ዘፍጥረት 12:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ስለዚህ አብራም ልክ ይሖዋ በነገረው መሠረት ወጣ፤ ሎጥም አብሮት ሄደ። አብራም ከካራን በወጣበት ጊዜ ዕድሜው 75 ዓመት ነበር።+ ዘፍጥረት 27:42, 43 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 42 ርብቃ ታላቁ ልጇ ኤሳው ያለው ነገር ሲነገራት ወዲያውኑ ለታናሹ ልጇ ለያዕቆብ እንዲህ የሚል መልእክት ላከችበት፦ “ወንድምህ ኤሳው አንተን በመግደል ሊበቀልህ እያሰበ ነው።* 43 እንግዲህ ልጄ እኔ የምልህን አድርግ። ተነስተህ በካራን ወደሚገኘው ወደ ወንድሜ ወደ ላባ ሽሽ።+ የሐዋርያት ሥራ 7:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 እስጢፋኖስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ወንድሞችና አባቶች ሆይ፣ ስሙ። አባታችን አብርሃም በካራን መኖር ከመጀመሩ በፊት በሜሶጶጣሚያ ሳለ የክብር አምላክ ተገለጠለት፤+ የሐዋርያት ሥራ 7:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 እሱም ከከለዳውያን አገር ወጥቶ በካራን መኖር ጀመረ። አባቱ ከሞተ+ በኋላ ደግሞ አምላክ ከዚያ ተነስቶ አሁን እናንተ ወደምትኖሩበት ወደዚህ ምድር እንዲዛወር አደረገው።+
42 ርብቃ ታላቁ ልጇ ኤሳው ያለው ነገር ሲነገራት ወዲያውኑ ለታናሹ ልጇ ለያዕቆብ እንዲህ የሚል መልእክት ላከችበት፦ “ወንድምህ ኤሳው አንተን በመግደል ሊበቀልህ እያሰበ ነው።* 43 እንግዲህ ልጄ እኔ የምልህን አድርግ። ተነስተህ በካራን ወደሚገኘው ወደ ወንድሜ ወደ ላባ ሽሽ።+
2 እስጢፋኖስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ወንድሞችና አባቶች ሆይ፣ ስሙ። አባታችን አብርሃም በካራን መኖር ከመጀመሩ በፊት በሜሶጶጣሚያ ሳለ የክብር አምላክ ተገለጠለት፤+
4 እሱም ከከለዳውያን አገር ወጥቶ በካራን መኖር ጀመረ። አባቱ ከሞተ+ በኋላ ደግሞ አምላክ ከዚያ ተነስቶ አሁን እናንተ ወደምትኖሩበት ወደዚህ ምድር እንዲዛወር አደረገው።+