ኢዮብ 1:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 የእውነተኛው አምላክ ልጆች*+ በይሖዋ ፊት ለመቆም+ የሚገቡበት ቀን በደረሰ ጊዜ ሰይጣንም+ መጥቶ በመካከላቸው ቆመ።+ ኢዮብ 38:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 አጥቢያ ከዋክብት+ በአንድነት እልል ሲሉ፣የአምላክም ልጆች ሁሉ*+ በደስታ ሲጮኹ አንተ የት ነበርክ? 2 ጴጥሮስ 2:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ደግሞም አምላክ ኃጢአት የሠሩትን መላእክት ከመቅጣት ወደኋላ አላለም፤+ ይልቁንም በድቅድቅ ጨለማ አስሮ* በማስቀመጥ ፍርዳቸውን እንዲጠባበቁ+ ወደ እንጦሮጦስ* ጣላቸው።+ ይሁዳ 6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 በተጨማሪም መጀመሪያ የነበራቸውን ቦታ ያልጠበቁትንና ተገቢ የሆነውን የመኖሪያ ስፍራቸውን የተዉትን መላእክት+ በታላቁ ቀን ለሚፈጸምባቸው ፍርድ በዘላለም እስራት በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ አቆይቷቸዋል።+
4 ደግሞም አምላክ ኃጢአት የሠሩትን መላእክት ከመቅጣት ወደኋላ አላለም፤+ ይልቁንም በድቅድቅ ጨለማ አስሮ* በማስቀመጥ ፍርዳቸውን እንዲጠባበቁ+ ወደ እንጦሮጦስ* ጣላቸው።+
6 በተጨማሪም መጀመሪያ የነበራቸውን ቦታ ያልጠበቁትንና ተገቢ የሆነውን የመኖሪያ ስፍራቸውን የተዉትን መላእክት+ በታላቁ ቀን ለሚፈጸምባቸው ፍርድ በዘላለም እስራት በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ አቆይቷቸዋል።+