-
ዘፍጥረት 28:16-19አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
16 ከዚያም ያዕቆብ ከእንቅልፉ ነቅቶ “በእርግጥም በዚህ ስፍራ ይሖዋ አለ፤ እኔ ግን ይህን አላወቅኩም ነበር” አለ። 17 እሱም በፍርሃት ተዋጠ፤ እንዲህም አለ፦ “ይህ ስፍራ እንዴት የሚያስፈራ ነው! ይህ የአምላክ ቤት እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም፤+ ይህ የሰማያት በር ነው።”+ 18 በመሆኑም ያዕቆብ በማለዳ ተነሳ፤ ተንተርሶት የነበረውን ድንጋይ ወስዶ እንደ ዓምድ አቆመው፤ በአናቱም ላይ ዘይት አፈሰሰበት።+ 19 ስለዚህ ያን ቦታ ቤቴል* አለው፤ የከተማዋ የቀድሞ ስም ግን ሎዛ+ ነበር።
-