የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘካርያስ 12
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘካርያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ይሖዋ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ይጠብቃል (1-9)

        • ኢየሩሳሌም፣ “ከባድ ድንጋይ” (3)

      • ለተወጋው ይለቀስለታል (10-14)

ዘካርያስ 12:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እስትንፋስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዮብ 26:7፤ ኢሳ 42:5
  • +መዝ 102:25፤ ኢሳ 45:18

ዘካርያስ 12:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ጎድጓዳ ሳህን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘካ 14:14

ዘካርያስ 12:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ለመሸከም የሚያስቸግር።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሶፎ 3:19
  • +ዘካ 14:2, 3

ዘካርያስ 12:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ሺኮች።” የነገድ አለቃ የሆነ ሰው “ሺክ” ተብሎ ይጠራ ነበር።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 41:10፤ ኢዩ 3:16፤ ዘካ 12:8

ዘካርያስ 12:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በተገቢው ቦታዋ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 41:15
  • +ሚክ 4:13፤ ዘካ 9:15
  • +ዘካ 2:4

ዘካርያስ 12:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የዳዊት ቤት ግርማና።”

  • *

    ወይም “ግርማ።”

ዘካርያስ 12:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እጅግ ደካማ የሆነው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 23:6፤ ኢዩ 3:16፤ ዘካ 2:5፤ 9:15
  • +ዘፀ 14:19፤ 23:20

ዘካርያስ 12:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 54:17፤ ሐጌ 2:22

ዘካርያስ 12:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 19:34, 37፤ 20:27፤ ራእይ 1:7

ዘካርያስ 12:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 23:29፤ 2ዜና 35:22

ዘካርያስ 12:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 5:13, 14፤ ሉቃስ 3:23, 31

ዘካርያስ 12:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 6:16
  • +ዘፀ 6:17፤ 1ዜና 23:10

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘካ. 12:1ኢዮብ 26:7፤ ኢሳ 42:5
ዘካ. 12:1መዝ 102:25፤ ኢሳ 45:18
ዘካ. 12:2ዘካ 14:14
ዘካ. 12:3ሶፎ 3:19
ዘካ. 12:3ዘካ 14:2, 3
ዘካ. 12:5ኢሳ 41:10፤ ኢዩ 3:16፤ ዘካ 12:8
ዘካ. 12:6ኢሳ 41:15
ዘካ. 12:6ሚክ 4:13፤ ዘካ 9:15
ዘካ. 12:6ዘካ 2:4
ዘካ. 12:8ኤር 23:6፤ ኢዩ 3:16፤ ዘካ 2:5፤ 9:15
ዘካ. 12:8ዘፀ 14:19፤ 23:20
ዘካ. 12:9ኢሳ 54:17፤ ሐጌ 2:22
ዘካ. 12:10ዮሐ 19:34, 37፤ 20:27፤ ራእይ 1:7
ዘካ. 12:112ነገ 23:29፤ 2ዜና 35:22
ዘካ. 12:122ሳሙ 5:13, 14፤ ሉቃስ 3:23, 31
ዘካ. 12:13ዘፀ 6:16
ዘካ. 12:13ዘፀ 6:17፤ 1ዜና 23:10
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘካርያስ 12:1-14

ዘካርያስ

12 የፍርድ መልእክት፦

“ስለ እስራኤል የተነገረው የይሖዋ ቃል።”

ሰማያትን የዘረጋው፣+

የምድርን መሠረት የጣለውና+

የሰውን መንፈስ* በውስጡ የሠራው ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

2 “እነሆ፣ ኢየሩሳሌምን በዙሪያዋ ያሉትን ሕዝቦች ሁሉ የምታንገዳግድ ጽዋ* አደርጋታለሁ፤ ጠላት ይሁዳንም ሆነ ኢየሩሳሌምን ይከባል።+ 3 በዚያ ቀን ኢየሩሳሌምን ለሕዝቦች ሁሉ ከባድ* ድንጋይ አደርጋታለሁ። ድንጋዩን የሚያነሱት ሁሉ ክፉኛ መጎዳታቸው የማይቀር ነው፤+ የምድር ብሔራትም ሁሉ በእሷ ላይ ይሰበሰባሉ።+ 4 በዚያ ቀን” ይላል ይሖዋ፣ “እያንዳንዱን ፈረስ በድንጋጤ፣ ጋላቢውንም በእብደት እመታለሁ። ዓይኖቼን በይሁዳ ቤት ላይ አደርጋለሁ፤ የሕዝቦቹን ፈረሶች ሁሉ ግን አሳውራለሁ። 5 የይሁዳም አለቆች* በልባቸው ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ አምላካቸው ስለሆነ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ብርታታችን ናቸው’ ይላሉ።+ 6 በዚያን ቀን የይሁዳን አለቆች በእንጨት መካከል እንዳለ የሚነድ ምድጃና በታጨደ እህል መካከል እንዳለ የሚነድ ችቦ አደርጋቸዋለሁ፤+ እነሱም በስተ ቀኝም ሆነ በስተ ግራ፣ በዙሪያቸው ያሉትን ሕዝቦች ሁሉ ይበላሉ፤+ ኢየሩሳሌምም በገዛ ስፍራዋ* ይኸውም በኢየሩሳሌም ዳግመኛ የሰዎች መኖሪያ ትሆናለች።+

7 “የዳዊት ቤት ውበትና* የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ውበት* ከይሁዳ እጅግ የበለጠ እንዳይሆን ይሖዋ በመጀመሪያ የይሁዳን ድንኳኖች ያድናል። 8 በዚያ ቀን ይሖዋ በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ዙሪያ መከታ ይሆናል፤+ በዚያም ቀን ከእነሱ መካከል የሚሰናከለው* እንደ ዳዊት ይሆናል፤ የዳዊትም ቤት እንደ አምላክ፣ በፊታቸውም እንደሚሄደው የይሖዋ መልአክ ይሆናል።+ 9 ደግሞም በዚያ ቀን በኢየሩሳሌም ላይ የሚመጡትን ብሔራት ሁሉ ለማጥፋት ቆርጬ እነሳለሁ።+

10 “በዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የሞገስንና የምልጃን መንፈስ አፈሳለሁ፤ እነሱም የወጉትን ያዩታል፤+ ለአንድያ ልጅም እንደሚለቀስ ያለቅሱለታል፤ ለበኩር ልጅ እንደሚለቀሰው ያለ መራራ ለቅሶም ያለቅሱለታል። 11 በዚያን ቀን በኢየሩሳሌም የሚለቀሰው ለቅሶ በመጊዶ ሜዳ፣ በሃዳድሪሞን እንደተለቀሰው ለቅሶ ታላቅ ይሆናል።+ 12 ምድሪቱም ታለቅሳለች፤ እያንዳንዱም ቤተሰብ ለየብቻው ያለቅሳል፤ የዳዊት ቤት ቤተሰብ ለብቻው፣ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣ የናታን+ ቤት ቤተሰብ ለብቻው፣ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣ 13 የሌዊ+ ቤት ቤተሰብ ለብቻው፣ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣ የሺምአይ+ ቤት ቤተሰብ ለብቻው፣ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣ 14 የቀሩትም ቤተሰቦች በሙሉ፣ እያንዳንዱ ቤተሰብ ለብቻው፣ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው ያለቅሳሉ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ