ዘፍጥረት 16:1, 2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 የአብራም ሚስት ሦራ ለአብራም ልጆች አልወለደችለትም ነበር፤+ ይሁንና አጋር+ የምትባል አንዲት ግብፃዊት አገልጋይ ነበረቻት። 2 በመሆኑም ሦራ አብራምን እንዲህ አለችው፦ “እንግዲህ እንደምታየው ይሖዋ ልጆች እንዳልወልድ አድርጎኛል። እባክህ ከአገልጋዬ ጋር ግንኙነት ፈጽም። ምናልባትም በእሷ አማካኝነት ልጆች ላገኝ እችላለሁ።”+ ስለሆነም አብራም የሦራን ቃል ሰማ። ሮም 4:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 እምነቱ ባይዳከምም እንኳ 100 ዓመት ገደማ+ ሆኖት ስለነበር የሞተ ያህል ስለሆነው የገዛ ራሱ አካል እንዲሁም ሙት* ስለሆነው የሣራ ማህፀን አሰበ።+ ዕብራውያን 11:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ሣራም የተስፋን ቃል የሰጠው እሱ ታማኝ* እንደሆነ አድርጋ ስላሰበች ዕድሜዋ ካለፈ በኋላም እንኳ ዘር ለመፀነስ በእምነት ኃይል አገኘች።+
16 የአብራም ሚስት ሦራ ለአብራም ልጆች አልወለደችለትም ነበር፤+ ይሁንና አጋር+ የምትባል አንዲት ግብፃዊት አገልጋይ ነበረቻት። 2 በመሆኑም ሦራ አብራምን እንዲህ አለችው፦ “እንግዲህ እንደምታየው ይሖዋ ልጆች እንዳልወልድ አድርጎኛል። እባክህ ከአገልጋዬ ጋር ግንኙነት ፈጽም። ምናልባትም በእሷ አማካኝነት ልጆች ላገኝ እችላለሁ።”+ ስለሆነም አብራም የሦራን ቃል ሰማ።