ዘፍጥረት 41:51 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 51 ዮሴፍም “አምላክ የደረሰብኝን ችግር ሁሉና የአባቴን ቤት በሙሉ እንድረሳ አደረገኝ” በማለት ለበኩር ልጁ ምናሴ*+ የሚል ስም አወጣለት። ዘፍጥረት 46:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ዮሴፍ በግብፅ ምድር ሳለ ምናሴንና+ ኤፍሬምን*+ ወለደ፤ እነዚህም የኦን* ካህን የሆነው የጶጥፌራ ልጅ አስናት+ የወለደችለት ናቸው።