ዘፍጥረት 41:15, 16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ከዚያም ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፦ “ሕልም አይቼ ነበር፤ የሚፈታልኝ ሰው ግን አልተገኘም። አንተ ሕልም ሰምተህ መፍታት እንደምትችል ሰማሁ።”+ 16 በዚህ ጊዜ ዮሴፍ ለፈርዖን “ኧረ እኔ እዚህ ግባ የምባል ሰው አይደለሁም! ለፈርዖን መልካም የሆነውን ነገር የሚያሳውቀው አምላክ ነው”+ ሲል መለሰለት። ዳንኤል 2:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 ይሁንና ሚስጥርን የሚገልጥ አምላክ በሰማያት አለ፤+ እሱም በመጨረሻዎቹ ቀናት የሚሆነውን ነገር ለንጉሥ ናቡከደነጾር አሳውቆታል። በአልጋህ ላይ ተኝተህ ሳለህ ያየኸው ሕልምና የተመለከትካቸው ራእዮች እነዚህ ናቸው፦ ዳንኤል 2:45 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 45 አንድ ድንጋይ የሰው እጅ ሳይነካው ከተራራው ተፈንቅሎ ብረቱን፣ መዳቡን፣ ሸክላውን፣ ብሩንና ወርቁን ሲያደቅ እንዳየህ ሁሉ እንዲሁ ይሆናል።+ ታላቁ አምላክ ወደፊት የሚሆነውን ነገር ለንጉሡ አሳውቆታል።+ ሕልሙ እውነት፣ ትርጉሙም አስተማማኝ ነው።”
15 ከዚያም ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፦ “ሕልም አይቼ ነበር፤ የሚፈታልኝ ሰው ግን አልተገኘም። አንተ ሕልም ሰምተህ መፍታት እንደምትችል ሰማሁ።”+ 16 በዚህ ጊዜ ዮሴፍ ለፈርዖን “ኧረ እኔ እዚህ ግባ የምባል ሰው አይደለሁም! ለፈርዖን መልካም የሆነውን ነገር የሚያሳውቀው አምላክ ነው”+ ሲል መለሰለት።
28 ይሁንና ሚስጥርን የሚገልጥ አምላክ በሰማያት አለ፤+ እሱም በመጨረሻዎቹ ቀናት የሚሆነውን ነገር ለንጉሥ ናቡከደነጾር አሳውቆታል። በአልጋህ ላይ ተኝተህ ሳለህ ያየኸው ሕልምና የተመለከትካቸው ራእዮች እነዚህ ናቸው፦
45 አንድ ድንጋይ የሰው እጅ ሳይነካው ከተራራው ተፈንቅሎ ብረቱን፣ መዳቡን፣ ሸክላውን፣ ብሩንና ወርቁን ሲያደቅ እንዳየህ ሁሉ እንዲሁ ይሆናል።+ ታላቁ አምላክ ወደፊት የሚሆነውን ነገር ለንጉሡ አሳውቆታል።+ ሕልሙ እውነት፣ ትርጉሙም አስተማማኝ ነው።”