የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘካርያስ 13
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘካርያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ጣዖታትና ሐሰተኛ ነቢያት ይወገዳሉ (1-6)

        • ሐሰተኛ ነቢያት ኀፍረት ይከናነባሉ (4-6)

      • “እረኛውን ምታ” (7-9)

        • አንድ ሦስተኛው ይነጥራል (9)

ዘካርያስ 13:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 36:25, 29

ዘካርያስ 13:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 23:13
  • +ዘዳ 13:5

ዘካርያስ 13:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 13:6-9፤ 18:20

ዘካርያስ 13:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 1:8፤ ማቴ 3:4

ዘካርያስ 13:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በእጆችህ መካከል።” በደረቱ ወይም በጀርባው ላይ ማለት ነው።

ዘካርያስ 13:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በጎቹም ይበተኑ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 34:23፤ ሚክ 5:4፤ ዮሐ 10:11፤ ዕብ 13:20
  • +ኢሳ 53:8፤ ዳን 9:26፤ ሥራ 3:18
  • +ማቴ 26:31, 55, 56፤ ማር 14:27, 50፤ ዮሐ 16:32

ዘካርያስ 13:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ይሞታል።”

ዘካርያስ 13:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሚል 3:2, 3
  • +ኤር 30:22

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘካ. 13:1ሕዝ 36:25, 29
ዘካ. 13:2ዘፀ 23:13
ዘካ. 13:2ዘዳ 13:5
ዘካ. 13:3ዘዳ 13:6-9፤ 18:20
ዘካ. 13:42ነገ 1:8፤ ማቴ 3:4
ዘካ. 13:7ሕዝ 34:23፤ ሚክ 5:4፤ ዮሐ 10:11፤ ዕብ 13:20
ዘካ. 13:7ኢሳ 53:8፤ ዳን 9:26፤ ሥራ 3:18
ዘካ. 13:7ማቴ 26:31, 55, 56፤ ማር 14:27, 50፤ ዮሐ 16:32
ዘካ. 13:9ሚል 3:2, 3
ዘካ. 13:9ኤር 30:22
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘካርያስ 13:1-9

ዘካርያስ

13 “በዚያ ቀን፣ ኃጢአታቸውንና ርኩሰታቸውን ለማንጻት ለዳዊት ቤትና ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የውኃ ጉድጓድ ይቆፈራል።+

2 “በዚያ ቀን” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ “የጣዖቶቹን ስም ከምድሪቱ ላይ እደመስሳለሁ፤+ እነሱም ዳግመኛ አይታወሱም፤ ደግሞም ነቢያቱንና የርኩሰት መንፈሱን ከምድሪቱ ላይ አስወግዳለሁ።+ 3 አንድ ሰው ዳግመኛ ትንቢት ቢናገር የወለዱት አባትና እናቱ ‘በይሖዋ ስም ሐሰት ስለተናገርክ በሕይወት አትኖርም’ ይሉታል። ደግሞም የወለዱት አባትና እናቱ ትንቢት በመናገሩ ይወጉታል።+

4 “በዚያ ቀን እያንዳንዱ ነቢይ ትንቢት በሚናገርበት ጊዜ ሁሉ በገዛ ራእዩ ያፍራል፤ ሰዎችንም ለማታለል የነቢያት ዓይነት ፀጉራም ልብስ+ አይለብስም። 5 ደግሞም እንዲህ ይላል፦ ‘እኔ ነቢይ አይደለሁም። ይልቁንም አራሽ ነኝ፤ ምክንያቱም አንድ ሰው ልጅ ሳለሁ ባሪያ አድርጎ ገዝቶኛል።’ 6 አንድ ሰውም ‘በትከሻዎችህ መካከል* ያሉት ቁስሎች ምንድን ናቸው?’ ብሎ ቢጠይቀው ‘በወዳጆቼ ቤት ሳለሁ የቆሰልኩት ነው’ ይላል።”

 7 “ሰይፍ ሆይ፣ በእረኛዬ+ ይኸውም

በወዳጄ ላይ ንቃ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።

“እረኛውን ምታ፤+ መንጋውም ይበተን፤*+

እኔም እጄን ታናናሽ በሆኑት ላይ አዞራለሁ።”

 8 “በምድሪቱም ሁሉ” ይላል ይሖዋ፣

“በእሷ ላይ ካለው ሁለት ሦስተኛው ተመትቶ ይጠፋል፤*

አንድ ሦስተኛው ግን በውስጧ ይቀራል።

 9 ደግሞም አንድ ሦስተኛው በእሳት ውስጥ እንዲያልፍ አደርጋለሁ፤

ብር እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፤

ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ።+

እነሱ ስሜን ይጠራሉ፤

እኔም እመልስላቸዋለሁ።

‘እነሱ ሕዝቤ ናቸው’ እላለሁ፤+

እነሱ ደግሞ ‘ይሖዋ አምላካችን ነው’ ይላሉ።”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ