13 በዚያው ቀን ኖኅ ከወንዶች ልጆቹ ከሴም፣ ከካምና ከያፌት+ እንዲሁም ከሚስቱና ከሦስቱ የልጆቹ ሚስቶች ጋር ወደ መርከቡ ገባ።+ 14 ከእነሱም ጋር እያንዳንዱ የዱር እንስሳ እንደየወገኑ፣ እያንዳንዱ የቤት እንስሳ እንደየወገኑ፣ በምድር ላይ ያለ መሬት ለመሬት የሚሄድ እያንዳንዱ እንስሳ እንደየወገኑ፣ እያንዳንዱ የሚበር ፍጥረት እንደየወገኑ እንዲሁም እያንዳንዱ ወፍና እያንዳንዱ ክንፍ ያለው ፍጡር ወደ መርከቡ ገባ።