርቷል።+
11 ኤፍሬም ኃጢአት ለመሥራት መሠዊያዎችን አብዝቷል።+
ኃጢአት የሚፈጽምባቸው መሠዊያዎች ሆነውለታል።+
13 መሥዋዕቶችን ስጦታ አድርገው ለእኔ ያቀርባሉ፤ ሥጋውንም ይበላሉ፤
ይሖዋ ግን በእነሱ አልተደሰተም።+
በደላቸውን ያስታውሳል፤ ለሠሯቸውም ኃጢአቶች ይቀጣቸዋል።+
እኔ ግን በከተሞቹ ላይ እሳት እሰዳለሁ፤
እሳቱም የእያንዳንዳቸውን ማማዎች ይበላል።”+