12 “ኤፍሬም ነፋስን ይመገባል።
ቀኑን ሙሉ የምሥራቅን ነፋስ ይከተላል።
ውሸትንና ዓመፅን ያበዛል።
ከአሦር ጋር ቃል ኪዳን ይገባሉ፤+ ወደ ግብፅም ዘይት ይወስዳሉ።+
2 ይሖዋ በይሁዳ ላይ የሚያቀርበው ክስ አለው፤+
ያዕቆብን እንደ መንገዱ ይቀጣዋል፤
እንደ ድርጊቱም ብድራት ይከፍለዋል።+
3 በማህፀን ሳለ የወንድሙን ተረከዝ ያዘ፤+
ባለ በሌለ ኃይሉም ከአምላክ ጋር ታገለ።+
4 ከመልአክ ጋር መታገሉን ቀጠለ፤ ደግሞም አሸነፈ።
ሞገስ እንዲያሳየው አልቅሶ ለመነው።”+
አምላክ በቤቴል አገኘው፤ በዚያም እኛን አነጋገረን፤+
5 እሱ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ነው።+
የመታሰቢያ ስሙ ይሖዋ ነው።+
6 “ስለዚህ ወደ አምላክህ ተመለስ፤+
ታማኝ ፍቅርንና ፍትሕን ጠብቅ፤+
ምንጊዜም በአምላክህ ተስፋ አድርግ።
7 ይሁንና በነጋዴው እጅ አታላይ ሚዛን አለ፤
እሱ ማጭበርበር ይወዳል።+
8 ኤፍሬም ‘በእርግጥ እኔ ባለጸጋ ሆኛለሁ፤+
ሀብት አካብቻለሁ።+
ደግሞም ከደከምኩበት ነገር ሁሉ ጋር በተያያዘ በደልም ሆነ ኃጢአት አያገኙብኝም’ ይላል።
9 ይሁንና ከግብፅ ምድር አንስቶ እኔ አምላክህ ይሖዋ ነኝ።+
በተወሰነው ጊዜ እንደነበረው ሁሉ፣
እንደገና በድንኳኖች እንድትቀመጡ አደርጋችኋለሁ።
10 ለነቢያቱ ተናገርኩ፤+
ራእዮቻቸውን አበዛሁ፤
በነቢያቱም በኩል ምሳሌዎችን ተናገርኩ።
11 በጊልያድ ማታለልና ውሸት አለ።+
በጊልጋል በሬዎችን ሠውተዋል፤+
በተጨማሪም መሠዊያዎቻቸው በእርሻ ትልም ላይ እንዳለ የድንጋይ ክምር ናቸው።+
12 ያዕቆብ ወደ አራም ምድር ሸሸ፤+
እስራኤል+ ሚስት ለማግኘት ሲል በዚያ አገለገለ፤+
ሚስት ለማግኘትም ሲል በግ ጠባቂ ሆነ።+
13 ይሖዋ በነቢይ አማካኝነት እስራኤልን ከግብፅ አወጣው፤+
በነቢይም አማካኝነት ጠበቀው።+
14 ኤፍሬም ግን እጅግ በደለው፤+
ደም በማፍሰስ የፈጸመው በደል በላዩ ላይ ይሆናል፤
ላመጣበትም ነቀፋ ጌታው ብድራት ይከፍለዋል።”+